Get Mystery Box with random crypto!

ፎቶዎችን በፊት ለፊት ገፁ ላይ ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ በዘመኑ ዝነኛው የTonight Show | ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)

ፎቶዎችን በፊት ለፊት ገፁ ላይ ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ በዘመኑ ዝነኛው የTonight Show አቅራቢ ጆኒ ካርሰን በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ዙሪያ ሠፊ ዘገባ ይዞ ቀርቧል፡፡ በአሜሪካ የዘመኑ ቁንጮ ኮሜዲያን የነበሩት እነ ፍሊፕ ዊልሰንና ሩት ቡዚ የካትሪንን የአሰባበክ ለዛና የተክለ ሰውነት ገፅታ እያስመሰሉ በየመድረኮቻቸው ላይ ያቀርቡ እንደነበር የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን በመጽሐፉ ላይ ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡ ይህንን የካትሪን ኩልማን በምድር አጽናፍ ሁሉ መግነንን ሳስብ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈሩት እነዚህ ህያው የእግዚአብሔር ቃሎች ይባርኩኛል፡- አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ (መሃ2፡12)።
የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ (ነህ 12፡43)።
በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፥ … ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤
በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም። … ዝናውም ወዲያው በየስፍራው
ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ … ወገኔ የእግዚአብሔር ሰው በአንተ ውስጥ ያደረውን መንፈስ ቅዱስ እውቅና ከሰጠኸው በቀሪ ዘመኔ ሁሉ ይጠቀምብኝና ልሙት የሚል የወንጌል ፅናት ካለህ መታሰቢያህ ፈጽሞ ጎጥ ውስጥ ተሸሽጎ አይቀርም፡፡ እግዚአብሔር አምላክህ ስለ ስሙ ሲል ተጽኖህን አለማቀፋዊ ያደርገዋል፡፡ በአንተ እውቅና ውስጥም የዘላለም አ ንዳው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አብዝቶ ያገነዋል፡፡
የካትሪን ኩልማን ወርቃማ አባባሎች
በእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ተቀብቶ ለማገልገል ምንም ዓይነት የሃይማኖት ፎርሙላ አያስፈልግም፡፡ ሚስጥሩ አንድ ነው ልክ ጌታ ኢየሱስ እንደተናገረው በርሃብ የታጀበ የማገልግል ፍቃደኝነት ብቻ፡፡
ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ። ‹‹ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ›› ብሎእንደተናገረው ማለት ነው (ዮሐ 7፡37)፡፡
• በአለም ላይ ትልቁ ስኬት ማለት ራስን ለእግዚአብሔር ፍቃድ ማስገዛት ነው፡፡
• እግዚአብሔር በዱሮ መንገድ መሄድ አይወድም፤ እንዲሁም አሮጌን ነገር አያድስም፡፡ ይልቁንም አዲስን ነገር ማድረግ እጅግ ደስ ይለዋል፡፡
• ግና የሆኑ የመርከብ ካፒቴኖች ሻካራማና አለታማ በሆኑ ባህሮች ውስጥ አልፈው ያሰቡት ቦታ መድረስ ይወዳሉ፡፡ እንዲሁ ግና የሆኑ የክርስቶስ አገልጋዮች ጠማማና አዳጋች በሆኑ የህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፈው ከፍጻሚያቸው ጋር ይገናኛሉ፡፡
•  የእግዚአብሔር ኃይል በሙላት በእኛ ውስጥ እንዲገለጥም ሆነ እንዲሰወር ሚስጥሩ ፍቃዳችን ውስጥ ተሸሽጓል፡፡
• ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ለደህንነታችን ብቻ ሳይሆን ለበሽታችንም ጭምር ነው፡፡ ‹‹ተፈፀመ›› ብሎ የተናገረው ስለ መዳናችን ብቻ ሳይሆን ስለ ተግዳሮቶቻችንም ያካትታል፡፡

ጃሚ ቡኪንግሃም ጎስት ሪትን ብላ በጻፈቺው መጽሐፏ ውስጥ የካትሪን ኩልማንን በርካታ የፈውስና የተሃምራት አገልግሎቶችን በሰነድ መልክ ዘግባለች፡፡ ከብዙዎቹ ጥቂቶችን የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ቁጥራቸው ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሠዎች ኪም በማስረጃ ከሚያውቀው ከተለያዩ በሽታዎችን ክሮኒክ ካንሰርንም ጨምሮ ተፈውሰዋል፡፡
• በሃይማኖት የፈውስ ተሃምራት ዙሪያ ተደጋጋሚ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቁት ፕሮፌሰር ከርነር የካትሪን ኩልማንን የፈውስ አገልግሎት እውነተኛነት ለማረጋገጥ በቅርብ ጊዜ ባደረጉት ጥናት መሠረት የሚከተለውን ፅሐፍ በጥናታዊ ፅሑፎቻቸውን ውስጥ አካተዋል፡፡
‹‹አንዳንድ ሠዎች በካትሪን የፈውስ አገልግሎት ዙሪያ ያለቸውን ጥርጣሬ ሲያንፀባርቁ ሰምቺያለሁ፡፡ ለዚህም ነው በካትሪን ኩልማን የፈውስ አገልግሎት ዙሪያ እውነተኝነቱን ለማረጋገጥ በርካታ ታሪካዊ ሰነዶችን ሳገላብጥ የከርምኩት፡፡ ምናልባት ከሰነድ አያያዝ ችግር ግነቶችና አጠራጣሪ ግንዛቤዎች ቢኖሩም የካትሪን ኩልማን የፈውስ አገልግሎት እውነተኛነት የሚያረጋግጡ በቂ ማስራጃዎችን እነሆ በእጆቼ ላይ ይገኛሉ፡፡ በብዙ በሽተኞች ላይ የተካሄዱት ፈውሶች አምላካዊ እጅ ካልሆነ በስተቀር በሰው ልቦና የሚታሰቡ አይደሉም›› ብለዋል፡፡
ራልፍ ዊክርሰን የደቡብ ካሊፎኒያ የክርስቲያን ሴንተር ባለራዕይና መስራች ነው፡፡ በእርሱ ላይ የመጣው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ክብር ምንጩ ካትሪን ኩልማን እንደነበረች ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ቤን ሂን በቆመበት አደባባዮች ሁሉ አሁን ላለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት
መነሳሳትና መቀጣጠል ካትሪን ኩልማን ምክንያት እንደሆነቺው ይመሰክራል፡፡ እንደውም ቤን ሂን
አግዝፎ ሲናገር ‹‹የካትሪን ኩልማን የአገልግሎት ሌጋሲ የቀጠለው በእኔ አገልግሎት ነው›› እያለ ይመሰክራል፡፡ እውቋ የፔንቴኮስታል ታሪክ ዘጋቢዋ ቪንሰን ሲናን "She was a woman minister at a time when most healing evangelists were men›› ብላ ስለ ካትሪን ኩልማን ትመሰክራለች፡፡
ወገኖቼ ኢትዮጵያም በመንፈስ ቅዱስ ክብር በቅርብ ጊዜ ትወረሳለች፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሙላታዊ ክብሩን ልክ እንደ ካትሪን ኩልማን እንደውም አልቆ በእኛም አገር እናቶችና እህቶችም ላይመጠቀም ይጀምራል፡፡ ሙታን ይነሳሉ፤ አንካሶች ይዘላሉ፤ መስማትና ማየት የተሳናቸው ወንጌልን ይሰማሉ ክብሩን ይመለከታሉ፡፡ ዘመኑ ሩቅ አይደለም፡፡ እነሆ በደጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በከባድ የመንፈስ ቅዱስ ክብር ትታረሳለች፡፡