ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ዝም ይላል እነ ሸህ ቃሲም ማክሰኞ ጠዋት ተያዙ ረቡዕ ፍርድቤት ቀርበው የ5ሺ ብር ዋስትና ተፈቀደላቸው ፖሊስ መልሶ ይግባኝ ጠየቀ ሃሙስ 9 ሰአት ድጋሚ ፍርድ ቤት ቀረቡ የፖሊስ ይግባኝ ውድቅ ሆነ። የዋስትናው ብር ተከፍሎ የፍርድ ቤት ፕሮሰስ አልቆ ፖሊሱ መፈቻ እንዲፈርም ቢሮው ሲኬድ የለም ተብለው አደሩ፣ ዛሬ ጁመዓ ጠዋት ይፈታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ፖሊስ አሁን ሁለተኛ ዙር ይግባኝ በሰበር ፕሎት ጠየቀ ፍርድ ቤቱ ለሰኞ 4 ሰአት ቀጠሮ ሰጠ። የተፈለገውም ይኸው ነው ያለ ወንጀላቸው የታሰሩ ሸይኾች ፍርድ ቤቱ ቢለቃቸውም ፖሊስ አልፈታም ብሎ ይግባኝ እየደራረበ ያንገላታቸው ይዟል። ሰሚ ተመልካቹ እውነተኛ ፍርድ ሰጪው አላህ ነው። ይህም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍሯል። አላህም ዘንድ ተመዝግቧል። አላህ ይፈርዳል። @IkhlassTube 250 viewsmâmĭłă(ቀምጣላው) , 20:32