Get Mystery Box with random crypto!

✞ ቆሜ አለው ✞ ቆሜ አለው ሁሉንም አልፌ በምልጃው ከሞት ተርፌ ፀሎቱ ኃይል አደረገልኝ ገብረ መ | ዘ_መርቆሬዎስ

✞ ቆሜ አለው ✞

ቆሜ አለው ሁሉንም አልፌ
በምልጃው ከሞት ተርፌ
ፀሎቱ ኃይል አደረገልኝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ እረዳኝ (2)

/አዝ=====

አበቃ ሲባል አልቆ ተስፋዬ
በሀዘን ብዛት ሲፈስ እንባዬ
ገብረ ህይወት መጣ ፃድቁ አባቴ
ደዌ ተሻረ ፀና ጉልበቴ (2)

/አዝ=====

የጭንቁን ዘመን እረስቻለው
ከሰዎች እኩል በክብር ቆሜ አለው
እርሱ ባይቆምልኝ በእግዚአብሔር ፊት
አልቆምም ነበር ዛሬ በህይወት
አልኖርም ነበር ዛሬ በህይወት

/አዝ=====

በጽድቅ ክንዱ እየደገፈ
ክፉን በምልጃው እያሳለፈ
ስለ ቃልኪዳኑ በስሙ ታምኜ
አልጠግብም ፃድቁን እርሱን አመስግኜ (2)

/አዝ=====

በደዌ ኃጢያት የተጠቃችሁ
ሞትን በችግር ለጠበቃችሁ
ፃድቁን ጥሩት ይረዳችኋል
ከአፈር ከትቢያ ያነሳችኋል (2)

#ዘ-መርቆሬዎስ ወጣት ማህበር

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥ @Merkorawos ✥
✥ @Merkorawos ✥
✥  #ዘ_መርቆሬዎስ ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥