Get Mystery Box with random crypto!

አሏህ ያሻውን ሰሪ ነው:: ነገራቶችን ለመቀያየር ከፈለገ ሰበብ አስባብም አይፈልግም:: ያለ ግምት | MAME OFFICIAL

አሏህ ያሻውን ሰሪ ነው:: ነገራቶችን ለመቀያየር ከፈለገ ሰበብ አስባብም አይፈልግም:: ያለ ግምት ያሻውን የሚሰራ ጌታ ነው:: የተፈጠረውን ነገር ሁሉ ወደ አሏህ እናስጠጋው:: ብዙም መረበሽ የለብንም ያደረገበትን ምክንያት ጀሊሉ ያውቃል:: እኛ የማናውቀውን ሁሉ አዋቂ ጌታ ነው:: ሲፈልግ በቅፅበት ነገራቶችን መቀያየር የሚችል ጌታ ነው:: ወደ ራሳችን መለስ እያልንም እንይ::

አስሃቡል ካህፍ ወደ ዋሻው በገቡበት ቀን ሃገራቸው ሙሉ ለሙሉ የኩፍ*ር ጨለማ ወርሷት ነበር:: በገሃድ የአሏህን ስም መጥራት ወንጀል ነበር:: እነሱ ለግማሽ ቀን ወይም ለ አንድ ቀን ተኝተው ሲነሱ ሃገሪቱ ሁሉ በኢስላም ኑር አብርታ ጠበቀቻቸው:: በእርግጥ ለሌላው ህዝብ ግማሽ ቀን ሳይሆን 300 አመታት ተቆጥረው ነበር:: አሏህ ጋር ግን ግማሽ ቀኑም 300 አመቱም ያው ነው:: የመሻኢኾቻችንን አደብ ፣ሰብር እና መንገድ ተከትለን ሀቁን ከፍ እናደርገዋለን:: እና አብሽሩ ኑስራው ቅርብ ነው:: በዱዓ በአዝካር እንታገዝ::