Get Mystery Box with random crypto!

MEGA Et 💬

የቴሌግራም ቻናል አርማ mega_trainingroom — MEGA Et 💬 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mega_trainingroom — MEGA Et 💬
የሰርጥ አድራሻ: @mega_trainingroom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 321
የሰርጥ መግለጫ

Contact:- 251926016275

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-13 11:53:39
18ዓመት የሞላት ልጇን የቤት ክራይ እየከፈለች እንድትኖር ያስገደደችዉ እናት!:

በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አንዲት እናት 18ዓመት የሞላትን ልጇን ቤት ዉስጥ አብራ ለመኖር በየወሩ 100ዶላር ክራይ እንድትከፍል በማድረግ ይህንንም በግልጽ ፊርማ የሚጸና የዉል ስምምነት መፈጸሟ ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል።

"The Independet" የተባለዉ የብሪታኒያዉ የዜና ምንጭ እንደዘገበዉ እናት ከልጇ ጋር የተፈራረመችዉን ዉል በቪዲዮ ከቀረጸች በኋላ "18ዓመት ዓመት የሞላት ልጅ በቤት ዉስጥ ለመቆየት ስትወስን" የሚል ርዕስ በመስጠት በማሕበራዊ መገናኛ ላይ አጋርታለች። ወደ ኋላም "ይህ ሁነት የማስተማርና ልጇን ለስኬት የማዘጋጀት አንዱ አካል ነዉ" በማለት ለማብራራት ሞክራለች።

ይህ ዉል ለአንድ ዓመት የሚጸና ሲሆን ልጅ የስምምነት ጊዜዉ እስኪጠናቀቅ በየወሩ የ100ዶላር ክራይ እንድትከፍል ያስገድዳል። የተጠቀሰዉን ወርሀዊ ኪራይ ወር በገባ 10ቀን ዉስጥ መክፈል ያለባት ሲሆን ከዚያ በላይ ካለፈ እንደዘገየ ተቆጥሮ ቅጣት የሚከተል ይሆናል።
ምንጭ #አልጀዚራ_ሙባሸር
Hamudi Hamudi
161 viewsFuad muhidin, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:07:41
ለአንተ ችግሮች ሌሎች መፍትሄ አያበጁም፤ብቻህን ችግርህን መፍታት ተለማመድ። በራስህ መንገድ የፈታሃቸው ችግሮች ዘላቂ የመሆን እድላቸው ሰዎች ከፈቱልህ በብዙ ይልቃሉ።ምክንያቱም ሰዎች የገጠመህን መሰናክል ያሻግሩሃል እንጂ ነገን አይዘውሩም።

Diya Nesre

join My Telegram channel
https://t.me/+UU4iOWnCOsEhe5Jo
134 viewsFuad muhidin, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 11:09:10
የነገዋን ኢትዮጵያ .....
የነገ ኢትዮጵያን መመልከት የፈለገ የዛሬ ልጆችና ታዳጊዎችን ይመልከት። ነገ የምንመኛትን ኢትዮጵያን ለማየት የዛሬ ታዳጊዎች ላይ እንስራ። ያልዘራነውን አናጭድም። ጥሩነትን ካላሳየነው ትውልድ መልካም ፍሬ አንጠብቅ። ትጉህ፣ በራሱ የሚቆም፣ ኃላፊነቱን የሚወጣ ፣ ለሌሎች አሳቢ እና ተነሳሽ አድርገን ያላሳደግነው ትውልድ በተዓምር ካልሆነ በስተቀር ምርጥ ዜጋ አንጠብቅ።
ወቅቱ ተማሪዎች የቀለም ትምህርት አጠናቀው ለእረፍት ወደ ቤት የተመለሱበት ወቅት ነው። አሁን ደግሞ ዘና እያሉ ስብዕናቸውን የሚገነቡበት ፤ ለወደፊት ህይወታቸው ክህሎት የሚያዳብሩበት ነው።
ለዚህ ደግሞ ጋላክሲ ዊዝደም ሁነኛ ቦታ ነው። ይምጡ፤ ልጅዎን ይላኩ፤ ልጅዎ እጅጉን በብዙ አትርፎ ይመለሳል።
ምዝገባ እያካሄድን ነው።
122 viewsFuad muhidin, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 21:31:00
ክረምቱን የልጅዎ ስብዕና ላይ በመስራት የነገ ማንነቱን ይገንቡ፡፡
ለልጅዎ የሚያወርሱት ትልቁ ነገር መልካም ማንነት የገነባ ፣በራሱ የሚተማመን እና ራዕይ ያለው ሰው ማድረግ ነው በለን እናምናለን፡፡
ልጆቻችን ትልቅ ስጦታችን ናቸው፡፡ ለትልቅ ስጦታ ደግሞ እንክብካቤ ያሻዋል፡፡
በበጋው ወቅት በቀለም ትምህርት የተገነባው አዕምሯቸው በክረምቱ ደግሞ በመልካም ስብዕና እና በህይወት ክህሎት ስልጠናዎች ይገንቡ፡፡

ራስን ማወቅ
በራስ መተማመን የራዕይ መኖር
መልካም ልምድ መገንባት
የአቻ ተጽዕኖን መቋቋም
የንግግር ክህሎት
የመሪነት ክህሎት
ስነምግባር እና ሌሎችም

እነዚህን እና ሌሎችም ርዕሶችን ባካተተ መልኩ ፣ ታዋቂ ሰዎች የሚጋበዙበት እና አዝናኝ ትምህርታዊ ጉዞ የተካተተበት ልዩ የክረምት ስልጠና ልጅዎእኛ ጋር ቢያሳልፍ በውጤቱ ይረካሉ፡፡
174 viewsFuad muhidin, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 07:52:49
"ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡"

ለተለያዩ የፅሑፍ፣ ድምፅና የምስል መልዕክት ከስር ያኖርኩትን የቴለግራም ቻናል ይቀላሸሉ
t.me/+UU4iOWnCOsEhe5Jo
141 viewsFuad muhidin, 04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 21:18:22
''አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡''

#ኢማም አሊ ኢብን ጣሊብ

#ኢማም #motivation #inspiration #Quran #Hadith #viral #viralvideo #duet #Tiktok #tiktokviral #ethiotiktok

የተሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ t.me/friendsmessage
140 viewsFuad muhidin, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 14:42:47
ዘመን ዛሬ ከ9:00_ 11:00 በ አዋሽ FM 90.7

፨ በዘመን የ ትኩረት መሰናዶ የኔ -ነገን ተስፋ ስለማድረግ እናወራለን።

፨ በ ስፓርት ሰዓታችን አጫጭር ወሬዎችን እና የዝውውር መረጃዎችን እናጋራቹሀለን።

፨ እንዲሁም ከተለያዩ የመረጃ ምንጭ ያገኘናቸውን ትኩስ ወሬዎች እና የመዝናኛ መረጃዎችን ይዘናል ።

ምርጫችሁ አዋሽ 90.7 FM ይሁን።

Telegram:-t.me/zemenradio
133 viewsFuad muhidin, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 09:16:38 14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
#ቲም_ኖትኪ

15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
#ሱዚ_ካስም

16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
#ብሩስ_ሊ

17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
#ካረን_ላንብ

18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
#ስቴፈን_ማክክሬን

19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
#ሮቢን_ሻርማ

21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
#ኤሪክ_ቶማስ

22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል ፡፡
#የማዎሪ_አባባል

23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
#ስኮት_ቤልስካይ

24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል ፡፡
#ያልታወቀ_ሰው

25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡
129 viewsFuad muhidin, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 09:16:32
#25_ሕይወት_ቀያሪ_አባባሎች

1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
#ፍራንክ_ኦሽን

2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
#ቶማስ_ጄፈርሰን

3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡
#ዶናልድ

4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
#ኢማም_አሊ

5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
#ዋልተር_ባግሆት

6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡
#ጂም_ዋትኪንስ

7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
#አርል_ኒተንጋል

8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
#አዚም_ፕሪሚጂ

9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
#ዚግ_ዚግላር

10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
#አልበርት_አንስታይን

11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
#ካርል_ጉስታቭ

12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
#ሪያኖር_ሮዝቪልት

13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
#ኮንፊሺየስ
116 viewsFuad muhidin, 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ