Get Mystery Box with random crypto!

ሽልማት ነግሬአችሁ ነበር - የልጅ አስቸጋሪ፣ ካልገጠመው ወላጅ - አራሚ አስተማሪ። የሚፈልገ | የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹

ሽልማት


ነግሬአችሁ ነበር - የልጅ አስቸጋሪ፣

ካልገጠመው ወላጅ - አራሚ አስተማሪ።

የሚፈልገውን - ቶሎ ማግኘት ሲሻ፣

ዕቃ ይሰባብራል - ያደርጋል ረብሻ።

ወላጆችም ፈርተው - እጅን ይሰጡታል፣

ጸባየኛውን ግን - አስረው ይቀጡታል።
.......
ሀገሬም ተሳስታ - አጥፊን ዝም አለችው፣

ክፋቱን ሸልማው - የልብ ልብ ሰጠችው።

ህመሟ ሚሰማው - ፀባየኛ ልጇ፣

በአጥፊው ሲደበደብ - ገላግላ በእጇ።

አቀፈች በዳዩን - ተበዳዩን ትታው፣

ማረም ሲያቅታት - ረብሻውን ፈርታው።


መክብብ ወልደገብርኤል 
January 24, 2022