Get Mystery Box with random crypto!

Maddbn እጅጉ ቃሲም ! ✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ maddbn23ethio — Maddbn እጅጉ ቃሲም ! ✍️ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ maddbn23ethio — Maddbn እጅጉ ቃሲም ! ✍️
የሰርጥ አድራሻ: @maddbn23ethio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 380
የሰርጥ መግለጫ

@maddbn & @Poemrs_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-10 18:19:07 #ትንሣዔ አልባ ሞት

አልገባሽም እየሞትኩ እንደሆነ
ስተነፍስ፣ ሣወራ፣ ፈገግ ስል፣ .... ከነፍሴ የሚንጠባጠበው ደም አይታይሽም ስጋዬ እየፈራሰ ወደ ውስጥ ሲወድቅ አጥንቴ ቀስ በቀስ ሲበታተን አይታይሽም።

እንዴት ይታይሻል ቢታይሽ ነው የሚገርመኝ!

፩ የረገጥኳት ጠጠር በተረከዜ
ስትሸሽገኝ ከእኔ ልቃ... ...

፪ ከለኮስኳት ሻማ በመቅረዜ
ቀድሜያት ቀልጬ ስጠልቅ እንደ ጨረቃ!

እኔስ እንዴት አሳይሻለሁ ፥
ብሞክርስ እንደ ምን ችላሁ ?
አብረን ሁነን አብረን ሳለን
ሁለት ሁነን ለየብቻ ፤
መሆኔ! እንዴት ይታይሻል ?
ከረገጥኳት ጠጠር ስርቻ !
ኢምንት ሆኜ ትቢያ መታቀፌ ፤
ተራምደሽ ከምታልፊያቸው አሸዋዎች መሀል መሠለፌ ፤
እኔም እንዳንቺ እኔኑ እየረገጥኩ አብሬሽ ማለፌ .....

እንዴት ይገባሻል ?

አፌስ እንዴት ይነግርሻል
ምላሴ ትታው በርራ ፤
ወደ ሌለሽበት ሽሽታ
ወደ ሩ..ሩቅ በረሀ .......
~
ግን እኮ እዛ ነሽ ፥
ዛሬም ስሞት ፣ ነገም ስሞት፤
እዚህ ጎኔ ሁነሽ ....
ካልታየሽ !

~~~

ለነፍስ ምትሆን አንዲት ቅንጣት
አስራት የለኝ ወይ በኩራት ፤
ክንፌ ረግፎ በደረቴ እርክጎተት፥
ስከተልሽ እንደ ቢራቢሮ
ስንከራተት
ወዳ'ንቺ ስባዝን
ስቃትት ስዋትት....

በዝብዘሺኝ አቅሙም የለኝ....

፵ ጅራፍ ፈርደውብኝ ፥
አንዱ እንኳ ቢያርፍብኝ....
ከስርሽ የምፈርስ የዘላለም ሟች ነኝ!

maddbn
60 views🇲 🇦 🇩 🇩 🇧 🇳 . E . Q ., 15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 09:16:41 መስተ ውበት

maddbn እጅጉ

ቀጭን ለግላጋ ..... ..እርጥብ ቄጤማ። ቅጥነቷ ደስ የሚል ቁመቷም የሰጠ....ደም ግባታም የሆነች ቆንጆ ናት። ሞቫይሉ ላይ የሞላው የእሷ ምስልና ቪዲዮ ነው። አሁንም አሁንም እየመራረጠ ያሳየኛል በፍለጋው መሀል ያዳንቃል በተኛበት ሆኖ እያፏጨ ምስሏን 'ቀረብ ረብ' አርጎ ያየውና፤ በእግሩ አየር ላይ እንደመሮጥ አይነት በፍጥነት አወራጭቶ ከብለል ይላል። እንሳሳቃለን በሁኔታው።
"እየው በናትህ!" ብሎ ፊቴ ላይ ደቀነው የከፈተውን ቪዲዮ። ከአገጬ ወደ ደረቴ ጠጋ አድርጌ ማየት ጀመርኩ... ታምራለች ስትደንስ የቡጊ ውጊ ሴት አማልክት ትመስላለች።

አንገቷ ላይ በሀብል ያንጠለጠለችው ከዚህ በፊት አይቸው የማላውቀው ጠልሰም ቢጤ አብሯት እየተወዛወዘ ዳንሷን ያዳምቃል። የሆነ ነገር እንድጠረጥር ፮ተኛው ስሜቴ ሹክ ብሎኝ አለፈ....። እየዘፈነች ሌላ ቪዲዮ አሳየኝ፤ ያምራል ድምጿ ለጉድ!! ጉሮሮዋ ንፁህ ነው ድምጿ ከምንም ሳይላተም ምንም ሳይንገጫገጭ እንደ እንባ ኩልልል ብሎ ይወርዳል። ያለ ማጋነን በዚህ መረዋ ክርስትናን ብትሰብከው ዲያቢሎስ ጌታን ይቀበላል። እቺ ገነት ገብታ ሁሉ እንጆሪ ለመልቀም ቅርጫቷን ይዛ በዱር በጫካው በአትክልት ቦታው እየዞረች ብትዘምር አንበሳው " ነይ እኔን ጋልቢኝ !" ንስሩ "ተይው እሱን ጎፈሬው ቀምሎዋል ነይ እኔ ይዤሽ ልብረር ...?" እያሏት ሲፎካከሩ ቆማ እያየች ሳታስበው ቅርጫቷ በየፍራፍሬው ተሞልቶ፤ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "እነሆኝ እመቤቴ ሆይ እኛ ለቅመንልሻል" ብሎ ዘወር ሲል፤ አሻግራ ስታይ ሁሉም መላዕክት ከአንገቱ ሰበር ብሎ እጅ ይነሳል። " ያ አንተ ያለህ ገብሬል ሰይፋን የት ጣለው ባክህ?" ነብሮች ያንሾካሽካሉ..........።

ለምን የ፩ሚሊዮን ሴት ውበት ባከነባት፤ ወይስ አካብደናት ነው? ራሴን ጠየኩኝ። እንከን ስፈልግባት ፊቷ ማንኪያ ቢጤ ነው በደንብ ያልተለመጠ አፍንጫዋ አከባቢ ከላይኛው ከንፈሯ እስከ ስረኛው አይኗ ሩብ ጉዳይ ሰመጥ ይላል ፊቷ ሰመጥ እንኳን ይበዛል ትን...ሽ ትንሽ በጣም ገባ ብሎዋል ቢሆንም ልንቀበለው አንፈልግም ያን እንከን። ለምን ? ለምን ጉድለቷ ላይ ደበዘዘብን አይናችን? <አስማት ይሆን እንዴ?>

"ይሄ ምንድነው?" አልኩት አንገቷ ላይ ያለውን ነገር።
"የቱ?" አለ ቆጣ ብሎ አቃቂር ሳወጣ እንደቆየሁ ገብቶታል።
"ይሄ ነዋ አንገቷ ላይ ያለው መስተ ውበት ነው?" እንዳይናደድ ሳቅ ብዬ።
"መስተ ውበት ደግሞ ምንድነው?"
"እንደ መስተ ፋቅር ነዋ"
"መስተ ውበት ሚባል ነገር የለም ባክህ ምንድን ምትዘባርቀው"
"ነው እንጂ ለሁሉም በጣም ቆንጆ ሆና እንድትታይ የሚያደርግ"
"ኦ ሰውዬ አትበድብኝ እዛው ሂደህ ተፈላሰፍ መስተ ውበት ይላል እንዴ ግም"
"ካ ካ ካ" አልቻልኩም ሳቅሁ። "ምንድን የሚያናድድህ ደሞ ልትደበድበኝ ነው እንዴ?"
እጁን አወራጨና "ኤጭ ወደዛ በል ባክህ" አለ።
" ጥናዣም ስትፈልግ በሻይ ብላት " አልኩ የምር ተናድጄ።

መጨቃጨቁ ስለማያዛልቀን ትቼው ማሰላሰል ጀመርኩ <እውነት ቆይ እንደ መስተ ፋቅር መስተ ውበት ቢኖርስ?> <ያ ለመወደድ ወይም መወደጃ ነው ይሄ ደግሞ ውብ ሆኖ መታያ በመልክ ብቻ መማረኪያ ከፍቅር ውጪ .... ግን ይቀራረባሉ መስተ ውበት የአይን ፍቅር ጋ ግንኙነት አለው ኮ....> <በቃ አንድም ሁለትም ናቸው ።> እንዲህ እያልኩ ከራሴ ጋር ብዙ ዘባረቅኩ፤ እውነት ግን መስተ ውበት ሚባል የለም እንዴ ? ካለ አለ ከሌለም እንደ ደብተራ መድገም ባልችልም እነሆ የአዲስ ድግምት ሀሳብ ባለቤት ነኝ።

\\
maddbn
፳፩ ታህሳስ ፪፻፲፫
57 views🇲 🇦 🇩 🇩 🇧 🇳 . E . Q ., 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 17:08:35 የባተሌው ዜና መዋዕል !

ረመጥ አቅፌ የምሰቃይ ስጉም፤
ላላመልጠው ምሸሽ የራሴን ተንከተም ።
ነፍሴን ለመሸጥ ያቀናሁ ገበያ።
ነፍሴን ልሸምት የወጣሁ ገበያ ።
ሹም በላዬ የራሴ ባሪያ !
ባዶ ባዶ.......... ባዶ
ብዘዙዙ ሚሊዮን ባዶ
አቻ የሌላቸው ..........

ኮኮቦች ቢረግፉ ጥንድ ማይሆኗቸው
እልፍ አእላፍ ባዶ
ቀልጦ ማያጠፋቸው የአትላንቲክ በረዶ
..... .... ..

ነፋስ ማይበትነው ወደዚም ወደ እዛ፤
እሰከ ተሲዓት ድረስ የማይጠፋ ጤዛ።
የደብተራ ክህነት
የሺ እግዜር ቤዛነት፥
ተመን የማይሆነው
የማይወዳደረው .....።
**
ብዙ ጎዶሎነት ፥
፲ሺ ከንቱነት
በ፳ ዓመት እድሜ ፥
፺ አፈር ድሜ ።
..... ...................
..................................

!
maddbn
66 views🇲 🇦 🇩 🇩 🇧 🇳 . E . Q ., 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 18:04:53 # ህልሜን በህልሜ አየኋት
ማድብን

የፍቅር ሙዚቃ <ክሊፕ> እንደሚሰራ ሰው ፩ እግሬን አጠፍ አድርጌ ፣ እጆቼን ኪሴ ውስጥ ከትቼ እያፏጨው ፤... .. ዛፍ ተደግፌ በጆሮዬ ፤ ወፎች ሚያዜሙትን ቅኔ ያዘለ ሙዚቃ... ፣ በአይኔ ከየዛፉ የወዳደቁ ፍሬዎችን ማንጎራጎር የሰለቻቸው ወፎች አሞሮች ሲሻሙት ... ቢራቢሮዎች በውብ አበባ ዙሪያ እየበረሩ አባሮሽ ሲጫወቱ እያየሁ ... ሁሌ እያረፈደች ልቤን ብትሰቅለውም ቀርታ ስለማታውቅ ገሊን ጠብቃታለሁ።

ዛሬ ከእሷ ጋር በ11 ሰዓት እዚህ ውብ ስፍራ ቀጠሮ አለኝ ። እንኳን እንደኛ ልባቸው ለተቃቀፈ ፤ ቂም ና ቁርሾ ያለባቸው በደም ሚፈላለጉ ጠበኞች ድንገት ቢገናኙ ተቃቅፈው ሚሳሳሙበት ! ፍቅር ብቻ ሚነፍስበት ገነት ቀረሽ በየብስ ያለ ቦታ ነው። ቦታውን ሰፋ አርጌ ሁሉም የሀበሻ ህዝብ እዚህ እንዲኖር ባደርግ ምኞቴ ነው።

"ምነው ዛሬ ደሞ ብዙ ቆየችሳ ? " በሚል የሸሚዜን እጅጌ ሠብስቤ ፣ ሠዓት አይቼ ቀና ስል ፤ በቀስተ ደመና የተነከረ ፣ በዓለም ካሉት ሁሉ እጅግ የተዋበውን ቀሚስ ለብሳ ፣ ለመራመድ እንዲመቻት በግራ እጇ ወደ ላይ ሰብሰብ አድርጋ ይዛው እንደሙሽራ ፣ ወፍራም ጥቁር ወዛም አብረቅራቂ ፀጉሯን ንፋስ እየበተነው ቃላት በማይገልፀው ውብ ቅርፅ ተጠርበው በተደረደሩ በረዶ ጥርሶችዋ ፈገግታዋን ለኩሳ ፣ እንደ " remote control " በተስለመለሙ ቁጥር ስሜቶቼን ሚቀያይሩትን አይኖችዋን ተክላብኝ ፣ ዜማና ሪትም ባለው አረማመድዋ አጠገቤ መጥታ እቅፍ..ፍ አርጋ ስትስመኝ ፣ ፀጉሯ አሁንም በንፉስ ፊቴ ላይ ሲበተን የፀጉሯን ጠረን እየሳብኩ ዘላለም መኖር ስመኝ ፣ የተመኘሁትን ስነግራት ፤ <<አንተ እብድ ብላ ! >> ስትስቅብኝ ፣ እብድ አትበይኝ አላልኩሽም ብዬ ጉንጯን ቆንጠጥ ሳደርግ ፣ የውሸት ስታኮርፍ የቆነጠጥኩት ቦታ ላይ እስማታለሁ .... ። << እሱጋ ብቻ ነው የምትስመኝ ? >> ብላ እነዛ ለደቂቃ ችዬ ማላያቸውን አይኖችዋን በአይኔ ላይ ተክላብኝ ከንፈሯን ፤ ስስ ቀይ ከንፈሯን ! እንድስመው ስታመቻች ፣ ልስማት ስጠጋ ተጠግቼም የ፩ ጣት ግማሽ ከንፋስ ሲቀረኝ ......

ፊቴ ላይ የተረጨውን ውሀ እየጠራረኩ << መቀስቀስሽ እሺ ይሁን ውሀ መርጨቱን ምን አመጣው ! ደሞ ምን ከመሰለ ህልም መሰለሽ የቀሰቀስሺኝ ምን እንደው እዚ... >> ተነጫነጭኩ!

<< ብጠራህ ብጠራህ መች ትሰማለህ እንዲሁ እየተገላበጥክ ታንጎላጃለህ እንጂ : ከነጋ ደሞ የት አገር ነው ሚታለመው ባክህ ቀጣፊ በል አሁን ቁርስ ቅመስና ቶሎ ውጣ ሰዓት ሂዶብሀል... >>

<< አልበላም እንደውም ደህና ዋይ>> ፊቴን ተለቃልቄ እነደነገሩ ለብሼ ወጣሁ ።

maddbn
95 views🇲 🇦 🇩 🇩 🇧 🇳 . E . Q ., 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 21:24:56 Channel name was changed to «Maddbn እጅጉ ቃሲም ! »
18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 21:23:40 Channel photo updated
18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ