Get Mystery Box with random crypto!

ከዛሬ 2 ዓመት በፊት ግንቦት 25, 2020( እ.ኤ.አ ) በአሜሪካ ብዙ ጥቁሮች ለተቃውሞ አደባባይ | ከአለም ጋለሪ🌐

ከዛሬ 2 ዓመት በፊት ግንቦት 25, 2020( እ.ኤ.አ ) በአሜሪካ ብዙ ጥቁሮች ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጡ ያደረገ ክስተት ደረክ ቹብን በተባለ በነጩ ፖሊስ ባልደረባ ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ ጥቁር ሰው በመግደሉ ነበር ሁኔታው በወቅቱ በተንቀሳቃሽ ምስል መውጣቱን ተከትሎ ከአሜሪካም አልፎ በመላው አለም የምኖሩ ጥቁሮች ቁጣቸውን እንዲያሰሙ ያነሳሳ ነበር ግድያውም አሰቃቂ በሆነ መልኩ የፖሊስ ባልደረባ እግሩን በጆርጅ አንገት ላይ ለ8 ደቂቃ ከ 48 ሰኮንድ በማድረግ ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረጉ ነው በጊዜውም ጆርጅ መተንፈስ አቃተኝ እያለ ቢጮህም የምሰማውን ለማግኘት አልቻለም እንዳያመልጥ እጅ እግሩ ታስሯል በተኛበት ላይመለስ ይህችን አለምን በደረክ አማካኝነት ተሰናበታት ህይወቱ ካለፈም በኋላ ብዙዎች ጥቁሮች "የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አላት" በማለት አደባባዮችን አናወጡት የእውነት ነው የጥቁሮች ህይወት በምድር ባይሆንም በሰማይ ዋጋ አላት ይህ የሆነው በዛሬው ዕለት በዚህች ቀን ነበር ፡፡