Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ ናፊ ባ ክፍል ~ በአምባዬ ጌታነህ #አዲስ አበባ ፒያሳ ..ኦልድ ታውን(Old Tow | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​​​​ ናፊ ባ

ክፍል ~

በአምባዬ ጌታነህ
#አዲስ አበባ ፒያሳ
..ኦልድ ታውን(Old Town Bar & Restaurant)
የጣራው ስር መናፈሻ ነፋሻማነቱ ደስ ይላል። ጨረቃዋ በግማሽ ለመድመቅ ከኮከቦቹ ጋር የፅሐይን መጥለቅ ብቻ አሰፍስፋ ትጠብቃለች። ፍም የመሰሉት የምዕራብ ሰማዮች የምድርን አተካራ ለጥቃ የምትሰናበተውን ፅሐይ ለማስገባት አጅበዋታል። ይሄን ሁሉ ትዕይንት ፊትለፊቱ ካለ የቤት መስታወት ነው የሚመለከተው። "ምነው ወዳጄ ፍዝዝ ብለህ ቀረህ ምን እያየህ ነው?"አለ ዮዳሄ የጓደኛውን የመስፍንን አይን የሳበውን ትዕይንት ለመመልከት እየዞረ። መስፍን አንገቱን ነቀነቀና "ምንም ዝም ብዬ ፊት ለፊት ስመለከት በመስታውቱ ውስጥ ሰማዩን እየቃኘሁ ነበር"አለና የሚጠጣውን የሐበሻ ጃምቦ አንስቶ ችርስ አለው" ጠርሙሶቻቸውን ከፍ አድርገው"ችርስ ችርስ "ተባባለው ጠጡ።
ማዶ ጃንጥላው ስር በከፊል ጡቶቿን አጋልጦ ያሰጣ ልብስ ለብሳ የጭኖቿን ብርቱካናማነት የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ለብሳ ከሎሚ የነጡ ተረከዞቿና በአንደኛው እግሯ ላይ አሳርፋ አራዳዋን የምትልፍ አንዲት ሴት ፊት ለፊታቸው ተቀምጣ መስፍንና ዮዳሔን ትገላምጣለች። ነገር ግን አንዳቸውም ሊያይዋት አልቻሉም።
"ሁለታችንም የሚያመሳስለን ነገር አለ። ግን እስከመቼ ድረስ ነው በዚህ ኮንዲሽን የምንቀጥለው?"አለ ዮዳሔ ሁለቱንም እጆቹን አገጩ ላይ አስደግፎ " አላውቅም ዮዳሔ አታስጨንቀኝ ውስጤ ላይ የሚላወሰው ጥያቄ ይበቃኛል። አንተ ደግሞ አትጨምርብኝ እንጅ"አለና መስፍን ጃምቦውን ጭልጥ አድርጎ ጠጥቶ አስተናጋጇን ጠርቶ እንድትደግመው አዘዛት። ዮዳሔ ዝም ብሎ ተመለከተውና "ግን በእውነት ምንም ሊገባኝ አልቻለም ምን ሆነህ ነው ከእኔ የተለዬ እንደዚህ ያደረገህ ከቀን ወደቀን እየተቀየርክብኝ ነውኮ" "አንተ ላይ ብቻ አይደለም የተቀየርኩት ወዳጄ ራሴም ጭምር ላይ ነው የተለወጥኩት። አሁን ዝም ብለህ ጥያቄህን መጠየቅ አቁምና ጠጣ። ቀኑ ቅዳሜ ነው የቤቱ ቫይቭ ደግሞ ደስ ይላል። እዚህ እንስከርና ወርደን እንጨፍራለን"አለ መስፍን ፊቱ እንደተኮሳተረ "እሺ በቃ ጓደኛዬ "አለና ዮዳሔ ከፍ አደረገለትና ጠጥቶ "ሽንት ቤት ደርሼ መጣሁ"ብሎ ሄደ። መስፍን ዙሪያ ገባውን እያማተረ ሳለ ፊት ለፊት ከተቀመጠችው ልጅ ጋር ተፋጠጠ፡። ጠቀሳት ጠቀሰችው ሄዶ እንድትቀላቀላቸው ጠየቃት ተስማምታ ሶስተኛ ወንበር ስባ ተቀመጠች። ዮዳሔ ሲመጣ ደንግጦም ደስ ብሎትም "ከየት አገኘኻት ባክህ ብሎ ተቀመጠ። "ያው ብቻዋን ስለሆነች እኛም ብቻችንን ስለሆንን ከሁለት ሶስት መሆን ይሻላል ብዬ ጋበዝኳት እሷም ተስማማች"አለ መስፍን። "ጥሩ ነው ያደረከው "አለና ዮዳሄ ወደ ልጅቷ ፈገግ ብሎ ጠጋ ብሎ" እንተዋወቅ ዮዳሔ እባላለሁ። እሱ ደግሞ ብሎ ወደ መስፍን ሲዞር ገላመጠው በዚህ ጊዜ አንድ ነገር አስታወሰ"በፍፁም መጠጥ ቤት ላገኘኸው ሰው ሙሉ ራስህን ማስተዋወቅ የለብህም። የመጠጥ ቤት ስም ሊኖርህ ይገባል። እኔ ለምሳሌ በረከት በሚል ስም ነው የምተዋወቀው። የሚፈጠረው አይታወቅም አንተን የሚያጠቃህ ሰው ሰው የሚልክብህ ስምህን ነግሮ ነው ስለዚህ አንተም ስም ሊኖርህ ይገባል! ኧረ አሻፈረኝ ካልክ አይመለከተኝም ነገር ግን እኔን ለሰው ከማስተዋወቅህ በፊት ለማላቀው ሰው የምተዋወቅበትን ፌክ ስሜን መዘንጋት የለብህም"እንዳለው አስታውሶ " እ እሱ ደግሞ በረከት ይባላል "አለ ና የእሷን ስም ጠየቃት። "እኔ ሒወት እባላለሁ!" "ጥሩ ስም ነው በቃ እንጫወት ቆንጆ" ብሎ ብርጭቆውን ከብርጭቆዋ ጋር አጋጭቶ ፉት አለ። ጨዋታቸውን እያደሩ መጠጡም እየበዛ ሄደ።ጣራው ያለውን ነፋሻማነት እንደ እርጎ ከሚገመጠው ጃምቦ ጋር እያጣጣሙ እያለ ጃምቦ አልቋል ተብለው ታች ወርደው ክለቡን ተቀላቀሉ። ቆሞ የሚጠጣ ሞልቷል። የዘፈኑ ድምፅ ከቤቱ አልፎ ውጭ ላይ ይሰማል። የጨፋሪው ተከታይ ዜማ ለጉድ ነው።መስፍን ሒወትና ዮዳሔ እየጨፈሩ ባለበት ሽንት ቤት ደርሶ ሲመለስ ነፍሳቸውን አያውቁም። የሒወትና የዮዳሔ በፍጥነት መግባባትና መመቻቸት እያስገረመው ሙዳቸውን ላለመረበሽ ሒሳብ ከፍሎ ትቷቸው ወጣ።
ሒዎትዮዳሔ ለብዙ ጊዚያት የሚተዋወቁ ጓደኛሞች እንጅ ከስአታት በፊት የሚተዋወቁ አይመስሉም። ሰውነታቸው በላብ እስኪጠመቅ ድረስ ሲጨፍሩ ቆይተው ሲመለሱ መስፍንን ከቦታው አጡት። "እንዴ በረከት የት ሄደ?"አለች ሒዎት ቀድማ "አላውቅም። ምንም አልነገረኝም" "እንዴት ሳይነግርህ ይሄዳል? ነው ብቻውን ስለሆነ ደብሮት ነው?"አለች ሒዎት። "አይ እይደዛ አይደለም። ብቻውን ሆነ አልሆነ ግድ የለውም።በቃ ተይው እኛ እንዝናና አለና በጆሮዋ የሆነ ነገር አንሾካሾከላት፣ ከት ከት ብላ ሳቀችና ቶርክ መቶረክ ጀመረች። ዮዳሔ ወገቧን ይዞ ኤግለስ ያስጨፍራት ጀመር። "የአጨፋፈር አይነትና ጭፈራ ግን አንተ ጋር ነው ያሉት"አለችው ጆሮው ስር ተደግፋ "አመሰግናለሁ አንቺም በጣም ጎበዝ ጨፋሪ ነሽ ተመችተሽኛል"አላት "እኔም አመሰግናለሁ ሒሳብ እንክፈልና እንውጣ?!"አለች ሒወት "እሺ "አለና አስተናጋጇን ጠራት። ሒሳብ ለመክፈል እርስ በእርስ እየተገላገሉ ሳለ አስተናጋጇ "ሒሳብ ተከፍሏል። ጓደኛችሁ ነው ከፍሎ የሄደው እና ይቺን ወረቀት ደግሞ ለአንተ እንድሰጥህ ሰጥቶኛል "ብላ የተጠቀለለችውን ወረቀት ሰጠችው። ዮዳሔ ጥቅሏን ቀስ አድርጎ ፈታና አነበባት "ወዳጄ ራስህን ጠብቅ ጥንቃቄ ማድረግህን እንዳትረሳ። አገኘሁ ብለህ ዝም ብለህ ዘው እንዳትል ነግሬሀለሁ!"የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ነበር። ዮዳሔ ሳቅ አለና ወረቀቷን ጨምደድ አድርጎ ወደ ኪሱ አስገባት። "ምን ብሎህ ነው?" "ተይው ባክሽ ዝም ብሎ ነው"አለ እየሳቀ "ገብቶኛል።ተወው"አለች ሕሊና ፈገግ ብላ። "እሺ ከገባሽ ጥሩ እና "መሀል ሆቴል" ጋር አልጋ ብንይዝ አይሻልም ትያለሽ?" "አዎ ደስ ይለኛል ግን እስካሁን አያልቅም?" "እንጃ የሚያልቅ አይመስለኝም።ቸክ አድርገን እዛው አካባቢም መያዝ እንችላለን"አላትና ወጡ። በሲኒማ አምፒር ታጥፈው የግሪክ ቤተክርስቲያንን በግራ ትተው ተሻግረው መሀል ሆቴል ጋ ደረሱ። የእንግዳ ተቀባይዋም በስነስርዓት ከተቀበለቻቸው በኋላ አንድ አልጋ ብቻ እንደቀረ ነግራቸው ከፍለው ቁልፍ ይዘው ገቡ።

<በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ በጣለው ሲያተርፉ
ራሱን ሲጥል ግን - አይተውት አለፉ››
የሚል የቀዬ እርዚቅ
የሚል የሰው ግጥም የሚል የአበሽ ቅኔ
ልብ አውቃዬ ሆኖ
ልክ እንደ አገር መዝሙር እንዳልዘመርኩ እኔ
ከአፍታ ዕድሜ በኋላ
የሆነውን ሁሉ ታሪኬን ቀየርሽው
ከትናኝ ከልለሽ
ከብናኝ አራግፈሽ ወስደሽ ልትፈውሽው
ሰው አይቶ ያለፈውን
የጣልኩት ራሴን - አየሁ ስታነሽው!!
ይህን እኔ ያየሁ
ሰርክ እንዲህ እላለሁ፤
እንኳ ራስን ጥሎ - ገፍቶ ጣይ ባለበት
ሰው በሰው ላይ ሊያሴር - በሚማስንበት
በዚህ ከይሲ ዘመን - በዚህ የክፋት ዓለም
ሰው ራሱን ሲጥል
እያለፉ መሄድ - የሚገርም አይደለም፤

እልፎች ራስ ጥለው - ተስፋ ሲቆልፉ
እልፎቹም ገፍተረው - እየጣሉ ሲያልፉ
ነገር ግን
ከአመድና አቧራ - ከደይን የሚያነሱ
ድንገት ተወርውረው - ለጭንቅ የሚደርሱ
ጥቂት ሰዎች አሉ
አንቺን የመሰሉ !!
ጥቂት ሰዎች አሉ
አንቺን የመሰሉ!!"ብሎ በውብ አነባበብ ግጥሙን አነበበላት ተሕሚድ

ሼር
@kezim_kezam

የደራሲው ቀደምት ስራዎች
#መቅደላዊት
#ኤሴቅ