Get Mystery Box with random crypto!

የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ጥናት 2.8 በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበ | ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)

የዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ጥናት 2.8

በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ

“በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፥”ራእይ 1፥10

የጌታ ቀን ምንድነው መቼ ነው?

✥በመፅሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ "የጌታ ቀን" ለምለው አሳብ በብሉይና በአዲሱ ኪዳን የተለያዩ አውዳዊ ትርጉሞች አሉት።
በዝህ ቦታ ለተጠቀሰው የጌታ ቀን ምንድነው ለምለው የተለያዩ አመለካከቶች አሉ።

1.የፍርድ እና የእግዚአብሔር ቁጣ ቀን
2.የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን(እሁድ)

➤የጌታ ቀን የፍርድ እና የእግዚአብሔር ቁጣ ቀን ስሆን፦ሰው እግዚአብሔርን በለመታዘዙ ሀጢያቱ ምክንያት በተፈጠረው መዘዝ አሁን ዓለም ላይ የሚታየውን ክፋት እና የጨለማውን መንግስት ለማስወገድ እግዚአብሔር ቀን ቀጥሯል። ያም ቀን የጌታ ቀን በመባል ይታወቃል። ራዕ 11፥17 ኢሳ 2፥12 ኢዩ 1፥15 ህዝ 13፥5

➤የጌታ ቀን የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን(እሁድ) ስሆን፦ በቀደምት ቤተከርስቲያን ክርስቲያኖች የጌታን ከሙታን መነሳት ለማክበርና ለማምለክ የምሰበሰቡበትን ቀን ያመለክታል። ሀዋ 20፥7 1ቆሮ 16፥2

እንግዲህ ብዙዎች እንደምሰማሙት በዝህ ቦታ(ራዕ 1፥10) የጌታ ቀን ተብሎ የተጠቀሰው የሳምንቱን መጀመሪያ ቀን እሁድን ለማመልከት ነው። ይህ ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ እሁድን ለማመልከት እዝህ ቦታ ብቻ ተጠቅሷል።ዮሐንስ ይህንን ራዕይ የተቀበለው በዝህ ቀን ነበር።

በመንፈስ ነበርሁ ማለት ምን ማለት ነው?
✥ሀዋርያ ዮሐንስ በመንፈስ ነበርሁ ስል፦
➤መንፈስ ቅዱስን እየሰማሁ ነበር
➤በአምልኮ እና በፀሎት ውስጥ ነበርሁ
➤በህልውናው ውስጥ ነበርሁ
➤መንፈሳዊ ነገር እያሰብኩ ነበርሁ
➤ቅዱስ ቃሉን እያሰላሰልኩ ነበርሁ
➤በመንፈስ ቅዱስ እየተነዳሁ(እየተመራሁ) ነበርሁ ማለቱ ነው።
እንግዲህ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ሁሉንም መልእክት ጸሀፊዎች ይፃፉልን በመንፈስ ሆነው ነው እንጅ ዝም ብለው በስጋ ህይወት እንደ ልብወለድ እንጻፍ እንጻፍ ብለው አይደለም። የእግዚአብሔርን መልእክት ልዩ የሚያደርገውም ይህ ነው። ሰው በመንፈስ የምሆንበት ግዜ አለ ደግሞም በስጋ የሚሆንበት ግዜ አለ።
በመንፈስ ስሆን፦ ይፀልያል፣መንፈሳዊ ነገርን ያስባል፣ራዕይ ያያል፣ያመልካል፣የእግዚአብሔርን ቃል ያሰላስላል፣የእግዚአብሔርን ድምፅ ይሰማል።የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን ያንፀባርቃል።
በስጋ ስሆን፦ ስጋዊ ነገሮች ያስባል(መብላት፣መጠጣት፣የስጋ ፍሬዎችን መተግበር፣ሀጢያት መስራት ......የመሳሰሉትን ነገሮች ያደርጋል)።ከእግዚአብሔር ሀሳብ በተቃራኒው ይቆማል።

ሃዋሪያው ዮሐንስ ቀጥሎ የሚለን "በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ"ይላል።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው?
የመለከት ድምፅ የሚሰማው በተለያዩ ምክንያቶች ነው።
1.ሰንብት መግባቱን ለማሳወቅ
2.የእስራኤል በዓላት ስደርሱ
3.ንጉሥ ስቀባ
4.ጦርነት ስሆን
5.ስብሰባ ስጠራ
6.በኢየሱስ መምጫ ግዜ
7.በዝህ ቦታ በተገለጸው መሰረት "ለአስቸኳይ መልእክት" ይነፋል።
ዮሐንስ ዞር ይህንን ድምፅ ሰማ

መልእክቴ
✥ይህ አስቸኳይ የመለከት ድምፅ ተሰምቷልና
ከእንቅልፍ እንነሳ
ግዜው ደርሷልና ወንጌልን እንመስክር
ግዜው አልቋልና እንዘጋጅ
እንፀልይ እናንብብ እናገለግል
✥ለዘመናት የሚሆን ራዕይ የሚመጣው በመንፈስ ስንሆን ነውና በመንፈስ እንሁን።
✥የእግዚአብሔርን ድምፅ ከሌላ ድምፅ እንለይ።
✥መንፈሳዊ ነገርን የሚናስብበት ግዜ አለን? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
✥በመንፈስ ሆነን ሰማያዊ መገለጥ እንቀበል። ኢየሱስ ይመጣል
ይቀጥላል ....

ታናሽ ወንድማችሁ #መብራቱ መንግሥቱ ነኝ

https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp