Get Mystery Box with random crypto!

ከአንተ ጋር ያሉኝ አንዳንድ ጊዜዎች ዕድሜ ልክ ሳይሆኑ አፍታዎች ብቻ እንደሆኑ አውቃለሁ..ልክ እን | ኹሉድ ✍️

ከአንተ ጋር ያሉኝ አንዳንድ ጊዜዎች ዕድሜ ልክ ሳይሆኑ አፍታዎች ብቻ እንደሆኑ አውቃለሁ..ልክ እንደ ባህር አሸዋ ከእጆቻችን መካከል ተንሸራቶ በኖ እንደሚጠፋ አውቃለሁ..ነገር ግን ያ አሸዋ በእጄ ላይ እንዴት እንደሚሞቅ እንደነበር ማስታወስን እፈልጋለሁ,..ታሪካችን ያን ያህል እውነት እንዳልሆነ አውቃለሁ ነገር ግን ይህ የኔ ላንተ ያለኝ ስሜቴ ከምንም በላይ እውነት ነው,..መንገዶቻችን ተቃራኒ እንደሆኑ አውቃለሁ ነገር ግን አሁን ላይ ለኔ የአንተ ክንዶች በጣም አስተማማኝ ቤቴ ናቸው፣መጥላት ቢገባኝም እንኳን ለዘላለም አንተን እንደምወድህ አውቃለሁ..ምንም እንኳ ሕይወቴ ጨለማ  መራራ እና ከባድ የነበር ቢሆንም በሆነ ምክንያት መጥተህ ህይወት እንዲሰማኝ አድርገኸኛል ደስታን ዘርተህልኛል ታድያ ካንተ መለየትን እንዴት ለልቤ ላርዳው....