Get Mystery Box with random crypto!

ፍትህ ከመስፈኑ የተነሳ ተኩላዎች ፍየሎችን መብላት ያቆሙበት ዘመን ይሉታል የታሪክ ሊቃውንታት። ዘራ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

ፍትህ ከመስፈኑ የተነሳ ተኩላዎች ፍየሎችን መብላት ያቆሙበት ዘመን ይሉታል የታሪክ ሊቃውንታት። ዘራፊና ቀማኛ የጠፋበት ደጃፎች ተከፍተው የሚታደሩበት ይሉታል ሙጨሪኾች። አዎ በእርግጥም ነፍሱን ለአላህ ባሳደረ ፍፁም ፍትሀዊ መሪ አለም ትተዳደር ነበርና ነው። ሚስቱ የቀድሞው ኸሊፋ የዐብደላህ ኢብኑ መርዋን ልጅ ነበረች። አባቷ በተለያዩ ውድ ጌጣጌጦች አስውቧት። በወርቅ በተለበጡ ሸዋሊያዎች፣ በሚያብረቀርቁ የንገት ጌጣጌጦች፣ ውበትን በሚያጎናፅፉ የእግር አልቦዎች ተሽቀርቅራ አምራለች። ታዲያ እኚህ ሰው መንበረ ስልጣኑን ከአባቷ ሲረከቡ ለአስቸኳይ ጉዳይ እንደሚፈልጓት ነግረው ወደ ክፍላቸው አቀኑ። እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ጀመሩ:-

"አባትሽ በስልጣን ዘመናቸው የሰጡሽ ጌጣጌጦች የበዙ ናቸው። ይህ ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት የወጣ ንብረት ነውና እንድትመልሺ እጠይቅሻለሁ። ካልሆነ ግን የሙስሊሞችን ሐቅ ይዘሽ አብረን መኖር አንችልም። ጌጥሽን ወይም እኔን ምረጪ" አሏት።

አንገቷን ወደመሬት አቀርቅራ ንግግራቸውን ስታዳምጥ የነበረችው ፋጡማ
"አንተ የወደድከውን ጀነት እኔ የምጠላ ይመስልሀልን አኼራንና ድህነትን መርጬ ካንተ ጋር እኖራለሁ" አለች እጇን ወደ ጌጧ መክፈቻ እያስጠጋች። አውርታም አልቀረች ጌጧን ሁሉ አውልቃ አስረከበች። ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የነበረውን ውብ መኖርያ ቤታቸው ሳይቀር ወደ ሙስሊሞች ግምጃ ቤት አስገቡት። ግና ማረፊያ ይሆናቸው ዘንድ አንገት ማስገቢያ ቤታቸውን ሲቀይሩ ኻዲም ስላልነበራቸው ባለቤታቸው ፋጡማ ጭቃ ታቦካለች እሳቸው ተቀብለው ይለጥፋሉ። እኚያ ሰው ዑመር ኢብኑ ዐብዱል አዚዝ ይሰኛሉ። እንዲህ አይነት ፍትህ ነው ተኩላ ፍየልን እንዳይበላ ያደረገው።

[ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!!]
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

[ሀሳብ ለመቀያየር በግሩፓችን]
https://t.me/ARADO_MUSLIM_SHBAB_JEMEA_GROUP