Get Mystery Box with random crypto!

በውስጥ መስመር የተላከ ስሜ #M ነኝ የ27 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ በጣም ቆንጆ እንደሆንኩ ሰው ሁሉ | ማርሲ ኢንተርናሽናል የፍቅር ትዳር ኤጀንት

በውስጥ መስመር የተላከ

ስሜ #M ነኝ የ27 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ በጣም ቆንጆ እንደሆንኩ ሰው ሁሉ ይመሰክርልኛል፡፡ ለመጨረሻ
ጊዜ ፍቅረኛ የነበረኝ የዛሬ አራት ዓመት ነው፡፡ ያኔም ግን ግንኙነታችን ስድስት ወር
አልቆየም ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ፍቅረኛ መያዝ ብፈልግም ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ቁንጅናዬ
እያስደነገጣቸው ይመስለኛል ብዙዎች ደፍረው ለፍቅር አይጠይቁኝም፡፡ ፍቅረኛ
እንዳለኝም የሚገምቱ ብዙ ናቸው፡፡ ባህሪዬ በጣም ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ግን ፍቅረኛ
ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ቤተሰቦቼ እያማረጥኩ እንደሆነ ያስባሉ፤ ግን ደፍሮ ለፍቅር
የተጠጋኝ ሰው እንደሌለ አያውቁም፡፡ ሌሎች ጓደኞቼ ሁሉ ትዳር እየያዙ እኔ ግን እንዲህ
መዘግየቴ ያሳስበኛል፡፡ ብዙ ወንዶች በጣም ቆንጆ ሴት መቅረብ የሚያስፈራቸው
ለምንድነው? ውበቴ ጠላት እንደሆነብኝ እየተሰማኝ መጥቷል፡፡ ምን ላድርግ?

@MarsyeBot
@MarsyeBot