Get Mystery Box with random crypto!

Sαlαh Responds

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahircomp123 — Sαlαh Responds S
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahircomp123 — Sαlαh Responds
የሰርጥ አድራሻ: @mahircomp123
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.39K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ሙስሊም ባልሆኑ አካለት እሥልምና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ንፅፅራዊ ምላሾችን የሚሰጥ ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 09:31:39 አንዱን ለያሕዌ አንዱን ለሰይጣን

በኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ 16 ላይ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል አሮን ለእስራኤላውያን ኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ በሁለት ፍየሎች ላይ ጥሎ መስዋዕት እንዲያደርጋቸው ትዕዛዝ ያስተላልፋል።

“አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሔር ሌላውንም ዕጣ ለአዛዝኤል።” (Hebrew Bible)
— ዘሌዋውያን 16፥8

የእብራይስጡን ጨምሮ የዘጠነኛው መክዝ የዐረብኛው ቅጂ በግልጽ "አዛዝኤል (עֲזָאזֵל/عَزَازِيل) በማለት እንቅጩን ያስቀምጣሉ። ከ25 በላይ በሆኑ የአዲስ ኪዳን ምሁራን የተተረጎመው NET'ን ጨምሮ ከ20 በላይ የእንግሊዝኛ ቅጂዎች ቃል-በቃል "Azazel" ብለው ተርጉመውታል። አዛዝኤል በጥንት ዘመን ህዝበ-እስራኤል ፍየል መስዋዕት የሚያደርጉለት የበረሃ አጋንትት መሆኑን እንደ ጳውሎስ ቄረስ የመሳሰሉ ገለልተኛ ምሁራን ይናገራሉ:-

❝...ሆኖም ህዝብ እስራኤላውያን ከግብፁ ቲፎን በተለየ መልኩ ፍየል መስዋዕት የሚያደርጉለት አዛዝኤል የተባለ የበረሃ ሰይጣን ነበራቸው። ይህ እስራኤላውያን ከሁለቱም መሠረታዊ ሥርዓቶች እኩል ተደርገው ከሚታዩበት ምንታዌነት ገና እንደተላቀቁ ይጠቁመናል።
( The history of the Devil and the idea of evil, Pp .65)

አንዳንድ ሚስኪን ክርስቲያኖች ዘሌዋውያን 16:8 ላይ የሚገኘው ንባብ "Scapegoat" ተብሎ መተርጎም አለበት ይላሉ። በዚህም ሆነ በዚያ፣ ተተረጎመም አልተተረጎመም እኮ ይህ "ይለቀቃል" የተባለው ፍየል ለአዛዜል አልቀረበም ማለት አይደለም። ከጥንታዊያን የኦሪት ሊቃውንት መካከል አንዱ የሆነው አይሁዳዊው "ኢሳያስ ሆሮዊዝ" በአንቀጹ ላይ እንዲህ በማለት ጽፏል:-

עזאזל ביום כפור, ובגורלות הושוו עבד לאדונו ויקרא טז, ח גורל אחד לה' וגורל אחד לעזאזל
"...the scapegoat offered by the Jewish people to Azazel on the Day of Atonement Leviticus 16፥10..." / በዘሌዋውያን 16 ላይ እንደተገለጸው የተለቀቀው ፍየል በአይሁዳውያን የስርየቱ ቀን ለአዛዝኤል የቀረበው ነው።
( Shenei Luchot HaBerit, Torah Shebikhtav, Vayishlach, Torah Ohr 39)

እንደምናየው የግድ "የሚለቀቅ" Scapegoat ተብሎ መተርጎም አለበት ብላችሁ መጋጋጥ ከአጣብቂኙ አየወጣችሁም። ይህንን የፈሩት አንዳንድ አይሁዳውያን አዛዜል አንዴ ተራራ ነው፣ አንዴ እራሱ የፍየሉ ስም ነው፣ አንዴ ዳገቱ ነው እያሉ ጨልለዋል። አንዳቸውም ትርጓሜ ግን ለዐውደ-ንባቡ የሚስማማ አይደሉም። ከሁሉም በላይ ደግሞ የጥንታዊንያ አይሁዶች ፍየልን ለሰይጣኑ አዛዝኤል መስዋዕት የማድረግ ልማድ እንደነበራቸው በታሪክ መስፈሩ ደግሞ ነገሩን ወደፈለጉት አንድምታ መጠምዘዙን እጅግ ከባድ ያደርገዋል። ታዋቂው የብሪታኒካ መድብለ-እውቀት የሚከተለውን ጽፏል:-

❝አዛዝኤል በአይሁዳውያን ትውፊት (ጽሑፍ) ውስጥ ጥንት በስርየቱ (ዮሚ ኪፑር) ቀን የአይሁዳውያንን ኃጢአት የተሸከመው ፍየል (Scapegoat) የተላከለት አጋንንት ወይም እርኩስ መንፈስ ነው። ለሥርዓቱ ሁለት አውራ ፍየሎች ተመርጠዋል፤ አንደኛው ለእግዚአብሔር ሌላኛው ደግሞ ለአዛዜል (ዘሌዋውያን 16፥8)። የአምልኮ ሥርዓቱ የተከናወነው በሁለተኛው ቤተመቅደስ ውስጥ በሊቀ ካህኑ መሆኑን በሚሽና ውስጥ ተገልጿል። ሊቀ ካህኑ በምሳሌያዊ ሁኔታ የአይሁድን ሕዝብ ኃጢአት በሙሉ ወደ ፍየል ካስተላለፈ በኋላ ‟ለአዛዝኤል” ተብሎ የተዘጋጀውን ፍየል ወደ ምድረ በዳው ገደል እስኪሞት ድረስ ሸኙት። በአንዳንድ ረባናዊ ጽሑፎች መሰረት አዛዝኤል የተጣለ መልአክ ነው።❞
( Azazel, Jewish legend: Encyclopedia Britannica)

❐ ጫን ያለባቸው ሰባኪዎች ይህንን ለማስተባበል የሚጠቀሙት መንገድ በጣም ያስቃል። እንደው ቢቀርባቸውስ ? የሚያስብል መልስ እየሰጡ ተከታዮቻቸውን ያሸማቅቃሉ። ከዚህ ሁሉ ይህን የተበረዘውን መፅሐፍ ጥላችሁ ወደ መጨረሻው ኪዳን (ቁርኣን) ብትመጡ እኮ የዘለዓለም ሕይወትን ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓለምም ለአፍታ ያላያችሁትን ደስታ ታተርፋላችሁ። ጌታ አምላክ ሒዳያ ይሰጣችሁ ዘንድ እማፀነዋለሁ።

-------------------------------------------
Sαlαh Responds ◂
309 viewsedited  06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:24:38 ይህን እንዴት ሊያውቁት ቻሉ ?

የዘመናችን Anatomisቶች የሰው ልጆችን የመገጣጠሚያ ስርዓት ማወቅ እጅግ ከባድ ጥናት መሆኑን ይናገራሉ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የዘርፉ ምሁራን ሰዎች በውል ስንት መገጣጠሚያ እንዳላቸው ማወቅ አልቻሉም ነበር። ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ግን ዘመን ያፈራቸውን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በሰው ልጆች ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች (Joints) መኖራቸውን አረጋግጠዋል። የሚያስገርመው ይህ አይደለም !

የዛሬ 1400 ዓመታት የነበሩ ታላቁ መልዕክተኛ (ﷺ) ማንበብም ሆነ መጻፍ ሳይችሉ፣ ለአፍታ እንኳ ዓለማዊ ትምህርት ሳይወስዱ፣ የትኛውንም ቴክኖሎጂ ሳይጠቀሙ ዘመናዊያኑ ምሁራን እንኳ ያለ አናቶሚ ጥናት መድረስ ያልቻሉበትንን እውነታ እሳቸው አስቀድመው ለማህበረሰቡ አስተምረዋል። ነቢዩ ሙሐመድ እንዲህ ነበር ያሉት:-

في الإنسانِ سِتُّونَ وثلاثُمِائةِ مِفْصَلٍ
‟የሰው ልጆች ውስጥ ሦስት መቶ ስድሳ መገጣጠሚያዎች «Joints» አሉ።
( ኢማሙ ሙስሊም/ ሶሂህ አል-ጃሚዕ 4239)

ሱብኃን አሏህ ! በእውነቱ ይህ እጅግ የሚያስገርም ነገር ነው። እስኪ ዘመናዊው ሳይንስ የሚለውንም እንመልከት።

⓵ ❝A joint is where two or more bones meet and allow movement. There are 360 joints in the adult human body.❞
( Source:-The joints: chiropractic. By Dr Molly casey)
⓶ ❝The joints connect bone to bone, and there are 360 joints in our bodies
( Source:-Hudson Physicians: Bone and joint)
⓷ ❝There are 360 joints in the human body. Joints are lined with cartilage which cushions and enables the joint to move smoothly and easily.❞
( Source:-The Medical Healthcare : Joint Problems)

❐ ነቢያችን በወቅቱ የትኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሊያውቅም ሆነ ሊደርስበት የማይቻለውን አያሌ እውነታዎች ለማህበረሰቡ ብሎም ለዓለም አስተዋውቀዋል። ያልተማረ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለደ ማንበብም ሆነ መጻፍ የማይችል ነቢይ እነዚህን እውነታዎች እንዴት ሊያውቃቸው ቻለ ? ይህ ከግልጠተ-መለኮት እንጂ በሰው የሚቻል ነውን ? ለእናንተው ልተው።
-------------------------------------------
Sαlαh Responds ◂
777 viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:24:35
578 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:30:47
እዚህ ቤት 4k ተከታዮች እያላችሁ ነው እስካሁን ቲክቶክ 1ሺ ያልገባሁት ? ወይስ በፈሊጣዊ አነጋገር ዝገው እያላችሁኝ ነው ? ለማንኛውም «ይህንን ተጭናችሁ» ሳይሞለ ፎሎው ብታደርጉ አሪፍ ነው ! Let's beat Khaby lame ትላለህ :))
956 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:20:59 የአቡበከር ስድብ ?

ኢስላም ጠል ሚሺነሪዎች የነቢዩ ደቀመዝሙር የሆነው አቡበከር በብልግና ቃል ተሳድቧል ብለው የሚያዘዋውሩት ሪዋያዎች አሉ። እርግጥ ነው ! የተነሳው ሐዲስ ጠለቅ ብሎ ላልመረመረውና ከላዩ ብቻ እንዲሁ በግርድፉ ላነበበው ማንኛውም ክርስቲያን ይቅርና ለሙስሊሙ እንኳ ስድብ ሊመስል የሚችል ማምታቻ ነው። ለማንኛውም ዘርዘር አድርገን እንመልከት:-

በስድስተኛው ሒጅራ ነቢዩ እና ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች ዑምራ ለማድረግ ወደ መካ እያቀኑ በጉዟቸው ላይ ሳሉ እረፍት አድርገው ለመስገድ ቁጭ ባሉበት ዑርዋ ከአንዳንድ ቁረይሾች ጋር ጥቂት ሰራዊት ይዞ መጣባቸው። ነቢዩ ለጦርነት ወደ መካ የሚያቀኑ የመሰለው ዑርዋ ነቢዩንና ሙስሊሞችን ቆሞ ይሳደብ፣ ያንቋሸሽ ነበር። "እኛ ለጦርነት አይደለም የመጣነው" የሚለውን የመልዕክተኛውን ንግግር ለመስማት ፍቃደኛ ያልሆነው መሪያቸው ነቢዩን ከመሳደብ እና ከመዝለፍ ግን መቆጠብ አልቻለም። ይህ ሳያንሰው ደግሞ ❝አንተ ሙሐመድ ሆይ ! አሁን የተከተሉህ ሰዎች እኮ ጠላት ቢመጣብህ ጥለውህ የሚሮጡ ፈሪዎች ናቸው!❞ በማለት እነዚያን ደፋር ደቀመዛሙርት ቆሞ ይሳደባል። የተወዳጁ ነቢይ እና የሙስሊሞች ስም በማንም ጣዖት አምላኪ ሲንቋሸሽ መስማት ያልቻለው:-
فقَالَ لَهُ أَبُو بَكْرٍ امْصُصْ بَظْرَ اللاَّتِ أنحن نفر عنه وندعه؟
‟..አቡበክር የላትን ብልት/ቂንጥር ላስ እኛ ነን እርሱን ትተን የምንሮጠው ?” አለው።
( አል-ቡኻሪ 2731: መፅሐፍ 54 ሐዲስ 19)

1- እንግዲህ የዚያ ጠንካራ ንግግር ዐውዳዊ ምክንያት ይህ ነው። ከሁሉም በፊት ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ እንደው ይህ ቃል ምክንያት አልባ ደረቅ ብልግና ነው ራሱ ቢባል አንድ ስድብን መቋቋም ያልቻለው ሰው ስሜታዊ ሆኖ ተናገረው ከመባል የዘለለ ምንም ጮቤ የሚያስረግጥ ነጥብ አይደለም። አቡበከር እንደማንኛችንም የሰው ልጅ ነው፣ ይሳሳታል። የሆነ ሰው ተሳደበ ወይ ደግሞ ተሳሳተ ተብሎ እስልምና ላይ ሽንጥ ገትሮ ለሙግት መሮጥ አላዋቂነትን ነው የሚያሳየው።

2- ሲቀጥል "የእገሌን ብልት ንከስ/ሳም" ብሎ ማስነወር (አፍ ማስዘጋት) በአረቦች ዘንድ የሚታወቅ "ምሳሌያዊ አነጋገር" Proverb እንጂ እንደዛሬው "ደረቅ ስድብ" አይደለም። ስመጥሩ የቃላት-ሊቅ ኤድዋርድ ዊሊያም ሌን ይህን ንግግር በተመለከተ "A proverb of the arabs" በማለት የተለመደ ምሳሌያዊ ቃል መሆኑን ዘግቧል [Lane's Arabic-English Lexicon, Book 1, p.222]

በድረዲን አል ዐይኒ (d. 855 H) የሚከተለውን ጽፏል:-
وقال ابن التين: هي كلمة تقولها العرب عند الذم والمشاتمة، لكن تقول: بظر أمه، واستعار أبو بكر، رضي الله تعالى عنه، ذلك في اللات لتعظيمهم إياها
‟ኢብኑ ቲን እንደሚለው ይህ አይነቱ አነጋጋር ዓረቦች ሌላውን ለመውቀስ እና ለማንቋሸሽ የሚጠቀሙበት ሐረግ ነው። አቡበከርም እነርሱ ለጣዖቷ አክብሮት ስለነበራቸው ይህን ንግግር ተጠቅሞበታል።” ብሏል።
( አል-ዐይኒ: ኡምደቱል ቃሪዕ ጁዝዕ 14 ገፅ 10)

እንደምንመለከተው እነዚህ መሰል ንግግሮች ጥንት ዓረቦች ሌላውን የሚያንቋሽሹበት የተለመደ አይነት ምሳሌያዊ ንግግር እንጂ ዛሬ ላይ ባለው መልኩ ደረቅ የሆነ የስድብ አይነት አይደለም። አረቦች ይህን ሐረግ መጥፎ የሆነ የትኛውንም ነገር ለመግለጽ የሚጠቀሙበት መሆኑን ተጨማሪ ማስረጃ እንይ፣ ኢብኑ ረሺቅ የሚከተለውን ጽፈዋል:-
إن الشعراء ثلاثة: شاعر، وشويعر، و ماص بظر أمه
‟ገጣሚ ሦስት አይነት ነው። እጅግ ጥሩ የሚባል፣ ሌላው ተራ ገጣሚ እና (የመጨረሻው) ደግሞ የእናቱን ብልት የሚነክስ ነው።”
(ቀይረዋኒ: አል-ዑምደህ ፊል መሓሲን ቅፅ 2 ገፅ 116)

ልብ በል ! ይህ ንግግር:- ሦስተኞቹ ምድብ ገጣሚያን ምንም ዋጋ የሌለውን ሥራ ስለሚሰሩ ጥቅም አልባ ውጤታቸውን የሚገልጽ አስተያየት ነው እንጂ ተራ ስድብ አይደለም። በአጭሩ እነዚህ ገጣሚያን እጅግ መጥፎ ሥራ (ግጥም) ይጽፋሉ እያለ ነው፣ የተጠቀመው ገለጻ ግን "ብልት ይነክሳሉ" ብሎ ነው። ከዚህ የምንረዳው አረቦች ይህን መሰል ሐረግ የማይረባ ለሆነው የትኛውም ነገር እንደሚጠቀሙበት ነው። ይህ ከሆነ አቡበከር ስሜታዊ ሆኖ ይህን አረቦች ጥንት የሚጠቀሙበትን ምሳሌያዊ አነጋገር በመጠቀም የተሳዳቢውን አፍ ቢያሲዝ ምንም የሚያስገርም ነገር የለውም።

-------------------------------------------
Sαlαh Responds ◂
836 views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:26:46
ስታንፎርድ ኢንሳይክሎፒዲያ በሥላሴያዊይን ዶግማ ታሪክ ላይ በጻፈው ሰፊ ጥናታዊ ጽሑፍ የሚከተለውን አስቀምጧል:-

❝..በመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍለዘመናት ውስጥ የትኛውም የሥነ-መለኮት ምሁር (ሊቅ) አንዱ አምላክ እኩል መለኮታዊ ስልጣን ባላቸው ሦስት አካላት (አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ) ውስጥ ይኖራል በሚለው ሒሳብ በማመን ማንም የሥላሴ አማኝ አልነበረም።”
( History of Trinitarian Doctrines: The Stanford Encyclopedia of Philosophy)

እስከ ጥግ ድረስ በነጥቡ ላይ ጥልቅ ጥናት ያካሄዱት ምሁራን እውነታውን ተቀብለዋል። የኃለ ኃለ ሁሉም በአንድ ድምፅ እየተስማሙበት ነው። ሥላሴ በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተፈብርኮ ቀስበቀስ ወደ ቤተክርስቲያን ያደገ ሰው ሰራሽ ትምህርት እንጂ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው አስተምህሮ አይደለም።
-------------------------------------------
Sαlαh Responds ◂
904 viewsedited  19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:16:48 عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنه قَالَ أَمَرَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ بِالصَّبْرِ عِنْدَ الْغَضَبِ وَالْحِلْمِ وَالْعَفْوِ عِنْدَ الْإِسَاءَةِ
ከኢብኑ ዐባስ እንደተላለፈው:-‟አላህ ምዕመናንን በቁጣ ጊዜ ትዕግሥትን፣ በበደል ጊዜ ደግሞ መታረምንና ይቅር ባይነትን እንዲያሳዩ አዟቸዋል።
( ኢብኑ ሐጀር: ፈትሕ አልባሪ ጁዝዕ 8/423)
999 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:28:53 ወንድም አብዱልከሪም አዲስ ቪዲዮ ለቋል ገብታችሁ "Subscribe/Like/Share" በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፋፉ።

▸ ርዕሰ:- ❝የኢየሱስ የማስተዋል ችግር


390 views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:06:06 98▸ ሴት፣ ውሻ እና አህያ ?
99▸ በኃይል ለምን ያዛቸው ?
100▸ ሴቶች በክርስትና መፅሐፍት
101▸ ባርነት በእስልምና ለምን ?
102▸ አልሰቀሉትም አልገደሉትም
103▸ ዕዝራን የአምላክ ልጅ ?
104▸ ዒሣ የኢየሱስ ስም ?
105▸ ቀድማችሁ ሰላም አትበሉአቸው
106▸ ቅድመ ልደተ-ሙሐመድ....
107▸ ስለ ኆኖፌም እንዋቀስ ?
108▸ ሱረቱል ሐፍድ እና ኻል ?
109▸ ጌታችሁን ትገናኛላችሁ
110▸ የመስዋዕቱ ልጅ ማነው ?
111▸ ጅምላ ጨፍጫፊው አምላክ
112▸ ነቢዩ ኢየሱስ አልተሰቀለም
113▸ በአሻንጉሊት መጫወት ?
114▸ አላህ ባወረደው ይፍረዱ ?
115▸ በጆሮው ውሰጥ ይሸናል ?
116▸ የአላህ ቃል ፍጡር ነውን ?
117▸ በስድስት ወይስ በሰባት ቀናት ?
118▸ ዛፎች ከብርሃን በፊት ተፈጠሩ ?
119▸ አንዲትን ሚስት ብቻ አግቡ ?
120▸ አላህ ግራ እጅ የለውም ?
121▸ የይሁዳ አሟሟት ግጭት !
122▸ አደም በአላህ ላይ አላሻረከም።
123▸ አደም በአላህ ላይ አላሻረከም 2
124▸ የዕብራውያን ደብዳቤ ደራሲ !
125▸ ዙልቀርነይን አሌክሳንደር ነውን ?
126▸ በዘመነ ጃሒልያ ለሚኩሯራ ሰው ?
127▸ አላህ እራሱን ከፈረስ ፈጠረ ?
128▸ የክርስትያኖች ግብዝነት ሲጋለጥ
129▸ የዘይድ ቤት ታሪክ ቅጥፈት
130▸ ያልተሳካው ከንቱ ልፋት ቁጥር ²
131▸ የዝሙት ልጅ ማግባት ይቻላል ?
132▸ እውን "ቁሰም" የነቢዩ ስም ነውን ?

Sαlαh responds
548 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:06:05 በዚህ ቻናል የተለቀቁ መጣጥፎች።
1▸ ኢየሱስ አይመለክም !
2▸ ሱረቱል አሕቃፍ 46:9
3▸ የብሉይ ኪዳን መበረዝ
4▸ ያልተሳካው ትችት
5▸ አል-ሐጃጅ እና ቅያሬ ?
6▸ የአላህ ረህመት
7▸ መንፈስ ፈጠረኝ ?
8▸ አል-መሲሕ ዒሣ
9▸ ምድርን ዘረጋት
10▸ አምላክ አይደለም
11▸ ጎልማሶችን ማጥባት
12▸ ሰልመናል በሉ ?
13▸ ቃል እና መንፈስ
14▸ ሥላሴና ምሁራን
15▸ የራዕይ ውግዘት
16▸ የዱንያ ፍቅር
17▸ በራሱ መልክ ፈጠረው
18▸ ውሸት መናገር
19▸ የእርግማን ውጤት ?
20▸ ነገረ-ተሕሪም
21▸ የነቢዩ ንጽሕና !
22▸ አራተኛው አልጋ ?
23▸ የዙልቀርነይን ታሪክ
24▸ የባይብል ብርዘት
25▸ ኢየሱስ ይመጣል ?
26▸ አንድ ማይል መቀመጫ
27▸ ያልተቀነነው መልዕክት
28▸ የቁርኣን አሕሩፍ
29▸ የቁርኣን ቂርኣት
30▸ የከዕብ ግድያ ?
31▸ የስቅላት ውዝግብ
32▸ ማቴዎስ 28/19
33▸ የቁርኣን መጠበቅ
34▸ የታላቁ መመሪያ አጣብቂኝ
35▸ ኢሥቲንካህ ምንድነው ?
36▸ ከአይሁድ የተቀዳ ነው 1
37▸ ከአይሁድ የተቀዳ ነው 2
38▸ ዳግም መገንባት !
39▸ እውነተኛ ነቢይ ናቸው
40▸ የማርቆስ አጨራረስ
41▸ ጳውሎስ በቁርኣን ?
42▸ ቁርኣናዊያንና ክህደታቸው
43▸ አመልኮተ-ማሪያም
44▸ ሰባ ሁለት ደናግላን
45▸ ሥላሴ ባዕድ አምልኮ
46▸ ባይብል እና ታሪካዊ ዳራ
47▸ የገጣሚዋ ግድያ
48▸ ለምን በገነት ፈጠራቸው ?
49▸ አንድያ አምላክ ወይስ ?
50▸ የፈርዖን ወይስ የአርጤክስስ ?
51▸ ቀዳማይ ምንጮቻችን
52▸ የወንጌላት ደራሲያን
53▸ ሥላሴ በባይብል ?
54▸ ኢየሱስ ፍጡር ነው።
55▸ ታሪኽ አል-ጠበሪ
56▸ በተፍሲር ማመን
57▸ ኢብኑ ኢስሓቅ
58▸ የትንሳኤው ሁኔታ
59▸ የጠፋው አንቀጽ ?
60▸ ባይብል እና ታሪካዊ ዳራው 2
61▸ ሱረቱል ኒሳዕ 4/157
62▸ መንፈስ እና ብዥታ
63▸ ኢየሱስ ፍጡር ነው
64▸ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርዘት
65▸ አላህ ለነቢዩ ይሰግዳል ?
66▸ ሰመድ የአላህ ስም
67▸ በመግደል መፅደቅ ?
68▸ አል-ሙፋኸዛህ
69▸ የነቢዩ ታሪካዊነት
70▸ የተወገረች ዝንጀሮ
71▸ ታላቁ የነቢዩ ተዓምር
72▸ ብዙ ግልባጮች ?
73▸ ወንድ ይወልዳልን ?
74▸ የሐፍስ ቂርኣት !
75▸ የኸዲጃ ጋብቻ ?
76▸ የጠፉ የቁርኣን ክፍሎች
77▸ የውግረት አንቀጽ
78▸ የእግዚአብሔር ሴራ
79▸ የግመል ሽንት
80▸ አምስቱ ጥቢዎች
81▸ የባይብል ጭማሪ
82▸ የፎቶዎች ገበያ በገነት
83▸ ድንጋይ ታመልካላችሁ !
84▸ ሚስቶቻችሁን ምቱ ?
85▸ ስቅለት በሐዲስ ላይ ?
86▸ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊ
87▸ ውሻን መግደል ይቻላል
88▸ የአዒሻ እድሜ ክፍል 1
89▸ የአዒሻ እድሜ ክፍል 2
90▸ የአዒሻ እድሜ ክፍል 3
91▸ ያልተከበረው ትዕዛዝ !
92▸ ጥንታዊው ቤተመቅደስ
93▸ ያሲን የአላህ ስም ?
94▸ የቁረይሾች ድርድር
95▸ ኢየሱስ እና ፍቅረኛው
96▸ አምልኮተ ማሪያም 2
97▸ ግርዘት እና ጳውሎስ
510 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ