Get Mystery Box with random crypto!

#ምድር በራች ሚካኤል ሲመጣ# ___ ምድር በራች ሚካኤል ሲመጣ ገናና ነው አሰሙት እልልታ ሚካኤል | የአካባቢ ወጣቶች መዝሙራት

#ምድር በራች ሚካኤል ሲመጣ#
___
ምድር በራች ሚካኤል ሲመጣ
ገናና ነው አሰሙት እልልታ
ሚካኤል /2/የአምላክ ባለሟል
___
ክንፉን ሲዘረጋ ውሀ ተናወጠ
በክብር ሲገለጥ ነገር ተለወጠ
በፍቅሩ ተዳሰው ድውያን ዘለሉ
የሚካኤል አምላክ ይባረክ እያሉ
አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ብርሀን የሚተፉት ግሩማን አይኖቹ
በፍቅር ያዩናል ዘውትር ሳይሰለቹ
ሲቀድም ሲመራ ተከፍሏል ባህሩ
ከርሱ ጋር የወጡ ሞትን ተሻገሩ
አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አለሁ ብዙ ዘመን ዝናህን ስሰማ
በፋርስም አንተው ነህ በግብፅም ከተማ
ወጥቼ አልቀረሁም ከአገር ተሰድጄ
ዳግም አርፌአለሁ ባንተ በወዳጄ
አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዳቢሎስ ዙፋን ተገልብጧል በእርሱ
ጠላት ሚደቅበት መብረቅ ነው ቀሚሱ
ቆሟል ዙፋኑ ፊት ምህረት እየጠና
ያደረገው ተአምር መቼ ተነካና
አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ክንፉን ሲዘረጋ ውሀ ተናወጠ
በክብር ሲገለጥ ነገር ተለወጠ
በፍቅሩ ተዳሰው ድውያን ዘለሉ
የሚካኤል አምላክ ያባረክ እያሉ

@maheberat
@maheberat
For any comment
@Natnael1201