Get Mystery Box with random crypto!

የእግዚአብሔር የሆነ ነገር ሁሉ አይቅለልባችሁ የእርሱ የሆነውን የሚያቀልባችሁን ማንኛውንም ምክንያት | Kingdom of God🏥🏥🏥

የእግዚአብሔር የሆነ ነገር ሁሉ አይቅለልባችሁ የእርሱ የሆነውን የሚያቀልባችሁን ማንኛውንም ምክንያት አስወግዱት።

የእግዚአብሔር ነገር አክብዶ የቀለለ የለም።የእግዚአብሔር የሆነውን አቅልሎ የከበረ የለም።ዋናው ነገር ዋናውን ነገር ዋና ማድርግ ነውና ዋናውን ሊያቀልባችሁ የተነሳው ተራ አጀንዳ በመተው እግዚአብሔር መጀመሪያ ያለውን አንሡ።

የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ ዋጋ መስጠት የሚጀምረው ከvalue system ነው።ማንም ሰው ለእግዚአብሔር ነገር ያለው value system እንድ እግዚአብሔር ሃሳብ ወይም እንድ እግዚአብሔር ቃል አቆጣጠር እስካልሆነ ድረስ መቼም የእግዚአብሔር ነገር በእርሱ ዘንድ አያከብርም።

የእግዚአብሔር ጉዳይ በእግዚአብሔር እውነት ይተረጎማል እንጂ በእኛ መረዳት አይብራራም።