Get Mystery Box with random crypto!

ጥሩ ስራ የሚሰራ ሰው ሲታይ ከአንተ ጋር ነኝ ሲባል ጥሩ ነው አሉ ሠይዲ ወመውላየ ሸምሰዲነል አብሬ | MAME OFFICIAL

ጥሩ ስራ የሚሰራ ሰው ሲታይ ከአንተ ጋር ነኝ ሲባል ጥሩ ነው አሉ ሠይዲ ወመውላየ ሸምሰዲነል አብሬትይ::

አብዛኛዎቻችን ግን ከዚህ ተቃራኒ ነን:: ጥሩ የሚሰራውን ሰው አደናቅፈን ልንጥለው እንፈልጋለን:: ወይንም ያየነውን ጥሩ ነገር ለራሳችን ልናደርገው እንከጅላለን:: ነብስያችን የተበለጠች ስለሚመስላት ልንደግፈው ፋንታ እንሀስዳዋለን እንመቀኘዋለን:: ሰው የተሻለ ጥሩ ሀሳብ እንኳ ሲያመጣ ሀሳቡ ከእኛ ባለመምጣቱ እንናደዳለን ላለመቀበል ምክንያት እንደረድራለን::

ነብስያ ብዙ አይነት ሸሮች አሏት:: ቆም ብልን ከራሳችን ጋር ካልተሳሰብንና እራሳችንን ካላረምን ነብስያችንን ዝቅ ማድረግ አንችልም:: ነብስያችን ዝቅ ካላለች ሩሓችን ከፍ አትልም::