Get Mystery Box with random crypto!

18ዓመት የሞላት ልጇን የቤት ክራይ እየከፈለች እንድትኖር ያስገደደችዉ እናት!: በዩናይትድ ስቴ | MEGA Et 💬

18ዓመት የሞላት ልጇን የቤት ክራይ እየከፈለች እንድትኖር ያስገደደችዉ እናት!:

በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አንዲት እናት 18ዓመት የሞላትን ልጇን ቤት ዉስጥ አብራ ለመኖር በየወሩ 100ዶላር ክራይ እንድትከፍል በማድረግ ይህንንም በግልጽ ፊርማ የሚጸና የዉል ስምምነት መፈጸሟ ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል።

"The Independet" የተባለዉ የብሪታኒያዉ የዜና ምንጭ እንደዘገበዉ እናት ከልጇ ጋር የተፈራረመችዉን ዉል በቪዲዮ ከቀረጸች በኋላ "18ዓመት ዓመት የሞላት ልጅ በቤት ዉስጥ ለመቆየት ስትወስን" የሚል ርዕስ በመስጠት በማሕበራዊ መገናኛ ላይ አጋርታለች። ወደ ኋላም "ይህ ሁነት የማስተማርና ልጇን ለስኬት የማዘጋጀት አንዱ አካል ነዉ" በማለት ለማብራራት ሞክራለች።

ይህ ዉል ለአንድ ዓመት የሚጸና ሲሆን ልጅ የስምምነት ጊዜዉ እስኪጠናቀቅ በየወሩ የ100ዶላር ክራይ እንድትከፍል ያስገድዳል። የተጠቀሰዉን ወርሀዊ ኪራይ ወር በገባ 10ቀን ዉስጥ መክፈል ያለባት ሲሆን ከዚያ በላይ ካለፈ እንደዘገየ ተቆጥሮ ቅጣት የሚከተል ይሆናል።
ምንጭ #አልጀዚራ_ሙባሸር
Hamudi Hamudi