Get Mystery Box with random crypto!

🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidstarsema6 — 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidstarsema6 — 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
የሰርጥ አድራሻ: @kidstarsema6
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

👨‍🦳👨‍🦳👴👴የዱሮውን ዘመን ዐስብ፥የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል አባትህን ጠይቅ፥ያስታውቅህማል ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ይነግሩህማል። ዘዳግሞ 32÷7👨‍🦳👨‍🦳👴👴

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-16 06:08:14 #የፍልሰታ_ስጦታ!... እውነተኛ ታሪክ
(...የፍልሰትዋ ተአምር...)

ከቅርብ ዓመታት በፊት ነው! በግብፅ ይኖር የነበረው ወጣት ምንም እንኳን ገና በወጣትነቱ በትምህርት፣ ሃብትና ትዳር "የተሳካለት ሰው" የሚባል ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በፊት ግን ይመካበት የነበረውን ትዳሩን ጥያቄ ውስጥ ገብቶበታል:: ባላወቀው ምክንያት የሚወዳት ባለቤቱ ከወገብ በታች ፓራላያዝ ትሆናለች:: እርስዋን ለማሳከም ያልሄደበት ሆስፒታል ባይኖርም የሚሄድበት ሆስፒታል እንደሌለ ግን ተነግሮታል:: "የያዛት በሽታ አይድንም!" የሚል መራራ ሐዘንን ሰምቷል! ብዙ ያሰበለት የልቡ ፍቅር ሲጠወልግ፣ የወደፊት ሕልሙ ሲጨልም፣ የልጅ አምሮቱም እንዲሁ ላይመጣ ሲቀር አስቀድሞ አውቋል ባለቤቱ አልጋዋ ላይ ትበላለች አልጋዋ ላይ ትፀዳዳለች! ለጥቂት ጊዜ እዛው አልጋዋ ላይ ሳምንታትንና ወራትን ስታሳልፍ ከራሱ ጋር እየታገለ በትዕግስት ቢያስታምማትም ከዚህ በላይ መቆየት ግን በአካል ሲኦል የመግባት ያህል ሁኖ ተሰማው:: ስለዚህ በፍቺ ከርስዋ ጋር መለያየትን መረጠ:: ነገር ግን ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት አስቀድሞ የንስሃ አባቱን ማማከር እንዳለበት አመነና ወደሳቸው ሄዶ ያሰበውን ይነግራቸዋል!

እሳቸው ግን በፍፁም እንደማይሆን፣ ጌታ "መፋታትን እጠላለሁ" እንዳለ፤ ያጣመረውን እርሱ መፍታት እንደማይገባ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ ያስረዱታል:: ከዚያም ሁለቱም በጸሎት እንዲተጉና ወደ እመቤታችን እንዲያመለክቱ ተነጋግረው ይለያይሉ:: የንስሃ አባቱም የወጣቱንና የባለቤቱን የክርስትና ስማቸውን ፅፈው በመቅደሱ መንበር ላይ አስቀምጠው ለ 3 ቀና ያህል በፅኑ ፆምና ጸሎት እየተጉ ቆዩ:: ከ3 ቀን ብኋላ ወጣቱ በሕልሙ፣ እርሱ ከሚሰራው ፎቅ ተወርውሮ ወድቆ ሲሰባብር፣ ሰዎችም መጥተው ሲያለቅሱለት፣ ባለቤቱ ግን መጥታ ለሰዎቹ "ምንም እንዲህ ተሰብሮ ቢጎዳም ከልቤ አፈቅረዋለሁና አልለየውም! ባለቤቴ ነውና አልለየውም! እስከ ሞት ድረስ አስታምመዋለሁ" ስትላቸው በሕልሙ ያያል:: ወጣቱም "ይሄ የጌታ መልዕክት ይሆን እንዴ?" ይልና ያየውን ሄዶ ለንስሃ አባቱ ይነግራቸዋል! እሳቸውም የእግዚአብሔር እጅ በድንግል ማርያም ምልጃ ስራውን እንደሚሰራ፣ ምንም እንኳን ሚስቱ በሞት አፋፍ ላይ ብትሆንም ሞትን የሚገድል ክርስቶስ ግን እንደሚፈውሳት፣ ፍቺዉንም መሰረዝ እንዳለበት የሚናገር ሕልም እንደሆነ ይተረጉሙለታል::

እርሱም "ያሰብኩትን ሳይሆን ጌታዬ ያሰበው ይሁን" ብሎ ፍቺውን ሰርዞ ለሚወዳት ባለቤቱ በፀሎት ፈውስን ይለምን ጀመረ:: ከጥቂት ሳምንታት ብኋላ የተወደደው
#ጾመ_ፍልሰታ ይገባና እርሱም 14 ቀናት በተመስጦ በጾምና በጸሎትና ቆይቶ ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችንን የትንሳኤዋና የዕርገትዋን በዓል ያከብር ዘንድ ወደ ቤ/ክ ሲሄድ፣ ባል ከሚስቱ ልጆችም ከወላጆቻቸው ጋራ ጧፍ አብርተው ሲዘምሩ ተመልክቶ ልቡ በሐዘን ይመ'ታል! ልጅም ሚስትም በማጣቱም በማዘን በቤ/ክኑ በነበረው የእመቤታችን ስዕለ አድኅኖ ፊት ተደፍቶ <እመቤቴ ሆይ የወጣትነት ዕድሜዬን በደስታ ያልፈፀምኩበት፣ የልቤን ጓደኛ በበሽታ ያጣሁበትስ ምን ዓይነት ቀን ነው? እርስዋ በአልጋ ታስራ የምትቆይበት እኔ ደግሞ በእርስዋ ስቃይ የምሰቃይበት እስከመቼ ነው? እባክሽን ጽንሱን ያዘለለ ድምፅሽን አሰሚኝና እኔም ለክብርሽ ልዝለል! እባክሽን ለቶማስ የሰጠሽውን ሰበንሽን በሚስቴ ላይ ጣይ!> እያለ ምርር ብሎ ያለቅሳል::

ከቤ/ክ መልስ ወደ ቤቱ ሲገባ ግን ሚስቱ ከአልጋዋ የለችም! ፍርሃት ፍርሃት አለው! ምናልባት ሞታ ሊቀብርዋት ሂደው ይሆን? ብሎ አሰበ:: ደግሞ ቆይቶ "አይ! አይደለም! በፍፁም አይሆንም" ይላል ወደ ኩሽና ቤቱ ሲገባ ፍፁም ለማመን በማይቻል መልኩ ሚስቱ በ2 እግርዋ ቆማ ስትሰራ ያያታል:: አንደበቱ መናግር ቢያቅተውም ዓይኖቹ ግን የዕንባን ዘለላ እያፈለቁ ይናገሩለት ጀመር:: ሚስቱም ስታየው እየሮጠች መጣችን ተጠመጠመችበት:: <አንተ ወደ ቤ/ክ ከሄድክ ብኋላ ቤታችን ባለው የእመቤቴ ስዕለ አድህኖ ላይ ተንበርክኬ አለቀስኩ! "እመቤት ሆይ ችግሬን ታውቂያለሽና አማልጂኝ ለተጠማ ውሻ የራራው ልብሽ እባክሽ ለኔም ይራራልኝ! ቆሜ የትንሳኤሽንና የዕርገትሽን በዓል አክበር ዘንድ እግዚአብሔርንም አመሰግነው ዘንድ ፈውሺኝ" አልኳት::

ከዚያም አንዲት ብርሃን የለበሰች ሴት መጣችና "ተነስተሽ ቁሚ" አለችኝ! እኔም "መቆምኮ አልችልም" አልኳት:: እርስዋም "ልጄ ሆይ አይዞሽ! ጌታ ፈውሶሻልና አቆምሽ ዘንድ መጥቻለሁ" አለችኝ! ከዚያም ሁለት እጄን ይዛ አስነሳችኝ! ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ ስሜትም ተሰማኝ! ኃይልም በእግሮቼ መሃል አልፈና እግሮቼም ፀንተው ቆሙልኝ ከዚያም ባርካኝ ከዓይኔ ተሰወረች ብላ ለባልዋ ትነግረዋለች! እርሱም ከሚሰማው ነገር የተነሳ ዲዳ ሆነ በእግርዋም ተንበርክኮም ሊፈታት እንዳሰበና ተስፋ ቆርጦ እንደነበረ ይቅርታ ይጠይቃታል:: እርስዋም ይቅር ብላው ተቃቅፈው ጌታን አመሰገኑ! ተያይዘውም ትንሳኤዋንና እርገትዋን ለማክበር በጋራ ወደ ቤተክርስቲያን አመሩ! ስሟ በጌታ ዘንድ የሰለጠነ ንግስታችን እመቤታችን ፍቅርዋ በልባችን ጣዕሟም በአንደበታችን ያሳድርብን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ትለምንልን! ኣዕምሮውን ለብዎውን ትሳልብን ታሳድርብን!

#ምንጭ፦ Miracles of Saint Mery in Coptic orthodox church (Pop shinoda 3rd)

https://t.me/betelhem29
135 views03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 20:28:24 #ቤተ_ማርያም

#መስከረም

Title #አለን_መመኪያ

Duration ::



አለን መመኪያ አለን እናት

አለን መመኪያ አለን እናት
#ቅድስት_አርሴማ ፅኑ ሰማዕት

አለን መመኪያ አለን እናት

እምነትሽ ፅኑ #ፀጋሽ ልዩ ነው
በምልጃሽ አምኖ #ለሚማፀነው
#ቅድስት_አርሴማ ፅኑ ሰማዕት
ደርሰሽ አድኝኝ አንዳልሞት


አለን መመኪያ አለን እናት
……………………………
………………………………
………………………………

የእምነት ብርሃን አርማ መለያ
#ቅድስት_አርሴማ_ዘአርመንያ
ዲያብሎስ ወድቋል በፀበልሽ
ለተማፀነሽ ፈጥነሽ ስትደርሽ


አለን መመኪያ አለን እናት
……………………………
………………………………
………………………………

#አምላክ_መረጠች_ከዓለም_ለይቶ
#ፅኑ_እምነትሽን ፅናትሽን አይቶ
ለኛም ለምኝ እንድንፀና
………………………………………
……………………………………
………………………………………
………………………………………

@KIDSTARSEMA6 @KIDSTARSEMA6

@KIDSTARSEMA6 @KIDSTARSEMA6

@KIDSTARSEMA6 @KIDSTARSEMA6

@KIDSTARSEMA6 @KIDSTARSEMA6
227 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:29:04
ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?” (ቅዱሳን ሐዋርያት)

ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የእመቤታችንን ዕርገት ባየ በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት “ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?” ብለው ከየሀገረ ስብከታቸው ተሰባስበው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዋን ይሰጣቸው (ዕርገቷን ያሳያቸው) ዘንድ ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ጌታችንን ጠየቁት፡፡ እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ እመቤታችንንም ሐዋርያትንም አቍርቧቸዋል፡፡ እነርሱም እመቤታችንን በዓይናቸው ከማየት ባሻገር አብረው ሥጋውን ደሙን ተቀብለዋል፡፡









358 views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 19:58:52 የፍልሰታ ዋዜማ

በዲያቆን ሔኖክ ሃይሌ


የእናታችን የአማላጃችን የመመኪያችን የድሕነት ምክንያታችን #የድንግል_ማርያም_ሞትና_ትንሳኤ የምናስብበት #ፆመ_ፍልሰታ ልትገባ ነው።።28: 29:.30: ፨፨፨

እነሆ የጌታ #ባርያ_ብላ እራሷን በፍፁም ትሕንና ዝቅ አድርጋ የኛን ድሕነት ያስጀመረች እናታችን የምትሞትበት ቀንም ሲደርስም እነሆ #የጌታ_ባርያ_ብላ የሞትን ፅዋ የተቀበለችበት።። ሰው እንደመሆኗም ጥቂት የሞት ፍርሃት በከበባት ጊዜ እነ #ቅዱስ_ገብርኤል እንደ ልማዳቸው #ማርያም_ሆይ አትፍሪ ያሉበት በልጅነቱ እቅፍ ድግፍ አደርጋ የያስተኛችው ልጇ እናቱን በሞት እንቅልፍ ሊያስተኛ የወረደበት ታላቅ ክስተት የምናስብበት ፆመ ፍልሰታ ከፊታችን ቀርባለች።።።


እኛም እንዲህ እንላታለን #እናታችን_ሆይ_ብቻሽን_አትነሺ። በስምሽ የምትምለውን #ሃገራችንን
ይዘሽ ተነሺ።#በጦርነት_እየተለበለበ_በልጅሽ ማመኑን ያላቆመ #ሕዝብሽን ይዘሽ ተነሺ። ለእርዳታ ብለው በፆምሽ ወቅት የሚሰጣቸውን ብስኩቶች የፆም ነው ወይስ #የፍስክ ብለው የሚጠይቁ ባለ ማዕተብ ልጆችሽን ይዘሽ ተነሺ።



አበው ስለ ዕረፍትዋ እንዲህ በለዋል።።

ሌሎች #በድንግልና_የኖሩ ሴቶች ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥም በማለት ሞትን #ተቃወሙ።።። #ድንግል_ማርያም ግን በድንግልና አንድ ልጅ በመውለድ በልጇ ሞት እራሱ እንዲሞት አደረገችው።።።።


በዚች ቀን ታላቁ #ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው።። በዚች ቀን #ነቢዩ_ኢሳያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ስፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው።።።በዚች ቀን #ብርሃን_ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ #ከመቃብር_ራሳቸውን ቀና አደረጉ።።

#አርያም_በጣፋጭ_የመላዕክት_ዝማሬ ተሞላ።።።ምድር ደግሞ ኀዘን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች።።

ከወለደችም በኋላ ድንግልናዋ ላልፈረሰ ለእርሷ ከሞተች በኋላም ስጋዋ ሊፈርስ #አይገባውም።። #ፈጣሪን_በደረትዋ ያሳረፈች እርሷ በመለኮታዊ ድንኳን ማደር ይገባታል።።።።

#የአምላክ_እናት_ሆይ በመውለድሽ ምክንያት #ድንግልናሽን እንዳልተውሽ በመሞትሽም ይህንን አለም #አልተውሽም።። የሕይወት እናት ነሽና ዛሬም ወደ ሕይወት #ተሻገርሽ።በአማላጃችን ሆይ ነፍሳችን በኃጢአት ከመሞት ታደጊ።።።

ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ

የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በስጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍት እርሷን የሚመለከቱ የመጨረሻወቹን ምስጢራትም ማየት ነበረባቻው። ይህም የሆነው የክርስቶስ የእርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው አለም ለመሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው።።።ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ












282 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 18:19:05 ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በሰማ እትነት መከራ የተቀበሉበት                                 እለት ነው። ቅዱስ ቂርቆስ እድሜው የሦስት አመት ሳለ እናቱ ቅድስት እየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው። የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት።  መኮንኑም ወደ እርሱ አስጠራትና ስለ አምልኮ…
363 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 18:19:05   ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር።  ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በ እሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ።  የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር።  ይህን ያየችና የሰማች እናት ቅድስት እየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት።  ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት እየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ጸለየ።  ያን ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት።  ቅድስት እየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች። እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው።  ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም ልጄ ሆይ አንተ ከ እንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው።  ቅድስት እየሉጣም ለልጇ ያች የተወለድክባት እለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት አለችው።  የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት እየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወደያውኑን ቀዘቀዘ።  ከ እግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የ እሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።  ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ።  ከ እግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው።  መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው።  በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው።  ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም  በረከትን እንደሚያገኝ ቃል ኪዳን ሰጠው ።  እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣን በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን አሜን። እንኳን ቅዱስ ገብርኤል በዓል አደረሳችሁ!!!











312 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 18:19:05 ሕጻን አዱስ ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው።  አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታየም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኅዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው።  እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ።  ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ።  መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ስቃይ፡ ታላላቆች አንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው።  እናቱ ቅድስት እየሉጣንም ከ እርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰ  ቃያት።  እግዚአሔብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር።  ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ።  በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት።  ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር።









211 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 18:19:04 ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በሰማ እትነት መከራ የተቀበሉበት                                 እለት ነው።

ቅዱስ ቂርቆስ እድሜው የሦስት አመት ሳለ እናቱ ቅድስት እየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው። የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት።  መኮንኑም ወደ እርሱ አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት።  ቅድስት እየሉጣም መኮንን ሆይ፡ እድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው።  ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው።









204 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 12:00:26

290 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 11:59:51

255 views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ