Get Mystery Box with random crypto!

#ፍቅር_ከለለኝ_ከንቱ_ነኝ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር | 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊

#ፍቅር_ከለለኝ_ከንቱ_ነኝ

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር #ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ #ናስ ወይም #እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

ትንቢትም ቢኖረኝ #ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ

ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ፍቅር ይታገሣል፥

ቸርነትንም ያደርጋል፤

ፍቅር አይቀናም፤

ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም
የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥

አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤


ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም።።።።


1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 ÷1_8

እግዚአብሔር ለሁላችንም ፍቅርን ያድለን ከዚህ ሌላ የሚያስፈልገን ነገር የለም።።