Get Mystery Box with random crypto!

#ሐሙስ #በግዝት_በዓል_መስገድ_ይችላል?? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው | የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!

#ሐሙስ

#በግዝት_በዓል_መስገድ_ይችላል??

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ጸሐፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ በመባል ይታወቃል፡፡

ትሕትና ፍቅር መታዘዝ እንዲሁም የአገልግሎትን ትርጉም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ሕጽበተ ሐሙስ በመባልም እንደሚጠራ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም «ወሶበ ኀፀቦሙ እገሪሆሙ ነሥአ አልባሲሁ ወረፈቀ ካዕበ ወይቤሎሙ አእመርክሙኑ ዘገበርኩ ለክሙ … ወሶበ አነ እንከ ሊቅክሙ ወእግዚእክሙ ኀፀብኩክሙ እገሪክሙ ከማሁኬ አንትሙኒ ይደልወክሙ ትኅፅቡ እግረ ቢጽክሙ፡፡»፤ «እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንዲህም አላቸው ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?… እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል ሲል ተናግሯል፡፡ /ዮሐ.13-12-20/፡፡

ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተበት ወይም ራሱ ምስጢረ ቁርባንን የጀመረበት ቀን በመሆኑ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡

ይኸውም የሰው ልጆች ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ /ማቴ.26-26-29/፡፡ አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጐት ቀስ ብለው መጥተው የያዙበት ቀን ስለሆነ በዚህ ዕለት በለሆሳስ /ብዙ የድምጽ ጩኸት ሳይሰማ/ የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡

ሆኖም በአንዳንድ ሰዎች የሚነሳ ጥያቄ አለ። በግዝት በዓላት ላይ ሕማማት ቢውል ይሰገዳል ወይንስ አይሰገድም ተብሎ ይጠየቃል። በተለይ አሁን በሐሙስ እለት የእመቤታችን በዓል ይውላል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የግዝት በዓል ስለሆነ አይሰገድም የሚሉ አሉ።

ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው። የበዓሉን ዓላማ ካለማወቅ በዓሉ ምን እንደሆነ ካለማወቅ የመጣ ስለሆነ አይሰገድም ተብሎ መወራቱ ስህተት ነው።

እንደማጣቀሻ ይሁነን ዘንድ የግዝት በዓላት የምንላቸው እለተ እሁድ እለተ ቅዳሜ የሚካኤል በዓል(12) የእመቤታችን በዓል(21) በዓለ እግዚአብሔር(29) እነዚህ የግዝት በዓላት ተብለው በቤተክርስቲያናችን ይጠራሉ።

በእሁድና በቅዳሜ አይሰገድም ነገር ግን የሚሰገድበትም ጊዜ አለ። በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 19 ላይ አይሰገድም ካለ ቡኋላ ይህ ያልተወገዘበት አንቀጽ ነው ብሎ ይናገራል። ይህ ማለት የሚሰግድበት እሁድ አለ ማለት ነው የሚሰገድበት እሁድ መቼ ነው ከተባለ ሀጢያት በሰለጠነበት ሰዓት ዕለተ ሰንበት ቢሆን ይሰገዳል ማለት ነው።


ወደ ሕማማቱ ስንመለስ በመጀመሪያ ልናውቅ የሚገባን ነገር በዓሉ የስግደት በዓል መሆኑን መርሳት የለብንም። ዕለቱ ራሱ የስግደት በዓል ነው ከዐበይት በዓላት አንዱ ስቅለት ነው በዓበይት በዓላት ደግሞ መስገድ ወይንም ማዘን አይፈቀድም ይቺ ዕለተ ስቅለቷ ግን ትሰገድበታለች ምክንያቱም ዕለቱ የስግደት በዓል ስለሆነ ማለት ነው።

በሁለተኛ ደረጃነት ደግሞ በዚህ በሰሙነ ሕማማት የምንፈጽመው ስግደት የአምልኮ ስግደት ነው። የአምልኮ ስግደት በቤተክርስቲያናችን በ365 ቀን ውስጥ ይሰገዳል። ግዝት በዓል አያግደውም ስለዚህ የአምልኮ ስግደት ስለሚፈቀድ በሕማማቱም ያንኑ ነው የምንሰግደው ማለት ነው።

የሶስተኛ ደረጃ በዚህ በሰሙነ ሕማማት የእመቤታችን በዓል ራሱ መዋሉ በዚህ ሳምንት የደረሰባትን መከራና ስቃይ እንግልት አስበን አንዴ እየተነሳች እንዴ እየፈረጠች አምርራ ያለቀሰችበትን አስበን ይበልጥ የምንሰግድበት ነው።

ስለዚህ በሰሙነ ሕማማት ከጌታ ሕማም የበለጠ ሕማሙን የሚያሽር ምንም የግዝት በዓል የለም!!!!!!!!!!!

እንበለ ደዌ ወህማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሃነ ያብጽህክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ በፍስሃ ወበሰላም አሜን።

#ሼር_በማድረግ_ለሌሎች_ያካፍሉ!!!

@kidestaresema
@kidestaresema
@kidestaresema