Get Mystery Box with random crypto!

መፍትሄ የሌለው ችግር የለም ሁለት ጓደኛሞች ቀለል ባለ የቁምጣና የቲሸርት አለባበስ ሆነው በአን | MEGA Et 💬

መፍትሄ የሌለው ችግር የለም

ሁለት ጓደኛሞች ቀለል ባለ የቁምጣና የቲሸርት አለባበስ ሆነው በአንድ ጫካ ውስጥ ዘና እያሉና እየተጫወቱ ይሄዳሉ፡፡ በድንገት አንዱ ጠያቂ ሌላኛው መላሽ የሆኑበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡

ጠያቂ፡- “አሁን አንበሳ ቢመጣብህ ምን ታደርጋለህ?”

መላሽ፡- “ሽጉጤን አውጥቼ ግንባሩን ነዋ የምለው”፡፡

ጠያቂ፡- “እንዴ! ሽጉጡን ደሞ ከየት አመጣኸው?”

መላሽ፡- “አንተስ አንበሳውን ከየት አመጣኸው?”
የዚህ በልጅነታችን እንሰማቸው የነበሩትን ታሪኮች የሚመሰለው ታሪክ አስተማሪ ነጥብ፡- ለሚመጣው ለማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው!
አንዳንድ ሰዎች አመለካከታቸው ሁሉ አሁን “አንበሳ ቢመጣብኝስ” የሚል ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሁል ጊዜ የሚታያቸው የሚመጣው “አንበሳ” ነው፡፡ ስለሆነም ሁል ጊዜ በፍርሃት፣ በስጋትና ገና ለገና አንድ ችግር ይመጣ ይሆናል በሚል ጠርጣራነት ነው የሚኖሩት፡፡
የዚህ ተቃራኒ ሰዎች በማንኛውም ሰዓት ችግር ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ ለሚመጣው ችግር መፍትሄ የማምጣት ብቃትም እንዳላቸው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ገና ለገና ችግር ይመጣል ብለው ከመዝናናት፣ ከመግባባት፣ ከመስራት፣ ከመውጣት፣ አዳዲሲ ነገር ከመጀመር . . . አይመለሱም፡፡
አለማችን በየጊዜው የምትጋፈጠውን እንደወቅቱ ወረርሽ ያሉ ችግርችን እንመልከታቸው፡፡ ሁል ጊዜ ግን መፍትሄ ይገኝላቸዋል፡፡ ይህ አመለካከት ከሚነሳው ችግር ጋር አብሮ የሚነሳ ብርቱነትንና “እችለዋለው” የሚል አቋምን አመልካች ነው፡፡
ገደል ካለ፣ ድልድይ አለ! በሽታ ካለ፣ መድሃኒት አለ! ጠላት ካለ፣ ወዳጅ አለ! መውደቅ ካለ፣ መነሳት አለ! ሁል ጊዜ ራዕይህንና ተልዕኮህ መንገድ ላይ ሊቆም የሚመጣ ችግር ካለ መፍትሄም አለ! ስለዚህ፣ ገና ለገና ችግር ይመጣል ብለህ ከመንገድህ አትገታ!!
@በንጃሚን