2022-08-30 09:05:35
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር ከተቋሙ በከፍተኛ ውጤት ለተመረቁ 18 ተማሪዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ነጻ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል አወዳደሮ መስጠት እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡
የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የተመረቁና ለወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ መስከረም እና ሰኔ/2014 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው የተመረቃችሁ እስከ አርብ
ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-
• ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ
• ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
• የድጋፍ ደብዳቤ
• በተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት
የማመልከቻ ቦታ፡- በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
ለፈተና ያለፉ አመልካቾች በውስጥ ማስታወቂያ ከጳጌሜን 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም ይገለጻል።
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 05/2015 ዓ.ም።
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡- በዩኒቨርሲቲው አምስት ካምፓሶች/ኮሌጆች
Share&forward
Join
@merejamnch
@merejamnch
cross promotion መስራት የምትፈልጉ
Contact with me
@Gashtiman25
782 views06:05