Get Mystery Box with random crypto!

የማመስገን ጊዜ ይህ የተመረጠ የዕጣን ጊዜም ይህ ነው ሰው ወዳጅ መድሐኒታችን ክርስቶስን ማመስገኛ | ዲያቆን ዳንኤል ወንድሙ ቻ

የማመስገን ጊዜ ይህ የተመረጠ የዕጣን ጊዜም
ይህ ነው ሰው ወዳጅ መድሐኒታችን ክርስቶስን
ማመስገኛ ጊዜ
፠ ፦ ማርያም ዕጣን ናት ዕጣን እርሱ ነው
በማህፀንዋ ያደረው ከተመረጠ ዕጣን ሁሉ
የሚሸት ነውና የወለደችው መጥቶ አዳነን
፠ ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ መዓዛ ያለው ሽቱ ነው ኑ
እንስገድለት ትዛዞቹንም እንጠብቅ ኃጢአታችንን
ያስተሰርይልን ዘንድ
፠ ፦ ለሚካኤል ምሕረት ተሰጠው ለገብርኤል
ማብሰር ለድንግል ማርያም ሰማያዊ ሀብት
፠ ፦ ለዳዊት ልቡና ለሰሎሞንም ጥበብ
ለሳሙኤልም ነገሥታቱን የቀባ እርሱ ነውና የሽቱ
ቀንድ ተሰጠው
፠ ፦ ለአባታችን ለጴጥሮስ መክፈቻ ለዮሐንስም
ድንግልና ለአባታችን ለጳውሎስም
የቤተክርስቲያን ብርሃኗ እርሱ ነውና መልክት
ተሰጠው
፠ ፦ መዓዛ ያላት ሽቱ ማርያም ናት በማኅፀኗ
ያለው ከዕጣን ሁሉ የሚበልጥ ነው መጥቶ
ከእርሷ ሰው ሆነ
፠ ፦ ንጽሕት ድንግል ማርያምን አብ ወደዳት
ለተወደደ ልጁም ማደሪያ ልትሆን አስጌጻት
፠ ፦ ለሙሴ ህግ ለአሮን ክህነት ተሰጠው
ለካህኑ ለዘካርያስ የተመረጠ ዕጣን ተሰጠው
፠ ፦ የምስክር ድንኯን አደረጎት ጌታ እንደተናገረ
ካህኑ አሮንም በመካከልዋ የተመረጠ ዕጣን
ያሳርጋል
፠ ፦ ሱራፌል ይሰግዱለታል ኪሩቤልም
ያመሰግኑታል
፠ ፦ እግዚአብሔር በአእላፍ መላእክት ዘንድ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ ይጮሃሉ
በአለቆች ዘንድ ክቡር ነው
፠ ፦ መድሐኒታችን ሆይ ዕጣን አንተ ነህ
መጥተህ አድነኸናልና ይቅር በለን