Get Mystery Box with random crypto!

​​●●◦ የይቅርታ መሐልይ ◦●● ማነዉ የፈለገኝ? በማይነጋ ሌሊት በማይመሽ ቀን መሀል ተዘርሬ ስ | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​​●●◦ የይቅርታ መሐልይ ◦●●

ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡

ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡

ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡

✰ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም


╔═══❖• •❖═══╗
@kezim_kezam
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@kezim_kezambot
❥❥__⚘_❥❥