Get Mystery Box with random crypto!

በከርበላው ሸሂዶች የነብያችንﷺ ውድ የልጅ ልጅ ፣ በፋጢመቱል በቱል ዓለይሃ ሰላም እና ሠይዲና ዓሊ | MAME OFFICIAL

በከርበላው ሸሂዶች የነብያችንﷺ ውድ የልጅ ልጅ ፣ በፋጢመቱል በቱል ዓለይሃ ሰላም እና ሠይዲና ዓሊይ(ረ.ዐ) ልጅ ሠይዲና ሁሰይን እና ቤተሰቦች ሞት ሺአዎች ከልክ በላይ ያዝናሉና እኛ ሙስሊሞች ማዘን የለብንም ለማለት የሚዳዱ ሰዎች አሉ::

ይህ ማለት እኮ ነብዩሏህ ኢሳን ዓለይሂ ሰላም ከፊሎች ጌታ አድርገው ይገዙዋቸዋል ከፊሎቹ የጌታ ልጅ ናቸው ስለሚሉ እኛ ሙስሊሞች ልንወዳቸው አይገባም እንደማለት ነው::

ሱፍይ ይሁን ፣ ሱኒይ ፣ ሺአ ይሁን ፣ ወሃብይ ማንኛውም ሙስሊም ነኝ የሚል ሰው ሁሉ በሐቢቢﷺ ውድ ልጅ ሠይዲና ሁሰይን ዓለይሂ ሰላም ሞ"ት ካላዘነ ፣ ከርበላ ሲባል ልቡ ካልተሰበረ ፣ አይኑ እምባ ካላቀረረ ፣ እምባ ካላፈሰሰ እራሱን ይመርምር።

ያኔ በአሕለል በይቱና በዲነል ኢስላም ላይ ፈተና ሲያደርሱ የነበሩት ሰዎች ቢጤያቸው አሁንም ድረስ አሉ:: ትክክልኛውን የአህለል ሱናህ መስመር አስቀጣዮቹን ፣ አሕለል በይቶችን እና ወዳጆቻቸውን በጭፍን ይጠላሉ:: ክብራቸውን ያጎድፋሉ:: መሻኢኾቹ ግን ያኔ ሠይዲና ሁሰይን ዓለይሂ ሰላም በሀቅ ላይ ፀንተው እንድሞቱት ቢሞቱም ከሀቅ ፍንክች አይሉም::

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመርን ባለስልጣኖቹ ደውለው ሲያስፈራሩዋችው "እኔ እኮ ዑመር ነኝ አንተ አታዘኝም" እንዳሉት ነው:: ከጌታቸው ውጪ ለማንም አያጎብድዱም:: እስልምና ከፍ የሚለው በጀግኖች ነው ብለዋል የሱመያው መስጂድ ኢማም ሸይኽ ሰዒድ ረሂመሁሏህ:: እመነኝ ሀቅ ሁሌም challenge አለው:: ሁሌም ጁህድ ይፈልጋል:: at the end of the day ግን ሁሌም አሸናፊ ነውና ጀገን በል የሸኾቹ ወዳጅ::