Get Mystery Box with random crypto!

ላንተ ላንቺ ነው አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእ | 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊

ላንተ ላንቺ ነው

አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን በምስጋና እንዳሉ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያለቅሱ ጀመረ እንባቸው መሬት ጠብ..ጠብ አለ። ምእመኖቹ ጨነቃቸው ምን ሆነው ይሆን ብለው አዘኑ። መምህሩ ባፋቸው የሚሉት ነገር አላቸው። ጠጋ ብለው አደመጧቸው "
#ጌታዬ_ሆይ_እባክህ_ለቅዱስ_ስጋህና #ለክቡር_ደምህ_አብቃኝ" ነበር የሚሉት።

ምእመናኑ ተገርመው አባ ምነው ምን እያሉ ነው ብለው አፋጠው ያዟቸው። እርሳቸውም "አንተን ለማገልገል ለስጋና ለደምህ አብቃኝ" እያልኩ ነው። አሏቸው። ምእመኖቹም አባታችን ይህን ያክል ዘመን እያገለገሉ እንኳን ለርሰዎ እኛን እያቆረቡ እንዴት እንድህ ይላሉ አሏቸው።


እርሳቸውም "
#የመስቀሉ_ፍቅር_ገብቶኝ ለሰው ሳይሆን ለራሴ ብየ የማገለግልበት ስጋና ደሙንም ፍቅሩ ገብቶኝ የምቀበልበትን ቀን ነው የምለምነው" ብለው መለሱ።

ወዳጆቼ


ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ክርስትና በየሰፈሩ አለ። ለስው የምንሰራ ወይም ግዴታ ተጥሎብን የምናገለግል ብዙ ነን። "አገልግሎት ማለት የፈቃደኝነት ባርነት ነው" እንዲሉ በእንዲህ መልኩ መጓዝ ሲገባን ሰው አይተን ጀምረን በሰው አገልግሎት ያቆምን ብዙ ነን። አንዳንዶቻችን፦ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ መፆም፣ መስገድ፣ መፀለይ፣ መቀደስ፣ መዘመር፣ መስበክ፣ነጠላ መልበስ ግዴታ አልያም ህግ ነው ብለን የምንተገብር ብዙ ነን።
#መቼ_ነው_ግን_ፍቅሩ_ገብቶን_ስለፍቅሩ እነዚህን የምንተገብራቸው። ሰው ያየናል ይደረስብናል ብለን ሃጢአትን ከመስራት የምንከለከል ብዙ ነን።


አምላክን ፈርተን ሲኦል እንገባለን ብለን ክፉ ነገርን ሁሉ እንተዋለን። ግን ስለ ፍቅሩ ብለን ፍቅሩ ገብቶን ሃጢአት የሆነውን ሁሉ የምንተወው መቼ ይሆን? ወገኖቼ እየሰበክን እየዘመርን እያስቀደስንና እየቀደስን ያልዳን አለንና እርሱ ፍቅሩን ይሳልብን።።።። ሌላ ምንም አልላችሁም

https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29
https://t.me/betelhem29