Get Mystery Box with random crypto!

በባህርዳር ከተማ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ተግባር ያልገቡ ባለሀብቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ | ኩሩ ሚዲያ ኔትዎርክ - Kuru Media Network

በባህርዳር ከተማ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ተግባር ያልገቡ ባለሀብቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው ተገለጸ፦
በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የኢንዱስትሪእና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብርሀን ንጉሴ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከህልውና ጦርነቱ በፊት እና በኃላ በርካታ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን ተቀብለው በአሰራሩ መሰረት እያስተናገዱ እንደሆነ ገልጸዋል።
የህልውና ጦርነት ስኬታማ መሆን የባለሀብቶች ሚና እጅግ በጣም ሰፊ ድርሻ የወሰደ ነበር። ባለሀብቶች በህልውና ጦርነቱ ወቅት ምርታቸውን ሳያቋርጡ ሲሰሩና መንግስትን ሲደግፉ እንደነበር ተገልጿል።
በአሁኑ ጊዜ በግንባታ ላይ ያሉ 142 ፤ 277 ግንባታ ያጠናቀቁ፤ 143 ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተው በማምረት ላይ ሲሆኑ 11,546 የስራ እድልም ፈጥረዋል። ከ2010 ጀምሮ 600 የሚሆኑ ባለሀብቶች ፈቃድ ወስደው ወረፋ እየተጠባበቁ ሲሆን 72 ፕሮጀክቶች ውላቸው የተቋረጠ ነገር ግን ቅሬታ በማቅረባቸው ምክንያት ችግራቸው ድጋሜ እያተየ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሃላፊዋ አያይዘውም ወረፋ እየተጠባበቁ ከሚገኙት መካከል በተለይ ማሽን አዘጋጅተው ወደ ተግባር ለሚገቡና የስራ እድል ለሚፈጥሩ ባለሀብቶች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።
2014ዓ.ም
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ዩቱዩብ https://bit.ly/34Dxk7J
ቴሌግራም https://t.me/KuruMediaNetwork
ፌስቡክ https://fb.com/KuruMediaNetwor