Get Mystery Box with random crypto!

አምና ራሱን ሊያጠፋ የነበረው አትሌት ዘንድሮ ሜዳሊያ አሸነፈ! በዘንድሮው የአለም አትሌቲክስ ሻን | MEGA Et 💬

አምና ራሱን ሊያጠፋ የነበረው አትሌት ዘንድሮ ሜዳሊያ አሸነፈ!

በዘንድሮው የአለም አትሌቲክስ ሻንፒዮና የ400 ሜትር የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚው የእንግሊዙ ሀድሰን ስሚዝ ነው። ዛሬ ሜዳሊያ ለመቀበል በአለም ህዝብ ፊት የሽልማት ሰገነቱ ላይ ቢቆምም አምና በዲፕረሽን፣ በተስፋ መቁረጥና በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ለብቻው እየተሰቃየ ነበር።

ሀድሰን ከሽልማቱ በኋላ የአእምሮ ህመም ስቃዩን በግልፅ ተናግሯል። "በአእምሮ ህመም ምክኒያት ስሰቃይ ነበር። ሰዎች አያውቁም ግን ራሴን ለማጥፋትም ሞክሬ ነበር።" ብሏል።

ሀድሰን የማይታለፍ የሚመስለውን የሀዘን፣ የለቅሶ ምሽት ሲያልፍ ጠዋት ደስታ ሆኖለታል። ከጨለማ ባሻገር ብርሀን አለ። አንዳንዴ ጨለማው ጥቅጥቅ ያለ ይሆንና ተስፋ ያስቆርጣል። ተስፋ የመቁረጥ ስሜት፣ ሀዘን ወይም ዲፕረሽን ከተሰማችሁ የስነ ልቦና ባለሙያ ወይም የአእምሮ ሀኪም ማማከር ጥሩ ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት)