2022-06-13 19:42:38
#የተጻፈበት_ጊዜ
የሐዋርያት ሥራ የተጻፈበት ጊዜ በመጽሐፉ ውሰጥ ባይጠቀስም ፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከተጠቀሱት የታሪክ ክንዋኔዎች በመነሳት አማካይ የሆነ ጊዜ ሊሰጠው ይችላል።
ጊዜውን በተመለከተ ሦስት አቋሞች አሉ።
(1) ከ70 ዓ.ም በፊት
(2) ከ70—100 ዓ.ም እና
(3) በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ
በሁለተኛው ምዕተ-ዓመት ተጽፏል የሚለው ሃሳብ ቀደም ሲል የነበረ ቢሆንም ዛሬ ማንም እንደሱ የሚከራከር የለም። በመለስተኛ ወግ አጥባቂዎች ዘንድ የሚታመነው ደግሞ ከ75 ዓ.ም በኋላ የሚለው ነው ፡፡
ቢሆንም ግን ከ70 ዓ.ም በፊት የሚለው ከመጽሐፉ ከሚገኙ ማስረጃዎች አንጻር የተሻለ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡
ለዚህም ድምዳሜ እንደምክንያት የሚቀርቡት... የመጽሐፋን ድንገተኛ አጨራረስ፣ ጸሐፊው (ሉቃስ) ለሮማ መንግሥት የሚያሳየው ገለልተኛ አቀራረብ፣ የጳውሎስ ደብዳቤዎች፣ የአይሁድ ጦርነት እና ተያያዥ ክስተቶች አለመጠቀሳቸው ይገኙበታል ።
በሐዋርያት ሥራ ላይ የተፈጸሙ ክንዋኔዎች የተጠናቀቁት ወደ 60 ዓ.ም ገደማ ይመስላል። ሉቃስ ሐዋርያው ጳውሎስ በ59 - 60 ዓ.ም ገደማ ወደ ሮም ሲሄድ አብሮት ነበር (ሐዋ 13፥20)። በመጽሐፉ ውስጥ በተጠቀሱና ባልተጠቀሱ ክንዋኔዎች ላይ በመመርኮዝ መጽሐፉ የተጻፈበት ዘመን ከ70 ዓ.ም በፊት ባለው ጊዜ ያደርጉታል።
#ተደራሲያን
ቴዎፍሎስ የመጽሐፉ ዋና ተደራሲ ነው። እርሱ የሉቃስ የሥነ ጽሑፍ ረዳት ነበር። በወቅቱ የሕትመት ዋጋን ከመክፈል ባለፈ በመጽሐፉ ሕትመት ወቅት ሉቃስን ቤት ሰጥቶት ቅጂው እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲሠራ ያደርገ ነበር ፡፡
ሉቃስ ከቴዎፍሎስ ባሻገር ዒላማ የተደረጉ ታዳሚዎች ሳይኖሩት አይቀርም ፡፡ የታሰቡትን አንባቢዎች ማንነት ለመወሰን ፣ ሉቃስ ተደራሲዎቹ እንዲያውቁት የጠበቀውን ወይም ያልጠበቀውን ዓይነት መረጃ መመልከቱ አስተማሪ ነው፡፡
በዚህም መሰረት የሐዋርያት ሥራ የግሪኩን ብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ጠንቅቀው ለሚያውቁና የአረማይክ ቋንቋ ለማይችሉ የታሰበ መጽሐፍ ይመስላል፡፡ ይህ አሕዛብ ክርስቲያኖችን ያካትታል፣ ከፍልስጤም ውጭ የሚኖሩ ዲያስፖራ አይሁዶችንም አያገልልም።
በአጠቃላይ፣ ክርስትና ከአይሁድ ኑፋቄነት ወደ ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ መስፋፋቱን የሚያመለክተው የመጽሐፉ የሙግት ስሜት የተወሰኑ ተደራሲዎችን ሊያመለክት ይችላል። ማለትም ፣ በኢየሩሳሌም ትሑት ጅምር እስከ ሮም ግዛቶች የክርስትና እንቅስቃሴ አስገራሚ መስፋፋትን ለማጥናት ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው ተደራሲ ነው ፡፡
#የመጽሐፉ_ዓላማ
የሐዋርያት ሥራን ዓላማ ስንመረምር ሥራው የሉቃስ ወንጌል ቀጣይ መሆኑን መዘንጋት የለበትም ፡፡ የሐዋርያት ሥራ ዓላማ ከሉቃስ ወንጌል ዓላማ ጋር ተመሳሳይ ነው ለማለት ሳይሆን የቀደመው ከሁለተኛው ጋር በአግባቡ መያያዝ አለበት ለማለት (ሐ.ሥራ 1፥1 ይመልከቱ) ፡፡ የሉቃስ መቅድም በሐዋርያት ሥራ ላይም የሚውል ከሆነ - ሉቃስ ስለ ክርስትና በቅደም ተከተል የተደራጀ ሙግት ለመጻፍ እና ለእምነቱ ማረጋገጫ ለመስጠት ወይም አቃቤነት ለመቆም የተነሳ ይመስላል ፡፡
የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በአይሁድ መሲሕን ባለመቀበል ምክንያት መሠረት አድርጎ አሕዛብ እንደሚካተቱ ለማሳየት፣ በተከታታይ ለመሞገትና ለመጠየቅ ጳውሎስ ከኢየሩሳሌም እና ከፍልስጤም እንደወጣ ያሳያል።
ስለዚህ የመጽሐፉ ሥነ-ጽሑፋዊ አወቃቀር እግዚአብሔር ወንጌልን ለአሕዛብ (አማኝ አይሁዶችንም ጨምሮ) ለማዳረስ ያለውን እቅድ የሚያስረዳ ታሪካዊ ሙግት ያሳያል፡፡ የሉቃስ ዓላማ ክርስቲያን አንባቢዎቹን ለማነጽ እና የማያምኑትን ወንጌልን እንዲሰብኩ ለመርዳት የታሰበ ትክክለኛ የታሪክ ትረካ ለመጻፍ ነው ፡፡
225 views16:42