Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ የብርሀን በር | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ የብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከመንግስት ከተመደበለት መደበኛ እና የውስጥ ገቢ በጀት ለ2015 ዓ.ም. አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን ለመግዛት እና ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል።

1 የደንብ ልብስ
2 አላቂ የትምህርት እቃዎች
3 አላቂ የቢሮ እቃዎች
4 ሌሎች አላቂ እቃዎች
5 አላቂ የህክምና እቃዎች
6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
7 ቋሚ እቃዎች ለመግዛት የሚፈልግ ስለሆነ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል

ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋት 2:00- 7:00ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ። የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን አሽገው ዋናዉን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታዉ እስከሚከፈትበት ቀን ከጠዋት 4:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላል።ጨረታዉ በ11ኛዉ በስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፦
• ተጫራቾች የተጫረቱበትን እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
• ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸዉ በፊት የዉል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸዉ።
• ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምረዉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ መሞላት አለባቸው።
• ብርሀን በር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የእቃዎች ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20% ድረስ ለመቀነስ ወይም ለመር ብት አለው።
• ማንኛዉም ተጫራች ለናሙና /ለሳምፕል ያስያዘውን እቃዎች የጨረታ ውጤት ከተነገረ በኃላ 10 ቀናት ውስጥ መውሰድ አለበት ከዚህ ቀን ውጭ ዘግይቶ ለሚመጣ ተጫራች በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለ ቢበላሽ አይጥ ቢበላው ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናሳዉቃለን።
• ተጫራቾች የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦ ዋናው ሰነድ ውስጥ ማስገባት አለበት።
• ከተቋሙ የገዛችሁት የጨረታ ሰነዶች በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቶን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
• ጥቃቅን እና አነስተኛ የሆናችሁ ከምታመርቱበት ውጪ የምትወዳደሩ ከሆነ ሲፒኦ እና ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
• ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
• አድራሻ፡- አጠና ተራ ወረዳ10 ከተቃጠለው ህንፃ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0112792458 /0112739672


ለበለጠ መረጃ https://tender.2merkato.com/tenders/62f21eb22562a546f6cfc271?lang=am ይመልከቱ ወይም 6131ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን kefta.2merkato.com ይጎብኙ።