Get Mystery Box with random crypto!

የሰዓሊዉ ማስታወሻ! ከስር የምትመለከቱት ስዕል በአርቲስት ‹ፌዶር› የተሳለ ሲሆን አንድ ልጅ ከት | MEGA Et 💬

የሰዓሊዉ ማስታወሻ!

ከስር የምትመለከቱት ስዕል በአርቲስት ‹ፌዶር› የተሳለ ሲሆን አንድ ልጅ ከትምህርት ቤት ወድቆ ሲመለስ እና ቤተሰቡም እሱን ተመልክቶ በወቀሳ፣ በትችት፣ በስድብና በማናናቅ ሲቀበሉት ያሳያል። ከምንም በላይ የታናሽ ወንድሙ ቤተሰቡን ተከትሎ መሳለቅና በጥላቻ ዓይን መመልከት እጅግ ልብ የሚነካ ነዉ..!

በዚህ ምስል ሠዓሊው እንዲህ ሲል ትልቅ መልዕክት አስተላልፏል። "ቢያንስ ውሻዉ ያዘነለትን ያህል እዘኑለት!"
ሲሳካለትም ሆነ ሲወድቅም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሰዉነቱ ብቻ ይወደዋል። ልጆችዎን የሚጠብቁትን ያህል ባይሆንም የሚጠበቅባቸዉን ግብ እንዲያሳኩ ከፈለጉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይደዷቸዉ። ከስኬት ይልቅ በሽንፈታቸዉ ጊዜ የበለጠ support መደረጋቸዉ ለበለጠ ተነሳሽነትና ለተሻለና ዘላቂ ለዉጥ እንደሚያበቃቸዉ አይርሱ!።
وعَنْ أم المؤمنين عَائِشَةَ رضي الله تعالى عنها: أَنَّهَا قَالَتْ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِذَا أَرَادَ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ بِأَهْلِ بَيْتٍ خَيْرًا أَدْخَلَ عَلَيْهِمُ الرِّفْقَ».
እናታችን ዓኢሻ(ረ.ዓ) እንዳወራችዉ: ሰይዳችን ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ተከታዩን ብለዋል..
"አላህ ለአንድ ቤተሰብ መልካምን በሻ ጊዜ መተዛዘንን በመሀላቸዉ ያሰፍናል!" (ኢማም አሕመድ በሙስነዳቸዉ ዘግበዉታል)
Via:- @hamudi_hamudi1988