Get Mystery Box with random crypto!

እንባዬ ፈሰሰ በረታ ሀዘኔ ሀገሬ ስታንስ ፣ ዝቅ ሲል ወገኔ እውቀቱን ስላጣሁ፣ ስላልቻለ አቅሜ | ከጥበብ ማዕድ

እንባዬ ፈሰሰ
በረታ ሀዘኔ
ሀገሬ ስታንስ ፣ ዝቅ ሲል ወገኔ
እውቀቱን ስላጣሁ፣ ስላልቻለ አቅሜ
ልቤ ውስጡ ደማ ፣ ተሰበረ ቅስሜ !
ምን ታምር ከስቼ
ምን እድል አግኝቼ
ቀና ብላ ልያት ፣ ኢትዮጵያ እምዬ ?
ወረደ እንባዬ !

ተስፋ ባጣ- ከኔው
ደካማ አደረገኝ ፣ ኣይ የእግዜር ቅኔው
መቼ ነው ሚፈታ ፣ ትንቢት ትንሳኤዋ
መቼ ነው ሚሰማ ፣ ፀሎት ሱባኤዋ
ተሸርሽሮ ሳይፈርስ፣ የአድነቷ እርከን
መች ብርሃን ይሆናል፣ የኢትዮጵያ ቀን ?
መቼ ነው ድህነት ፣ ከምድሯ 'ሚሸሸው
መች ይሆን 'ሚነጋው፣ መች ነበር የመሸው ?
መላ ታሪኳ ላይ ፣ ተስፋ ተሰቅሎባት
እልፍ ትውልድ ያልፋል ፣ ችግሯን ያየባት
ምድሯ ኦና ሲቀር
ህዝቦቿ ሲያልቁ ይሆን ፣ ኢትዮጵያ 'ሚያልፍላት ?
ኧረ እኔ አልጠይቅም !

( አብርሃም ሙሉ ሰው)