Get Mystery Box with random crypto!

ለእግዚአብሔር ደሰታ እናገልግል! አገልግሎት ሰዎች ማስደስት ሳይሆን አገልግሎት እግዚአብሔርን | Kingdom of God🏥🏥🏥

ለእግዚአብሔር ደሰታ እናገልግል!

አገልግሎት ሰዎች ማስደስት ሳይሆን አገልግሎት እግዚአብሔርን ማስደሰት ነው።የአንድ አገልጋይ ውድቀት የሚጀምረው የጠራውን እግዚአብሔር ማስደሰት ትቶ ለሰዎች ደስታና ዕርካታ ለማገልገል ሲሮጥ ነው።

የትውልዱን ስስት እያወራህ የጌታ ባሪያ ልትሆን አትችልም።ትውልዱ የሚፈልገውን እየጠነቆልክ የእግዚአብሔር ሀሳብ አገልጋይ ለመሆን በጣም እረፍዶብሃል።

ትውልዱ የሚድነው የሚፈልገውን ስትነገረው ሳይሆን እግዚአብሔር የፈለገውን ስትነገረው ነው።ቤተክርስቲያን የተጨናነቀችው የእግዚአብሔርን ለመስማት በሚፈለጉ ሰዎች ሳይሆን የራሳቸውን መስማት በሚፈልጉ ሰዎች ነው።ይህ የሆነበት የመጀመሪያው ምክንያት የእግዚአብሔርን ሀሳብ እርሱም ክርስቶስን የሚያገለግሉ ሳይሆን ልብ ወለዳቸውን የሚተርኩ ስለ በዙ ነው።

መድኃኒታችን የፕሮግራም ማድመቂያ አይደለም እርሱ የማያልቅ ፕሮግራማችን ነው።እርሱ የፕሮግራማችን መጀመሪያ ነው መካከለኛም ነው መደምደሚያም ነው።ስንጀምርም እርሱ ነው ስንጨርስም እርሱ ነው።