Get Mystery Box with random crypto!

†​​ በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው † † † † † † | ዲያቆን ዳንኤል ወንድሙ ቻ

†​​ በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው
† † † † † † † † †
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

† #ኪርያላይሶን፦
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

† #ናይናን፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

† #እብኖዲ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

† #ታኦስ፦
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

† #ማስያስ፦
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

† #ትስቡጣ፦
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

† #አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

† #አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

† #አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

"ጸልዩ ከመ እግዚእ አምላክነ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ወይትወከፍ ስእለተነ ወያፈጽመነ ዛተ ሰሙነ በደኅና ወበሰላም ወያርእየነ ብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሐሴት ወይስረይ ለነ ኃጣዉኢነ

[ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር ይለን ዘንድ ልመናችንንም ተቀብሎ ይችን ሳምንት በደኅናና በሰላም ያስፈጽመን ዘንድ የትንሣኤውንም ብርሃን በፍጹም ደስታ ያሳየን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ ጸልዩ]"

✞ በእንተ ጽንዐ ዛቲ(ግብረ ሕማማት ገፅ ፻፳፪)
-----------------------------------
ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን
ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን
ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን
ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን
ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን
ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን
ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን
[በቀኝና በግራ በመቀባበል በል፡፡]

"እንበለ ደዌ ወሕማም፣
እንበለ ጻማ ወድካም፣
አመ ከመ ዮም
ያብጽሐነ ፤ ያብጻሕክሙ፣
እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም፡፡"አሜን