Get Mystery Box with random crypto!

እቴ ባርሞኒካ የመግደርደር ዳንስሽ የኔም አነፋፉ እያፈዘዛቸው ዘመኔና ህዝብሽ እያዩን ይለፉ እቴ | ከጥበብ ማዕድ

እቴ ባርሞኒካ
የመግደርደር ዳንስሽ የኔም አነፋፉ
እያፈዘዛቸው
ዘመኔና ህዝብሽ እያዩን ይለፉ

እቴ በነጠላሽ
በማለዳው ጥምቀት በበሰበሰው
አከናንቢኝና
ተሸሽጌ ልለፍ የዚን ዘመን ሰው

እቱ በታቦቱ
በረጠበው ፊትሽ ሳቅ ልይና ልመን
በዚም ክፉ ጊዜ
ካገር እንባ በላይ የሴት ሳቅ ቢሰማኝ እንዴት ነው ሚታመን?

እቴ ሆይ በሎሚ
አርሞኒካ የዘጋው ያጎርናና ድምጼን
ሃሩር ያበላሸው መልከመልካም ገጼን
ውዴ ባሳደገሽ ስጪኝ እና አክሚው
ካንቺ ሽታ አይበልጥም ምን ቢወደድ ሎሚው

[ @dagim_dagii ]


አፈር ለሚበላው ለሚበሰብሰው
አንዴ ስጪኝ እና አንጀቴን ላርሰው