Get Mystery Box with random crypto!

ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በሰማ እትነት መከራ የተቀበሉበት             | 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊

ሐምሌ 19 ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በሰማ እትነት መከራ የተቀበሉበት                                 እለት ነው።

ቅዱስ ቂርቆስ እድሜው የሦስት አመት ሳለ እናቱ ቅድስት እየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው። የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት።  መኮንኑም ወደ እርሱ አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት።  ቅድስት እየሉጣም መኮንን ሆይ፡ እድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው።  ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው።