Get Mystery Box with random crypto!

#አስተማሪ_ታሪክ ጥንዶቹ ከተጋቡ 11 ዓመታቸው ነው፡፡ ነገር ግን ልጅ ማግኘት አልቻሉም፡፡ በ | 👉👉👉❤️❤️❤️❤️👈👈👈

#አስተማሪ_ታሪክ

ጥንዶቹ ከተጋቡ 11 ዓመታቸው ነው፡፡ ነገር ግን ልጅ ማግኘት አልቻሉም፡፡ በሰተመጨረሻ ግን ከ11 ዓመታት ጥበቃ በኋላ የልመናቸውን ፍሬ ወንድ ልጅ ተበረከተላቸው፡፡ ልጁ ከእነሱ አልፎ የቤተ ዘመዱ ሁሉ ዓይን ማረፊያ ሆነ፡፡ ደስታ እና ፌሽታ ከእዚ ህፃን ጋር አብረው ወደ ጥንዶቹ ጎጆ ብቅ አሉ፡፡ ይህ ፃና 2 ዓመት ሆነው፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ጠዋት ባል ስራ እረፍዶበት እየተጣደፈ ሳለ እናት ከምትወስደው መዳኒት አንዱ ክዳኑ ተከፍቶ ሳሎን ጠረጴዛ ላይ ከእነ ብልቃጡ ተቀምጦ ተመለከተ፡፡ እና እንድታነሳውና ከድና ህፃኑ የማያገኘው ቦታ እንድታስቀምጠው ነግሯት ወደ ስራ ሄደ፡፡

እናት ብዙ ስራዎች ነበሯትና ስትሯሯጥ ጠረጴዛ ላይ ያለውን መድኃኒት ዘነጋችው፡፡ ትዝ እንዳላት ለማንሳት ወደ ሳሎን እሮጠች፤ ነገር ግን መድኃኒቱ የለም፡፡ ልቧ ለሁለት ተሰነጠቀ፡፡ ወዲያውኑ ልጇን ስትመለከት ከሶፋው ስር ወድቆ አራፈ ይደፍቃል፡፡ ቤቱን በእሪታ አቀለጠችው፡፡ ተጣድፈው ወደ ሃኪም ቤት ወሰዱት፡፡ ነገር ግን ከሚባለዉ በላይ እረፍዷል፡፡ ህፃኑ ድቡልቡሎቹን እንክብሎች እንደከረሚላ እያሰበ በሙሉ ውጧቸዋል፡፡ እናም እንኳን የ2 ዓመት ልጅ አዋቂም በማይችለው መልኩ ከመጠን በላይ መድኃኒት ጨጓራው ላይ በማረፉ ከ11 ዓመት ጥበቃ በኀላ በቤተ ዘመድ ፀሎት የመጣው ጨቅላ ገና ዳዴን እንኳን በቅጡ ሳይጨርስ ላይመለስ አሸለበ፡፡

እናት ዕብድ ሆናለች፤ ገና ደሞ ጠዋት ላይ እንድታነሳው አስጠንቅቋት የወጣው ባል ሲሰማ ምን እንደሚላት ስታስብ አእምሮዋ ተዛባ፡፡ ጠዋት ሰላም ዋሉ ብሎ በደስታ ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ የወጣው ባል ሆስፒታል እንዴት እንደደረሰ አያውቀውም፡፡ ሚስቱን ጨምሮ ዘመድ አዝማዱ ሲያለቅስ ውድ ልጁን እንዳጣ መንፈሱ ነገረው፤ ትንፋሽ ሳያወጣ እንባ ልክ እንደተከፈተ ቧንቧ በአይኖቹ ግራና ቀኝ ያለማቋረጥ መውረድ ጀመሩ፡፡

ወደ ሚስት ተጠጋ፤ ሚስት "ይቅርታ" በሚል አስተያየት በቀጣይ ከባል አንደበት የሚወጡትን ቃላት ለመስማት መጠበቅ ጀመረች፡፡ "አንቺ ነሽ ልጄን የገደልሽው" ይለኛል ብላ ጠበቀች፡፡ ባል ግን አንዲት ቃል ሳይተነፍስ አቅፏት ማልቀስ ጀመረ፡፡ ቀጠለና ውዴ "አይዞሽ እናቴ፤ እንግዲህ የፈጣሪ ፈቃድ ነው የሆነው" በማለት ሊያፅናናት ሞከር፡፡

እናት ፈፅሞ ያልጠበቀችውን ነገር በመስማቷ ጉልበት ሆናት፡፡ አዎ ይቺ እናት በዚህ ሰዓት የሚያስፈልጋት ወቀሳ፣ ለምን እንዲህ አላደረግሽም? የሚል ቁጣ ሳይሆን ብርታት የሚሆኗት የማፅናኛ ቃላት፣ እንባዋን የሚጠርጉ እጆች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ለክ እንደ ባል እሷም ያጣችው አንድ ልጇን ነው፡፡

በተጨማሪ ደሞ ለልጁ ሞት ከእሷ ባልተናነሰ ባልም ተጠያቂ ነው፡፡ መድኃኒቱን እንደተመለከተ ከማዘዝ ይልቅ እራሱ አንሰቶ ከድኖ ማስቀመጥ ይችል ነበር፡፡ አሁን ላይ አንቺ ነሽ፤ አንተ ነህ መባባሉ ህፃኑን አይመልሰውም፡፡ ነገር ግን በሕይወት ያሉትን ሰዎች ስሜት ይጎዳል እንጂ፡፡

በእኛ ህይወትም ሁሌ እንዲህ አይነት ሁነቶች ይፈጠራሉ፡፡ ነገር ግን ተጎጂ ሁለታችንም ሆነን ሳለ፤ ያጠፋነው ሁለታችንም ሆነን ሳለ ጣቶቻችንን ወደ ሌሎች ለመቀሰር እንወዳለን፡፡

"ምላስ አጥንት የለውም ግን ሰዎችን ይወጋል"

እኔነቴ ከሚለው የጳውሎስ መፀሐፍ የተቀነጨበ
#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos