Get Mystery Box with random crypto!

“አንድ ሰው ለመንገደኛ ሰው ከአካልህ አንዱን (ለምሳሌ እጅህን) አንስቶ ቢሰጠው ትበሳጫለህ። ሆኖም | 15:53

“አንድ ሰው ለመንገደኛ ሰው ከአካልህ አንዱን (ለምሳሌ እጅህን) አንስቶ ቢሰጠው ትበሳጫለህ። ሆኖም የአንተን አእምሮ ለመጣው ለሄደው ሁሉ ትሰጣለህ፤ ብዙ ሰው አንተን ያጠቃሃል፤ በዚህም ትበጠበጣለህ፤ ትቸገራለህ… ይህስ አያሳፍርህም?”
#ኤፒክቴተስ

ሳናስበውም ቢሆን አካላችንን እንጠብቀዋለን። ሰዎች እንዲነኩንም ሆነ እጃችንን ይዘው እንዲያሽከረክሩን አንፈቅድላቸውም። ሆኖም ወደ አእምሯችን ስንመጣ ቁጥጥራችን ይላላል። በፍቃደኝነትም ለፌስቡክ፣ ለቴሌቪዥን ወይም ለሌሎች ሰዎች ለሚያስቡት፣ ለሚናገሩት፣ ለሚያደርጉት ነገር አሳልፈን ሰጥተነዋል። ስራ ልንሰራ ተቀምጠን ጥቂት እንኳ ሳንቆይ ራሳችንን ኢንተርኔት ላይ እናገኘዋለን። ከቤተሰብ ጋር እንቀመጣለን፤ በደቂቃዎችም ስልካችንን ፍለጋ እጃችንን እንሰዳለን። ሰላም በተሞላበት መናፈሻ እንቀመጣለን ሆኖም ወደ ውስጣችን ከመመልከት ይልቅ አላፊ አግዳሚውን እየገላመጥን እንዳኛለን።

በእኛ ላይ ምን ችግር እንዳለ ሁሉ አናውቅም። በድርጊታችን ውስጥ ምን ያህል ብክነት እንዳለ አናስተውልም፤ ምን ያህል ደካማ እንደሆንን፣ ምን ያህል ራሳችንን እንደምንረብሽ አናስተውልም። ከዚህ የባሰው ደግሞ ማንም እንዲህ እንድንሆን ያላስገደደን መሆኑ ነው፤ ሁሉንም ችግር የፈጠርነው በራሳችን እጅ ነው።

ለስቶይኮች ይህ አይሰራም። ዓለም የእኛን ሰውነት መቆጣጠር እንደምትችል ያውቃሉ- ወደ እስር ቤት ልንጣል እንችላለን ወይም አገር ሰላም ብለን በወጣንበት ዶፍ ዝናብ ሊወርድብን ይችላል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን በእኛ ቁጥጥር ስር የሚገኘው አእምሯችን ነው። ልንጠብቀውም የተገባ ነው። በአእምሮህ ላይ ቁጥጥርን ማድረግህ ከሁሉም የላቀ ሃብት ነው።

@lifein1553