Get Mystery Box with random crypto!

#ትንሣዔ አልባ ሞት አልገባሽም እየሞትኩ እንደሆነ ስተነፍስ፣ ሣወራ፣ ፈገግ ስል፣ .... ከነ | Maddbn እጅጉ ቃሲም ! ✍️

#ትንሣዔ አልባ ሞት

አልገባሽም እየሞትኩ እንደሆነ
ስተነፍስ፣ ሣወራ፣ ፈገግ ስል፣ .... ከነፍሴ የሚንጠባጠበው ደም አይታይሽም ስጋዬ እየፈራሰ ወደ ውስጥ ሲወድቅ አጥንቴ ቀስ በቀስ ሲበታተን አይታይሽም።

እንዴት ይታይሻል ቢታይሽ ነው የሚገርመኝ!

፩ የረገጥኳት ጠጠር በተረከዜ
ስትሸሽገኝ ከእኔ ልቃ... ...

፪ ከለኮስኳት ሻማ በመቅረዜ
ቀድሜያት ቀልጬ ስጠልቅ እንደ ጨረቃ!

እኔስ እንዴት አሳይሻለሁ ፥
ብሞክርስ እንደ ምን ችላሁ ?
አብረን ሁነን አብረን ሳለን
ሁለት ሁነን ለየብቻ ፤
መሆኔ! እንዴት ይታይሻል ?
ከረገጥኳት ጠጠር ስርቻ !
ኢምንት ሆኜ ትቢያ መታቀፌ ፤
ተራምደሽ ከምታልፊያቸው አሸዋዎች መሀል መሠለፌ ፤
እኔም እንዳንቺ እኔኑ እየረገጥኩ አብሬሽ ማለፌ .....

እንዴት ይገባሻል ?

አፌስ እንዴት ይነግርሻል
ምላሴ ትታው በርራ ፤
ወደ ሌለሽበት ሽሽታ
ወደ ሩ..ሩቅ በረሀ .......
~
ግን እኮ እዛ ነሽ ፥
ዛሬም ስሞት ፣ ነገም ስሞት፤
እዚህ ጎኔ ሁነሽ ....
ካልታየሽ !

~~~

ለነፍስ ምትሆን አንዲት ቅንጣት
አስራት የለኝ ወይ በኩራት ፤
ክንፌ ረግፎ በደረቴ እርክጎተት፥
ስከተልሽ እንደ ቢራቢሮ
ስንከራተት
ወዳ'ንቺ ስባዝን
ስቃትት ስዋትት....

በዝብዘሺኝ አቅሙም የለኝ....

፵ ጅራፍ ፈርደውብኝ ፥
አንዱ እንኳ ቢያርፍብኝ....
ከስርሽ የምፈርስ የዘላለም ሟች ነኝ!

maddbn