Get Mystery Box with random crypto!

I ህቡዕ ገጽ ህቡዕ ገጽ | ኬልቅያስ

I ህቡዕ ገጽ
ህቡዕ ገጽ
ህቡዕ ገጽ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
ክፍል ሁለት

2008 ዓ.ም ባሌ ጎባ
እሁድ ምሽት 1:30

የተሰበሰበው ሰው የሚሆነውን ሲጠባበቅ ሁለት ሕግ አስከባሪዎች እየሮጡ መተው ያለማቋረጥ አንዱ ይደበድበው ጀመር። ዱላው ሲጀመር ውሱን ሰዎች " ኧረ እብድ ነው ተውት" የሚል ድምጽ ቢያሰሙም እምብዛው ግን " ልብሱን አስወልቆ ነው ኢሄንን መግረፍ ምን እብድ ነው? አውቆ አበድ አስመሳይ።" ሲሉ ዱላውን በዝምታ ሲቀበል ቆይቶ በፓሊስ ዱላ ዓይኑ አካባቢ በተመታው ከባድ ምት መቆም ተስኖት ሰማይ ምድሩ ዞሮበት ወደቀ።

ህመሙን ተቋቁሞ ያለውን ኃይል ሁሉ ተጠቅሞ ተነስቶ ሲቆም አንድ ዓይኑ ተጋርዳለች። እንደምንም ሲመለከት ፖሊሶቹ ትተውት እየሄዱ ነው። ከቆመው ሕዝብ ጀረባ ስትጮህ የመጣችውን ልጅ ከበዋት ያረጓጋታል። ይህን ሁሉ ቆሞ ሲመለከት ከነዓን ነገሩ ግራ አጋብቶታል። ፍጻሜውን ለማየት እንደቆመ ተደብዳቢው ሰው "" ፍትህ ጎድሏል ሞት ተፈርዷል ነፍስ ታደጉ" እያለ መጮህ ሲጀምር ሕግ አስከባሪዎቹ ተመለሱ። " ኡሌ ሂን ቁፍኔ?" አለው አንዱ ደብዳቢው ከሁለቱ። "" ሕይወት አድኑ ነፍስ ታደጉ"" አለ ተደብዳቢው በድጋሚ። ከተመለሱት ቀድሞ ሲደበድበው የነበረው ተንደርድሮ ኩላሊቱን በከስክስ ቢረግጠው የኋሊት ሲወድቅ ጭንቅላቱን ድንጋይ አጊኝቶት ደሙ ይንቆረቆር ጀመር። ዳግም ተነስቶ ደሙ ፊቱን እያጠበው " የእግዚአብሔርን መቅደስ ቤትሽን ሰውነትሽን የምትወጂ ሌላውን መቅደስ እንዲፈርስ በጭካኔ ለተሞላሽ ላንቺ ፍርድ ይገባል።" እያለ ሰዎች ወደ ከበቧት ሴት መጠቆም ጀመረ።

ገሚሱ ሰው ነገሩ አልገባ ስላለው ትቶ ሄዷል። በዚ መሀል ነበር የኔታ ጀምበሩ ከዋሉበት ወደቤት እያቀኑ ተሰብሳቢውን ሰው ሲያዩ "" ሰአሊለነ ቅድስት"" ሲሉ ከነዓን ሰምቶ "አይዞት የኔታ ቀላል ነገር ነው" በማለት ምላሽ ሲሰጥ "ለመሆኑ ምንድነው?" በማለት ጥያቄ ሲሰነዝሩ " አንድ እብድ..."" ሳይጨርስ " ምን ሆነ ዝምተኛው?" አሉት የኔታ። አንዲት ሴት አባሮ ሰው ደርሶ ታደጋት ክፉ አላደረሰባትም። እንዲያውም እርሱ ነው በፖሊሶች ዱላ ቲኒሽ የተጎዳው።" ሲላቸው ደነገጡ። የኔታ ከዚ በላይ መታገስ አልወደዱም በህዝቡ መሀል አልፈው አንድ ዓይኑ ተራራ ያከለ የሚጮህ ሰውጋ ደርሰው "" ምን ገጠመህ ዝምተኛው?" አሉት።

ሕግ አስከባሪው "" ኢሲን ሩኩታ ኢቲሂንሲቂና" ሲል ከጎናቸው ያለ ከነዓንን ""ምንድነው የሚለው"" አሉት። " እንዳይመታዎት ነው የሚለው እርሶ ተጠንቀቁ"" አለ እርሱም አክሎ። የሚፈሰውን ደም ያበጠውን ዓይኑን አይተው የኔታ በስሜት "" የማታስተውል መምህርህን የምትደበድብ ተማሪ"" ብለው ሲጮሁ ሰው ሁሉ ትኩረቱ ወደረሳቸው ሆነ። "" ማነው ያበደ እርሱ ወይ እኔ ወይ እናንተ?" ሲሉ ሕግ አስከባሪዎቹ እሳቸውንም ለመምታት ዳዳቸው። ነገር ግን የሃይማኖት አባት መሆናቸው ሌላ ችግር እንዳይፈጥር ተው።

"" አንቺ ምን ስልጣን ኖሮሽ ነፍስ ላይ ሞት የምትፈርጂ"" አለ ደሙ እየተንጠባጠበ። " ሰው ባያይ አምላክሽ ሁሉን እንዲያይ አይምሮሽ ስለምን ዘነጋ?"" አለ ደግሞ። "" ማናት?"" አሉ የኔታ። "" እርሷ"" አለ አጠገቧ ደርሶ። "" ድረሱላት እርሷ ማህጸኗን ረግማለች ራሷን እኔ አይደለሁም ብላ ክዳለች ድረሱላት"" እያለ ደሙን እያዘራ ወደመጣበት እያነከሰ ይሮጥ ጀመር።

የኔታ ወደ ወጣቷ ተመግተው " ምን አጥፍተሻል ልጄ?" ሲሏት መንቀጥቀጥ ጀመረች። "አይዞሽ አሁን እረሰሱም ሄዷል አትፍሪ ንገሪን?" አሏት በተማጽኖ። " አፍ የለኝም አላወራም ጥፋቴን በጥፋት ሳርም ጥፋት የገጠመኝ ባይተዋር ምስኪን ሰው ነኝ። ሕመሜን ያልፋል ብዬ እሹሩሩ እያልኩ ሳላውቅ አሳደኩት ዛሬም ከወገቤ አልወርድ አለ። አልችልም በቃ አሁን አልችልም"" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። የነበረው ሰው ተደናገጠ። "" አንዷ ወጣት ምንድነው ግርግሩ?" ብላ ስትጠጋ ባየችው ነገር ተደናገጠች። "" ራሄል "" አለች ጮክ ብላ። " ምንሆንሽ ምን ገጠመሽ?" የኔታ ቀጥለው "" እስቲ ሁላችሁም ወዲያ ሂዱ ብቻዋን ላውራት" ሲሉ ከጥቂት ሰዎች ውጪ ሌላው ወደየመንገዱ አቀና። የኔታና የምታውቃት ማርታ ብቻ ከአጠገቧ ሲቀሩ ከነዓን ርቆ ቆሟል። ዝምታ ሰፈነ በድንገት ራሄል " አባቴ ነፈሰ ገዳይ ነኝ ልጄን የጣልኩ ጨካኝ" ስትል " እመብርሃን ድረሽ" አሉ የኔታ። " ከንድ ችፍግ ስር አስቀምጬው ስዞር እብዱ አየኝ ተከተለኝ ስሮጥ ከኋላዬ እየሮጠ ተመለሽ ክህደት ነው። ሲለኝ ጮህኩ ሰዎች ደርሰው ይኼ ሁሉ ሆነ። በኔ ምክንያት በበደሌ ለኔ የሚገባውን እብዱ ተቀበለ ሲደበድቡት እንኳን ተውት ለማለት ከእውነት ፍረሀት አሸነፈኝ።" አለች ራሄል።

የኔታ "ልጄ ነገሩ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም አንቺ ከዚህ ልጅ ጋር ወደቤት ሂጂ። እኔና ጓደኛሽ ቶሎ ብለን ሄደን ለልጅሽ ልንደርስለት ይገባል።" ብለው ከነዓንን ጠሩትና " እባክህን ወደቤቷ አድርሳት ብለው እየተቻኮሉ ከማርታ ጋር እብዱ ወደሮጠበት አቀኑ። የኔታ እብዱ የምን ጊዜው መገኛው እግር የማይበዛባት በተለየም ማታ ሰው የማይሄድባት ጎዳና ላይ መነኛውን ስለሚያውቁ ወደዚያው አቀኑ። ቦታው ላይ ሲደረሱ የኔታና ማርታ ባዩት ነገር አንባቸውን መቆጣጠር አቃታቸውና ቆመው አለቀሱ። እብዱ ደሙ እየፈሰሰ እሳት አንድዶ የሚለብሰውን ዲሪቶ አንጥፎ ሕፃኑን አስተኝቶ ከላይ እናቱ አልብሳ የጣለችውን ኩታ አልብሶት እርቃኑን ቁጭ ብሎ ያለቅሳል። የኔታ እንባቸውን እየጠራረጉ ተጠግተው " ዝምተኛው ዋጋህን እማምላክ ትክፈልህ ስለኛም አብዝተህ ጸልይ ስራህ ታላቅ ነው። እንካ ይሄን ልበስ" ብለው የኔታ የለበሱትን ካቦርት ሰጡት። ሕፃኑንም ወስደው ማርታ ታቅፋው ወደቤት አቀኑ። ቤት እንደደረሱ ከነዓን አጠገቧ ተቀምጦ ራሄልን ስታለቅስ አገኟት። "በይ አሁን ለቅሶሽን አቁሚ ይኸው ልጅሽ" አሏት የኔታ። ከማርታ ልጁን እያለቀሰች ተቀብላ አቀፈችው። "ቆይ ለመሆኑ የምልሽ ልጄ ዘንግቼው አባቱ ልጁን ለማሳደግ ፈቃደኛ አይደለም?" አሏት። " መቼ ልጁ መሆኑን አምኖ" አለች ራሄል። "" አንቺ ታውቂዋለሽ አይደል?" አሉና የኔታ አብራው የተኛችውን ሰው እንዴት አታውቀውም ምን ማለቴ ነው ብለው በራሳቸው ሲገረሙ " እንኳን እኔ እርሶም እሱም እሷም ታውቁታላችሁ" ብላ ወደ እያንዳንዳቸው ስታመለክት ሁሉም ደነገጡ። " ማነው እርሱ?" የኔታ ጠየቁ። ራሄል እያለቀሰች አንዴ በስስት ልጇን እያየች ሳግ እያነቃት "" አ...ባ ወል...ደ...."" ስትል የኔታ አቋርጠዋት "" የልጁን አባት እኮ ነው የምልሽ "አሏት ደንግጠው።

""አዎ እኔም የምነግሮት ቆቡን ስላላከበረ ዓለምን ካድኳት ብሎ ዓለምን ተሸክሟት ስለሚዞር እድሌን ስለሰበረ ልጄን አይደለም ምንኩስናውን ስለካደ ስለዚህ ሕፃን አባት ነው የምነግሮት።" አለች ቃላቶቿ ወላፈኑ እንደሚያቃጥል ነበልባል እየተንቦገቦገ። " ልጁ አባቱ መነኩሴ ናቸው ነው የምትይኝ?" አሉ የኔታ ደንግጠው ስሙን ለመስማት አቅም እያነሳቸው። " አዎ" አለች እያለቀሰች "" አባቱ አባ ወ...ል.....ደ........

ይቀጥላል
ሐምሌ 16/2014 ዓም