Get Mystery Box with random crypto!

i ሰው: አንድ ጥያቄ አለኝ እውነት በዚህ ዘመን እውነተኛ ፍቅር ነው ወይስ ስሜት ነው ያለው? እስ | የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹

i ሰው:
አንድ ጥያቄ አለኝ እውነት በዚህ ዘመን እውነተኛ ፍቅር ነው ወይስ ስሜት ነው ያለው? እስኪ የምታውቁ ዘርዘር አድርጋቹ ንገሩኝ

Mekbib:
ፍቅርና ስሜት

በራሴ መነጽር - በራሴ እይታ - ያልከውን ቃኝቼ፣
የተረዳሁትን - ለመግለጽ ፈለኩኝ - ሀሳቤን አውጥቼ።
ስሜት ወጥ ቃል ነው - ብዙ ነገር ይዞ፣
ወዲያው ሚወለድ ነው - በፍጥነት ተረግዞ።
ስሜታዊ ሆነህ - ቁጣ ይይዝሃል፣
አንዳንዴ አጫፋሪ - አርጎ ያፈዝሃል።
ተኖ እንደሚጠፋ - እንደ ጠዋት ጤዛ፣
ዕድሜ አይኖረውም - የውበቱ ለዛ።
በስሜት ሚመራ - ቅርቡን ብቻ አይቶ፣
ነገን አይጠብቅም - በዕርጋታ ቆይቶ።
ስሜት አሁን በዝቷል - ሁሉም ሰው በሩጫው፣
ትዕግስትን አያውቅም - ሲገጥመው ፍጥጫው።
ወደድኩሽ ያላትን - ፍቅር አስመስሎ፣
ሙቀቷን የሚመኝ - በስሜት ቸኩሎ።
ለስሜት ተገዝቶ - በስሜት ሰው አርዶ፣
በነጋታው ሚሸሽ - የሚያሰማ መርዶ።
ሞልቷል በየቤቱ - ስሜት የሚገዛው፣
ግራ የገባው ሰው - በጣም ነው የበዛው።
ስሜት የበዛበት - ዓለምን ሳትፈራ፣
በፍቅር ብርሃን - ሕይወትህን አብራ።
ከጥቂቶቹ ጋር - አብረህ ተቀላቅለህ፣
አጣፍጠው ዓለምን - ፍቅርን ጨምረህ።
ፍቅር አይቸኩልም - ነገን ይጠብቃል፣
ከአፉ ሚወጣውን - ሁሉንም ቃል ያውቃል።
ፍቅር በማስመሰል - አይሄድም እርቆ፣
ያቆያል እራሱን - በልብ ውስጥ ጠብቆ።
ሲያዝኑ አብሮ ያዝናል - ደስታንም ተካፍሎ፣
ሳይደክመው ይጓዛል - ፍቅር ተከትሎ።
አግኝቶ ማጣትን - ሳያይ ቀድሞ አውቆት፣
ፍቅር መታመንን - በልቡ ጠብቆት።
ዘላቂ ኃይል ነው - ሁሌ ተቀጣጥሎ፣
በአብሮነት የሚዘልቅ - ማይሸሽ ያጣን ጥሎ።
ፍቅር ይታገሳል - በስሜት ቅስቀሳ፣
ማሳየት አይወድም - የምሬት ወቀሳ።
.......
መቼም ይሄ ዘመን - በጣም ሰለጠነ፣
በብዕር ቀረና - ጽሑፍ በስልክ ሆነ።
እንዲህ ሁሉም ነገር - ፈጥኖ ስናገኘው፣
ለዛ ይሆን እንዴ - በስሜት ምንዋኘው?
በዚያ በድሮ ጊዜ - በኤሊ ሩጫ፣
ተረጋግተን ኖርን - ስላልነበረ ምርጫ።
ለዛ ይሆን እንዴ - በዚህ ዓለም ፍቅራችን፣
ደብዝዞ ሚታየው - በገዛ ሥራችን?
ያም ሆነ ይሄ ግን - ባለንበት ዓለም፣
መልኩን ያልለወጠ - ምንም ነገር የለም።
ለዚህ ነው በዚህ ዓለም - ፍቅሩ ቀንሶ፣
የሚታየው ጎልቶ - የሰው ስሜት ብሶ።


መክብብ ወልደገብርኤል 
ጥር ፲፱ / ፳፻፲፬
January 27, 2022