Get Mystery Box with random crypto!

​​ ልሂድ ወደ ግሸን ልሂድ ወደ ግሸን /2/ | የአካባቢ ወጣቶች መዝሙራት

​​ ልሂድ ወደ ግሸን

ልሂድ ወደ ግሸን /2/

ልሂድ ወደ ግሸን
ዳስሽ እንድባረክ ዕፀ መስቀሉን "
መስቀልን በመስቀል እንባለ በቃሉ "
በግሸን ላይ ከብራል የጌታ መስቀሉ "
በክብር ተቀምጣል በአንባሰል ተራራ "
ዘለዓለም ይኖራል ድንቅን እየሰራ "

ልሂድ ፃድቃኔ ማርያም /2/

ልሂድ ፃድቃኔ ማርያም የበረከት ምድራን ደጃንም ልሳለም "
በገባልሽ ኪዳን የማህፀንሽ ፍሬ "
ድንግል ሆይ በምልጃሽ ተፈታ ችግሬ
እምነት ተባብሼ ፀበልሽን ብቀምሰው
የዓመታት ህመሜን ቁስሊን ተረተርሽው

ልየው አክሱም ፅዮንን/2/

ልየው አክሱም ፅዮንን
የኪዳኑ ታባት የከበረበት "
በእግዚአብሔር ጣቶች የተፃፉት ህግች "
በታባቱ ውስጥ ያሉት ሁለቱ ፅላቶች "
በሰሎሞን ዘመን በንግስተ ሳባ "
ከሚኒሊክ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ገባ "
እሰይ ደስ ይበልሽ እናቴ ኢትዮጵያ "
በምድርሽ ላይ ከትሞል የቃሉ ማደሪያ

እስኪ አምጡልኝ ቆቤን /2/

እስኪ አምጡልኝ ቆቤን ከደብረ ሊባኖስ ያሰፋውትን "
ቃልኪዳኑ ግሩም የወንጌል ገበሬ "
ታምርን ይሰራል ኪዳኑ እስከ ዛሬ "
ኢትዮጵያው ፃድቅ ተክለ ሃይማኖት "
በአርያም ታይተሃል ይዘ ማህጠንት "

እስኪ አምጡልኝ ዘንጌን /2/

እስኪ አምጡልኝ ዘንጌን
ከዝቋላ አባ ያሰራሁትን "
በርሃ ተወልዳ በርሃ ያደገው "
የእውነትን መንገድ ፅድቅን የፈለገ "
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሰራህው ስራ "
ዘለዓለም ይኖራል ገድል እያበራ "

ልሂድ ልሳለም /2/
የአዳዲዋን ማርያም ልሂድ ልሳለም
የእንጣጦዋን ማርያም ልሂድ ልሳለም
አክሱም ፅዮን ማርያም ልሂድ ልሳለም
ቅጥር ደጃን ልሳለም ልሂድ ልሳለም

ልምጣ ከደጅህ /2/
ደርሳልኛ ፀሎትህ ልምጣ ከደጅህ
ቅዱስ ዮሃንስ ፀበልህ ልምጣ ከደጅህ
ድኜ ቆምኩኝ ምልጃህ ልምጣ ከደጅህ
መጥቻለሁ ከደጅህ ልምጣ ከደጅህ

ናፈቀኝ ስምሽ /2/
የሲሪንቃው እመቤቴ ናፈቀኝ ስምሽ
ነይ አርሴማ ግቢ ቤቴ ናፈቀኝ ስምሽ
ስጦታሄ ሽልማቴ ናፈቀኝ ስምሽ
ቤቴ ክብሬ ነሽ ውበቴ ናፈቀኝ ስምሽ

@ maheberat
@maheberat

for any comment
@Natnael1201