Get Mystery Box with random crypto!

#ዛሬ_የቆሸሸው_ነገ_ታጥቦ_ይጠራልና_ቆሻሻውን_እንጂ_ልብሱን_አትጥላው እስኪ አንድ ነገር ልጠ | 👉👉👉❤️❤️❤️❤️👈👈👈

#ዛሬ_የቆሸሸው_ነገ_ታጥቦ_ይጠራልና_ቆሻሻውን_እንጂ_ልብሱን_አትጥላው

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ መልሱልኝ? አንድ ቡቲክ ገብታችሁ በጣም የሚያምረውን እና ውድ የሆነውን ልብስ ገዝታችሁ ወጣችሁ… ከዛም ለቀናት ለበሳችሁት በጣም ቆሸሸ… ያ የሚያምረውና የምትወዱት ልብስ አሁን ከማስጠላቱ የተነሳ እንኳን ለመልበስ በእጃቹሁ ለመንካት ቀፈፋችሁ እና ስንት ከፍላችሁ የገዛችሁትን ልብስ በመቆሸሹ ብቻ ትጥሉታላችሁ? ታቃጥሉታላችሁ? መቼም አዎ የሚለኝ አይኖርም፡፡

የሰው ልጅም እንደዚሁ ልብስ መጀመሪያ ላይ ፈጣሪ በውድ ዋጋ ፈቅዶና ወዶ ነው የሰጠው። ልብሱም ንፁህ የሆነው ስብዕናው ነው፡፡ ከዛ ወደዚች ክፉ ዓለም ሲመጣ አእምሮውም ሆነ ልቡ ቆሸሸ፡፡ ነገር ግን ሰውም ልክ እንደቆሸሸው ልብስ አስተሳሰቡና ተግባሩ ታጥቦ መፅዳት ይችላልና በሰዎች ላይ ተስፋ አንቁረጥ፡፡

በሱስ የተጠመደ ጓደኛ ካለክ ወንድሜ የተጠናወተውን ሱስ እንጂ ጓደኛክን አትጥላው፤ ምክንያቱም በአንድ ወቅት እሱም እንዳንተ እንከን የማይወጣለት ሰው ነበረና፡፡

ክፋት በልቡ ላይ ነገሶ በሰዎች ላይ መጥፎን የሚያደርግ ወዳጅ ካለክ ተግባሩን እንጂ እሱን አትጥላው፡፡ ጥላቻ እኮ የክፋት አንዱ አካል ነው። ክፉ የሚሰሩ ሰዎችን ከጠላን እኛ ከእነሱ በምን ተለየን? በልብ ያደረ ጥላቻ ነገ መጥፎ ተግባርን ይወልዳልና እንጠንቀቅ፡፡

ቀና ቀናውን እናስብ… መልካም መልካሙን እንናገር…

ይቀላቀሉን


#Pawlos
https://t.me/Loveerdey
#የጳውሎስ_መጣጥፎች
https://t.me/Arte_Pawlos