Get Mystery Box with random crypto!

merkatotube

የቴሌግራም ቻናል አርማ merkatotube — merkatotube M
የቴሌግራም ቻናል አርማ merkatotube — merkatotube
የሰርጥ አድራሻ: @merkatotube
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.03K
የሰርጥ መግለጫ

Important Ethiopian and international news.
If you have tips/ጥቆማ @merkatotube_bot
We are open 24/7

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-01 00:25:05
ጆ ባይደን የአሜሪካንን ምርጥ የጦር ጄቶች ለዩክሬን አልሰጥም አሉ
***
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እጅግ ዘመናዊ ናቸው የሚባሉትን አሜሪካ ሰራሽ ኤፍ-16 የጦር ጄቶችን ለዩክሬን አሳልፈው እንደማይሰጡ ገለጹ።

ጆ ባይደን ትናንት ሰኞ ከጋዜጠኛ “ኤፍ-16 ጄቶች ለዩክሬን ይሰጣሉ ወይ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “በፍጹም” የሚል አጭር መልስ ሰጥተዋል።

ጆ ባይደን ይህን ከማለታቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጀርመንም በተመሳሳይ ተዋጊ ጄቶቿን ለዩክሬን አሳልፋ እንደማትሰጥ ይፋ አድርጋ ነበር።

ዩክሬን በበኩሏ የአየር ክልሏ በሩሲያ በተደጋጋሚ እየተጣሰ ስለሆነ ያን ለመቋቋም የግድ ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ያስፈልጉኛል እያለች ነው።

“ኤፍ-16” ተዋጊ ጄቶች በዓለም ላይ አስተማማኝ ከሚባሉ የአየር ላይ ውጊያ ጄቶች የሚመደቡ ሲሆን፣ እነዚህኑ ጄቶች ከአሜሪካ ባሻገር ቤልጂየም እና ፓኪስታን ታጥቀዋቸዋል።

ዩክሬን አሁን እየተጠቀመችባቸው ያሉት ብዙዎቹ የጦር ጄቶች በሶቭየት ኅብረት ጊዜ የተመረቱ ናቸው።

እነዚህ ያረጁ ያፈጁ ጄቶች አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበረው ዩክሬን ነጻነቷን ከማወጇ በፊት ነው።

በዚህም የተነሳ ዩክሬን ሩሲያን በአየር ልትቋቋማት ተስኗታል።
@merkatotube @merkatotube_bot
167 views21:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 23:25:06
ጺም ስለሚያበቅሉ ሴቶች ሳይንስ ምን ይላል?
***
ጺም ማብቀሏ የፈጣሪ ስጦታ መሆኑን የምታምነው አያንቱ፣ ብዙ ሰዎችም እንዳትላጨው ቢመክሯትም እርሷ ግን ለተወሰነ ጊዜ ስትላጨው ነበር።

“ከፊቴ ላይ ለማጥፋት ብዬ የተለያዩ ቅባቶችን እቀባ ነበር። ቤተሰቦቼ ግን እንዳላጠፋው ይነግሩኝ ነበር። በተለይም እናቴ ‘ልጄ እንደ እናቴ ጺም አላት’ ብላ በጣም ትደሰት ነበር።”

በተለይ የወንድ ጓደኛዋ ጺሟን ወድዶ ለፍቅር እንደጠየቃት ትናገራለች።

ከጓደኛዋ ጋር ፍቅር ከጀመረች በኋላም “ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ እንዳትቆረጪው በማለት ያበረታታኛል” ትላለች።

ይህንኑ ጺሟን በተመለከተ የጤና ባለሙያ ለማናገር ቀጠሮ ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ የትምህርት ዕድል በማግኘቷ በቀጠሮዋ ላይ ሳትገኝ ቀርታለች።

“ከዚያ በኋላም ምን ይሰራልኛል ብዬ ተውኩት” ትላለች።

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የማህፀን እና ጽንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አዲሱ ግርማ በወንዶች ላይ ብቻ የሚወጣ ፀጉር በሴቶች ላይ ሲወጣ ችግር እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወንዶች በተፈጥሮ በፊት እና በደረታቸው ላይ ፀጉር ይበቅላል። ሴቶች ደግሞ በተፈጥሮ ይህንን ፀጉር አያበቅሉም።

በመሆኑም እንደ አያንቱ ሴቶች ጺም ካበቀሉ የሆርሞን መጠን መዛባት ምልክት መሆኑን እና ሕክምናም ያለው ነው።

ይህ መዛባትም በሴቶች ላይ ብቻ የሚከሰት መሆኑን የሚናገሩት የሕክምና ባለሙያው፣ በሳይንሳዊ ስሙ “ሂርስቲዝም (Hirstism)” እንደሚባል ይባላል። ምን መፍትሄ አለው?
@merkatotube @merkatotube_bot
285 views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 22:25:14
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስለተከሰተው ሁኔታ እስካሁን የምናውቀው
***
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከእውቅናዬ ውጪ ተሰጥቷል ያለችውን የጳጳሳት ሹመት ተከትሎ ጥር 18/2015 ዓ.ም ውሳኔ አሳልፋለች።

በፓሪያሪኩ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ጵጵስና ሹመት የሰጡ እና የተቀበሉ አባቶች ከቤተክርስቲያኒቷ ተወግዘው እንዲለዩ ወስኗል።

በዚህም አባ ሳዊሮስ፣ አባ አዎስጣጤዎስ እና አባ ዜናማርቆስ ከድቁና ጀምሮ ያለው ክህነተ ሥልጣናቸውን አንስቶ ያወገዘ ሲሆን፣ ሕገ ወጥ ሹመቱን የተቀበሉ 25 መነኮሳት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ጉባኤ ተለይተው እንዲወገዙ ወስኗል።

ይህንን ውሳኔም ተከትሎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኗን ቀኖና እና ሕግ ጥሰዋል ተብለው በመወገዝ እና እንዲለዩ የተወሰነባቸው አባቶች ውሳኔውን እንደማይቀበሉ አሳውቀዋል።
ይህንን ከስተት ተከትሎ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
@merkatotube @merkatotube_bot
491 views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 18:30:07
በደቡብ ክልል ለሚካሄደው ሕዝበ-ውሳኔ ስኬታማነት በቂ ዝግጅት ተደርጓል-ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ሕዝበ-ውሳኔ በተሳካ መልኩ ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ÷በደቡብ ክልል ሥር የሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ-ውሳኔ ስኬታማ ክንውን በቦርዱ በኩል በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በምርጫ ሂደት የሚያጋጥሙ ጉድለቶች የሚሻሻሉበት እና አፋጣኝ እርማት የሚወሰድበት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱንም ገልጸዋል።

በሕዝበ-ውሳኔው በነበረው የመቀጠል ወይም በአዲስ መደራጀት በሚሉት ሁለት የተለያዩ አማራጮች ክርክርና ውይይት እንዲያደርጉና የተሻለ የምርጫ ልምምድ እንዲኖር ተሰርቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ እና ሌሎች የሲቪል ማህበራት በምርጫ ሂደቱ መራጮች እንዲሳተፉ በማስተማር እና አፈጻጸሙን እንዲከታተሉ ፈቃድ መሰጠቱንም ተናግረዋል።

ለምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት ሰብሳቢዋ፤ የምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች በ31 ማዕከላት እንዲደርሱ የማጓጓዝ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም ሕዝበ-ውሳኔውን ለማካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉንና የድምፅ አሰጣጡን ለማከናወን የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውንም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም የሕዝበ- ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ የሚከናወን መሆኑ ታውቋል።
@merkatotube @merkatotube_bot
912 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:45:07
ዛሬ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ቡድን ሰብስቤ አነጋግሬያለሁ። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያሉ ግብአቶችን የማምጣት እና ለትግበራ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን የማመንጨት ሥራ እንዲሠሩ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ።
@merkatotube @merkatotube_bot
992 views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:30:07
ተቋማት ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ሊደግፉት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑን ተቋማት በልዩ ሁኔታ ሊደግፉት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

በቅርቡ ወደ ዉይይት እንደሚገባ የተነገረለት ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን የነበረዉ ሂደትና ቅቡልነቱ መልካም እንደሆነ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸዉ ኮሚሽነሮች ተናግረዋል፡፡

ያለፉ ስብራቶች እንዲጠገኑ ትዉልድም እንዲድን ፈጣን ዉይይት ዛሬም ልዩ አማራጭ ነዉ ያሉት የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ÷ ችግሮችን በጊዜ እና በፍጥነት ፈቶ ወደ እንድነት ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው ፥ ዉይይቱ ሲጀመር የሚፈጠሩ እንቅፋቶች እንዳይኖሩ ተቋማት ግንባር ቀደም መሆን አለባቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ፥ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መገናኛ ብዙሃንና የሲቪክ ማህበራት ለምክክር ኮሚሽኑ ድጋፍ ለማድረግ ሁሉንም በሮቻቸውን ክፍት የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባቸዉም ነው ያነሱት፡፡

ይህ ምክክር የተሳካና ተምሳሌታዊ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ የገለፁት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ÷ ለዲሞክራሲም መሰረት በመጣል ቀጣዩ ትዉልድም በተሻለ መንገድ እንዲጓዝ ያግዛል ነዉ ያሉት፡፡

በሃይማኖት ወንድራድ
@merkatotube @merkatotube_bot
997 views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:15:06
ወላጅ አባቱን በሽጉጥ ተኩሶ የገደለው ግለሰብ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወላጅ አባቱን በሽጉጥ ተኩሶ የገደለው ነብዩ ዘላለም የተባለ ግለሰብ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ነብዩ ዘላለም ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ቦሌ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት ቴዲ ባር አካባቢ ወላጅ አባቱ ሟች ዘላለም ገ/ሚካኤልን በሽጉጥ ጭንቅላታቸውን ሶስት ቦታ ላይ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ በማድረጉ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539(1)(ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ክርክሩን የመራው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት መሆኑ ተገጿል፡፡

ተከሳሹ ክሱ በችሎት ተነቦለት ድርጊቱን ስለመፈጸሙ ተጠይቆ ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ በበቂ ማስረጃ በማረጋገጡ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው ፍርድ ቤት ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሹ ላይ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት በ22 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣና ከማህበራዊ አገልግሎት ለ5 ዓመት እንዲታገድ ሲል ወስኖበታል፡፡

በተጨማሪም ÷ውሳኔው ከተሰጠ በኋላ ተከሳሽ ዳኞችን በችሎት ፊት "ውሳኔያችሁ የማይረባ ነው ከተፈታሁ በኋላ አሳያችኋለሁ"በማለቱ በችሎት መድፈር በ1 ዓመት ቀላል እስራት መቀጣቱን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@merkatotube @merkatotube_bot
937 views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 12:30:06
የአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አለም አቀፍ የስጋ ደዌ ቀን በኢትዮጵያ ለ24ኛ ጊዜ ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ69ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ አቶ ጌታቸው በዳኔ ጉዳዩን አስመልክቶ እንደተናገሩት ፥ የስጋ ደዌ ተጠቂዎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ፍላጎቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ግድ ይላል ፡፡

ሚኒስቴሩ ለማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች የተጋለጡ ዜጎች እንዲቋቋሙና ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተለይም የአካል ጉዳተኞች የእኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በጊዜያዊነት ድጋፍ ላይ ብቻ ያልተመሰረተ ዘላቂነት ያለው የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን የመገንባት ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማንሳታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሀና የሺንጉስ በበኩላቸው ÷ የበዓሉ ዓላማ በስጋ ደዌ ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰውን ማገለልና መድሎ ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ የሚያስችሉ ስራዎችን በስፋት ለመስራት ነው ብለዋል፡፡

የስጋ ደዌ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ደረጃ 2 የአካል ጉዳት የተገኘባቸው አዳዲስ የስጋ ደዌ ህሙማን መጠን ከ5 በመቶ በታች ለማድረስ እየተሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
@merkatotube @merkatotube_bot
1.1K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 12:15:07
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በግማሽ ዓመቱ 18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የገቢ እና እቅድ ሥራ ሂደት ዳይሬክተር አትንኩት በላይ እንደገለጹት፥ በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ተሰርቷል።

ከመደበኛ ግብር ከፋዮች እና መዘጋጀ ቤት አገልግሎት 22 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር ጠቁመዋል።

ከዚህ ውስጥም በግማሽ ዓመቱ 18 ቢሊየን 280 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ከ343 ሺህ 969 በላይ ግብር ከፋዮች የተገኘ መሆኑን ዳይሬክተሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በዚህም የእቅዱን 81 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው ገለጹት።

የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የግንዛቤ መፍጠር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻሉንም ጠቁመዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ ማቅረብ፣ ያለ ደረሰኝ አገልግሎት እና እቃ መሸጥ እንዲሁም ከዋጋ አሳንሶ ደረሰኝ መቁረጥ የተስተዋሉ ተግዳሮቶች መሆናቸውን አንስተዋል።

ከ467 ሚሊየን በላይ ብር የሀሰተኛ ደረሰኝ ግዢ ያቀረቡ 879 ግብር ከፋዮች ደረሰኙ ውድቅ እንደተደረገባቸውም አብራርተዋል።

በመላኩ ገድፍ
@merkatotube @merkatotube_bot
987 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 11:45:06
ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው በኢትዮጵያ ከቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው በኢትዮጵያ ከቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚሮዝላቭ ኮሴክ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው÷ በኢትዮጵያ እና በቼክ ሪፐብሊክ ዘለቄታዊ ግንኙነት ላይ በስፋት መምከራቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@merkatotube @merkatotube_bot
1.0K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ