Get Mystery Box with random crypto!

............ ' ከዛፉ ተማሩ ' .............. ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ | 👉👉👉❤️❤️❤️❤️👈👈👈

............ " ከዛፉ ተማሩ " ..............

ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንደትንጠለጠለበት ሁላ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል። ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ……..
ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር።
አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ሕይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፣ ልምዳችን፣ ስርዓታችን፣ ተግባራችን ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ ስራችንን እንደማስተካከል ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን። ወገን እናስተውል።

#አስተሳሰብና #አመለካከታችን ላይ መስራቱ ቢቀድም በጎ ነው፤አለዚያ ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ ይሆናል ነገሩ !!!!!!!!

#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos