Get Mystery Box with random crypto!

ሁለተኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

ሁለተኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

ሰላም ውድ የማኀበረ ቅዱሳን ቻናል ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ ። በረድኤት ያልተለየን በቸርነቱ የጠበቀን ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን
#አድስ-ኮርስ ነው እንድትከታተሉ በትህትና እንጠይቃለን ።
__________
ሁለተኛ
ኮርስ

#ነገረ__ሃይማኖት


#ምዕራፍ-፩ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት መግቢያ

#ሃይማኖት_ምንድነው?
ሃይማኖት፦ ሐይመ
ነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተሰደ ሲሆን ትርጉሙ ማመን መታመን ማለት ነው።

ማመን፦ ማመን ማለት በአንድ ስጋ/በእዝነ ስጋ / ጀሮ ሰምቶ፣ በልብ አስቦ በአጠቃላይ በስሜት ህዋሳትም ቢሆን አድምጦ እና ዳሶ ሊመረምሩት የማይቻለውን በእርቀት (እሩቅ በመሆን) እና በርቀት (በረቂቅነት) ያለውን ይሆናል።
ይደረጋል ብሎ መቀበልና እግዚአብሔርን አለ፣ ይኖራል ሁሉን ያዥ፣ ሁሉን ገዥ ነው ብሎ በልብ በረቂቅ መሳልና ማሰብ ሀሳብን በማወቅ ማረጋገጥ፣ መፍቀድ፣ መውደድ፣ መመካት ተስፋ ማድረግ ማለት ነው።

መታመን፦ መታመን ማለት ደግሞ በልብ በረቂቅ ሀሳብ ያመኑትን በአንደበት መመስከር መናገር፣ ወዶና ፈቅዶ በደስታ መቀደስ፣ ማመስገን፣ በግብር መግለፅ መተግበር፣ መስገድ፣ መገዛት፣ መገበር ማለት ነው።
እንዲሁም መታመን ማለት ይሆናል ይደረጋል ብሎ በእምነት የተቀበሉትን እንዲሆን እንዲደረግ፣ እንዲፈፀም ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ማለት ነው።
እነዚህን ሁለቱን ከያዘ ከተገበረ ሀይማኖት አለው ይባላል። (ማር 16፥16 ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል።)

ምላሹ፦ በማመንና በእግዚአብሔር መጠመቅ ነው። ሉቃ 15፥11-32
ልብስ የተባለው ሀይማኖት ነው፣ ቀለበት እሰሩለት የተባለው ቃል ኪዳኑን ነው፣ ለእግሩ ጫማን አጨሙት የተባለው፣ ወንጌልን ስጡት ነው፣ የሰባውን ፍሪዳ እረዱ እና እንብላ ማለቱ ስጋወደሙን ነው። ይህ ልጅ ሙቶ ነበር አሁን ግን ህያው ሁኖል ማለት የሰው ልጅ በህይወት እያለም ይሞታል ማለት ነው። ምክኒያቱ ደግሞ ከሀይማኖት ሲለይ
/ሲወጣ፣ አባት የተባለው እግዚአብሔር አምላክ ነው ከሞትም ወደ ህይወት ተለውጧል ያለው በንስሐ ነው።
~~~~~~~~

#ወስብሐት# _ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan