Get Mystery Box with random crypto!

የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት እንዲቀንስ የሚያደርጉ ምክንያቶች *** ጭንቀት ጭንቀት በሚሰማን | Medicine Daily

የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት እንዲቀንስ የሚያደርጉ ምክንያቶች
***
ጭንቀት
ጭንቀት በሚሰማን ወቅት ሰውነት በተለያየ መልኩ ለችግሩ መልስ ይሰጣል። አድሬናሊን ወይም ኮርቲሶል የሚባሉትን ሆርሞኖች በመልቀቅ ወይም በማምረት፤ ይህ ማለት ጭንቀት በሰውነት የሆርሞን ምርትና ስርጭት ስርአት ላይ ጣላቃ ይገባል ማለት ነው። የእነዚህ ሆርሞኖች መለቀቅ በሌላ መልኩ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎትን ይቀንሳል፡፡

ድባቴ ወይም ድብርት

ድብርት ሲኖር የሰውነታችን ባዮኬሚስትሪ ሊቀይረው ይችላል ይህ ለውጥ በውጤቱ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ፍላጎታችን ይቀንሳል፡፡

በራስ አለመተማመን

በራሳችን መተማመን እና ስለ ራሳችን ሰውነት ቅርጽ/ተክለ ሰውነት ያለን አመለካከት የወረደ ከሆነ ለግብረ ስጋ ግንኙነትን ፍላጎት ማጣት በሰፊው የተጋለጥን ነን።

እኔ ለሰው አላስብም ወይም አልመስጥም ብሎ የሚያስብ ግለሰብ የግብረ ስጋ ግንኙነትን የማድረግ ሀሳቡ/ፍላጎቱ በጣም ትንሽ ነው ይላሉ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች።

አልኮል ወይም አደንዛዥ እጽ መጠቀም

ከመጠን ያለፈ መጠጥ ድካም ያስከትላል የግብረ ስጋ ግንኙነትን ፍላጎታችን ይቀንሳል። ሌላው አደንዛዥ እጽ መጠቀም ይህን ችግር ያስከትላል።

እንቅልፍ ወይም እረፍት ማጣት

ይህ እክል ኮርቲሶል የተባለዉን ሆርሞን መጠን በሰውነታችን ውስጥ ይጨምራል የሆርሞኑ መጠነ መጨመር የግብረ ስጋ ግንኙነትን ፍላጎታችን ይቀንሳል።

መድሃኒቶች

ለተለያዩ የጤና እክሎች ለደም ግፊት፣ ለስነ ልቦና ችግር እና ለታይሮይድ ሆርሞን መዛባት የሚታዘዙ መድሐኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት የግንኙነት ፍላጎት መቀነስ ሊያስከትላሉ ይችላሉ።

ስንፈተ ወሲብ

አንድ ሰው ከዚህ ቀደም ስንፈተ ወሲብ በግንኙነት ወቅት ገጥሞት ከሆነ ድጋሚ ይመለሳል የሚለው ስጋት ውስጡ ስለሚኖር የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎቱ ይቀንሳል ወይም ግንኙነት ማድረግ ይፈራል።

የሆርሞን ችግር

የወንዶች የወሲብ ፍላጎት በቀጥተኛ ከቴስትሮን ሆርሞን ጋር ይያያዛል። ይህ ማለት የቴስቴስትሮን መጠን በሰውነታችን ውስጥ መቀነስ ይህን እክል ያስከትላል። የቴስቴስትሮን መጠን በተለያየ መንገድ ሊቀንስ ይችላል።

ማረጥ ወይም የወር አበባ መቋረጥ

ሴቶች የወር አበባ ማየት በሚያቆሙበት ወቅት የ ግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎታቸው ይቀንሳል። ይህም የሚከሰተው በዚ ወቅት በድንገት የኢስትሮጅን ሆርሞን ከመቀነሱ ጋር ተያይዞ ነው።

የኢስትሮጅን ሆርሞን በሚቀንስበት ጊዜ የብልት መድረቅ ያጋጥማል በዚህም ምክንያት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም ያስከትላል። ሴቶችም ህመሙን በመፍራት ለግብረ ስጋ ግንኙነት ያላቸው ፍላጎት ይቀንሳል።

የተለያዩ የጤና እክሎች

እንደ ካንሰር፣ የኩላሊት በሽታ እና የስኳር በሽታ ሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን በመቀነስ የግንኙነት ፍላጎትን ይቀንሳሉ።

በጥንዶች መካከል የሚፈጠር አለመጣጣም ወይም ቅራኔ።

መልካም ጤንነት!!
ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ!!!
ስለሚከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን።
_____
ተጨማሪ ወቅታዊና የተሟላ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ/Facebook፡- fb.com/medicinedailynet/
ቴሌግራም/Telegram: https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ