Get Mystery Box with random crypto!

“ልጆቼ ፦ እግዚአብሄርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ | ✞ ኪዳነ ምህረት እናታችን ✞

“ልጆቼ ፦ እግዚአብሄርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሄር ልናቀርብ ይገባናል ፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን? እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሄርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሄርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት፤ እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት እግዚአብሄርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

(ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)
ቻናሉን ለመቀላቀል


ኪዳነ ምህረት እናታችን