Get Mystery Box with random crypto!

የላም ወተት ለላም ልጅ! የህፃናት ወተት አይነቶች ጥቅም እና ጉዳት :- ሰ | Medicine Daily

የላም ወተት ለላም ልጅ!

የህፃናት ወተት አይነቶች ጥቅም እና ጉዳት :-


ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን
ዛሬም እንደተለመደው ለህፃናት እድገት ወሳኝ ከሆኑት ምግቦች አንዱ ስለሆነው ወተት መረጃ እንካቹ ብለናል።

ለህፃናት ምግብነት የሚውሉ የወተት አይነቶች፦
1. የእናት ጡት ወተት (Breast milk)
2. የላም ወተት (Cows milk)
3. የዱቄት ወተት (Formula milk)

የእያንዳንዳቸው ጥቅም እና ጉዳት
1. የእናት ጡት ወተት(#BreastMilk)

የእናት ጡት ወተት ተፈጥሯዊ እና በሰው ልጅ አዕምሮ ፈጠራ ሊመርት የማይችል እና መተኪያ የሌለው ተመራጭ የህፃናት ምግብ ነዉ።

ነገር ግን ከቴክኖሎጂ፣የአኗኗር ዘይቤ እና ስራ ጫና ምክንያት በተለይ በታዳጊ ሀገራት ጡት ማጥባት በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ ነዉ።

አንድ ህፃን በተወለደ በ 30-60 ደቂቃ ውስጥ የእናቱንን ጡት መጥባት አለበት

በመቀጠል በየ 2-3 ሰዓቱ ከ20-30 ደቂቃ ጊዜ እና በተጨማሪ ደሞ በፈለጉት ጊዜ መጥባት ይኖርባቸዋል።

የእናት ጡት ወተት ብቻውን እስከ 6 ወር ድረስ በቂ ነው። ወላጆች ከ 6 ወር በታች ለሆኑ ህፃናት ከጡት ወተት እና በሀኪም ከታዘዘ መድኃኒት ውጪ ምንም ነገር ወደ ልጃቸው አፍ መጨመር የለባቸውም(ውሃ፣ ሻይ፣ ቅቤ፣ ስኳር፣ ማር፣ ቡና....)

የእናት ጡት ወተት ለልጅ የሚሰጠው ጥቅም ምንድነው

ያልሞቀና ያልቀዘቀዘ ማብሰል የማያስፈልገውና የተመጣጠነ ምግብ ነው።
የአንጀት እድገትን እና ስራውን ያዳብራል፤ የአንጀት ቁስለትን ይከላከላል።
ተላላፊ በሽታዎችን ይከላከላል። የአንጀት እንፌክሽንን በ64%፣ የጀሮ መመርቀዝን በ 63%፣ የሳንባ ምችና ጉንፋንን በ72% ይቀንሳል።
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ይከላከላል። የስኳ በሽታን በ40%፣ ካንሰርን በ35%፣ አስምን በ 42%፣ አደገኛ ውፍረትን በ 30% ይቀንሳል።
ድንገተኛ የጨቅላ ህፃናት ሞትን በ72% ይቀንሳል።
ተጨማሪ ወጭና የማዘጋጃ ጊዜ አይጠይቅም
የልጆችን አዕምሮ እድገት ይጨምራል
የእናትና ልጅ ቁርኝትን/ትስስርን ይጨምራል
ለእናቶች ከወለዱ በኋላ ያለውን ደም መፍሰስን ይቀንሳል፣ እንዲሁም ለእናት የህሊና እርካታ ይሰጣል
የእናቶችን የአዕምሮ ጤናማ ያደርጋል
እርግዝናን ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ለተወሰነ ጊዜ ይከላከላል ... ወ.ዘ.ተ እና
በእነዝህ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች የእናት ጡት ወተት ለህፃናት 1ኛ ተመራጭ ነው

2. የዱቄት/ጣሳ ወተት(#FormulaMilk)

ዱቄት ወተት መጠቀም በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው።

አሁን ደሞ ዋጋውም አልቀመስ ብሏል

የዱቄት ወተት የእናት ጡጥን ባይተካም ለህፃናት የሚሆን ምግብ ነው። በተለይ በቪታሚን ዲ እና ብረት ማዕድን የበለፀገ ነው።

ስለዝህ 2ኛ ደረጃ ተመራጭ ወተት ነው። ነገር ግን በርካታ ችግሮች አሉት።

የዱቄት/የጣሳ ወተት ጉዳቶች ምን ምን ናቸው

ከንፅህና ጉድለት እና ጡጦ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ ለተቅማጥ፣ ተውከት እና ለጆሮ ኢንፌክሽን ያጋልጣል።

ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ያጋልጣል፤ ለምሳሌ:- ውፍረት፣ ስኳር ፣ግፊት ....
እንደ ተመረተበት ቦታ የተለያየ ይዘት አለው።
ለተጨማሪ ወጪ እና ጊዜ ብክነት ያስከትላል።
የልጅ እና የእናት ትስስርና ፍቅር ይቀንሳል
አንዳንዴ ድርቀት ሊያመጣ ይቺላል

3. የላም ወተት (#CowMilk)

የላም ወተት በትክክል ተመራጭ የሚሆነው እድሜያቸው 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህፃናት ነው።

ወተቱን ከማለብ ጀምሮ አስከ መመገብ እና ማስቀመጥ ድረስ ባለው ሂደት ከፍተኛ ንፅህናና ጥንቃቄ ያስፈልጋል። አለበለዚያ ለተቅማጥ እና ተውከት እና ምግብ መመረዝ ይዳርጋል።

የላም ወተት ከፍየል ወተት የተሻለ የጤና ጥቅም ስላለው ከፍየል ወተት ይልቅ ተመራጭ ነው።

ከ1 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የላም ወተት
የሚከተሉት በርካታ ችግሮች ስላሉት መስጠት አይመከርም።

ጨቅላ ህፃናት የላም ወተትን ሙሉ በሙሉ አንጀታቸው መፍጨት አይችልም
የላም ወተት የደም ማነስ ያስከትላል
የደም ማነስ በማምጣት በአዕምሮ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅኖ ያሳደራል
በስኳር ህመም የመጠቃት እድልን ያሰፋል
ለተቅማጥ እና ተውከት ያጋልጣል
ለአላስፈላጊ ውፍረት ሊዳርጋል ይችላል(ውፍረት ውስጥ ለገባ ህፃን፣ ውፍረት በዘር ካለ ክሬሙ የወጣ ወተት ተመራጭ ነው)
ብዙ ውሀ ከተጨመረበት ለምግብ አጥረት ያጋልጣል።

ይሄን ያህል ችግር ካመጣ እንዴት እንጠቀመው?

1. አስከ 6 ወር ያክል የእናት ጡት ብቻ ማጥባት (ስራ ሲገቡ የጡት ወተት አልበው መሄድ ጥሩ አማራጭ ነው)

2. ይህን ማድረግ ካልቻሉና አቅማቸው ከፈቀደ የዱቄት ወተት (Formula milk) መጠቀም (በንፁህና ማዘጋጀት፣ ማስቀመጥና መመገብ)።

3. የላም ወተት ከተቻለ አስከ 2 አመት ካልተቻለ እስከ 1 አመታቸው ድረስ መሰጠት የለበትም።

4. 6 ወር ሲሞላቸው ከጡት በተጨማሪ ምግብ መጀመር

5. በተቻለ መጠን የእናት ጡት ማጥባትን እስከ 2 ዓመት መቀጠል።

6. ብቸኛው አማራጭ የላም ወተት ከሆነስ(እናቲቱ ከሌለች፣ ማጥባት ካልቻለች፣ ማጥባት ከተከለከለች፣....)?

እድሜያቸው ከ2 ወር በታች ለሆኑ
40 ሚሊ ወተት እና 20 ሚሊ ውሃ አፍልቶና አቀዝቅዞ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ እና እንደፍላጐታቸው መመገብ

እድሜያቸው 2 ወር ለሞላቸው ህፃናት 60 ሚሊ ወተት እና 30 ሚሊ ውሃ አፍልቶና አቀዝቅዞ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ እና እንደፍላጐታቸው መመገብ

እድሚያቸው 3_4 ወር ለሆናቸው ህፃናት 80 ሚሊ ወተት እና 40 ሚሊ ውሃ አፍልቶና አቀዝቅዞ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ እና እንደፍላጐታቸው መመገብ

4-6 ወር ለሆናቸው ህፃናት 100 ሚሊ ወተት እና 50 ሚሊ ውሃ አፍልቶና አቀዝቅዞ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ እና እንደፍላጐታቸው መመገብ

ከ6 ወር በላይ ወተቱን ምንም ውሃ ሳይገባበት አፍልቶና አቀዝቅዞ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ እና እንደፍላጐታቸው መመገብ እና ተጨማሪ ምግብ መጀመር።

ከላይ የተገለፀው የላም ወተት በዉሃ አጠቃቀም የመጨረሻው አማራጭ እንጂ ብዙ ጊዜ ለህፃናት የሚመከር አይደለም

መልካም ጤንነት!!
ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ!!!
ስለሚከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን።
በዶ/ር መሐመድ በሽር (የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)

Via: HakimEthio
@medicinedaily
ይቀላቀሉን

https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ